Skip to main content
SearchLoginLogin or Signup

ድርቅ ተከላካይ በቆሎዎች በሚመረቱበት እና በሚሞከሩበት ጊዜ ሴት ገበሬዎች ይካተቱ

Amharic translation of DOI: 10.1007/978-3-319-76222-7_5

Published onOct 02, 2023
ድርቅ ተከላካይ በቆሎዎች በሚመረቱበት እና በሚሞከሩበት ጊዜ ሴት ገበሬዎች ይካተቱ
·

በናይጄሪያ ደቡብ ጊኒ ሳቫና አግሮ ኢኮሎጂካል ዞን  የሴቶች የእርሻ ላይ የድርቅ ተከላካይ በቆሎ ሙከራ ግምገማ

Abstract

ሴቶች በእርሻ ምርት እና በቤት ውስጥ የምግብ ደህንነት ላይ ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ፡፡

ነገር ግን በእርሻ ላይ በሚደረጉ የተለያዩ የቴክኖሎጂዎች ሙከራ ላይ ሴቶች ያላቸው ተሳትፎ አነስተኛ ነው፡፡

በዚህ ጥናት መረጃ የተሰበሰበው በ80 ሴቶች በተመራ እና በደንብ በተዋቀረ መጠይቅ ነው፡፡ ይህም የተካሄዴው በናይጄሪያ ደቡብ ጊኒ ሳቫና (ደ.ጊ.ሳ) አግሮ ኢኮሎጂካል ዞን  የእርሻ ላይ የድርቅ ተከላካይ (ድ.ተ) በቆሎ ዘር ላይ ነው፡፡

ጥናቱ ያሳየው ሁሉም ሴት ገበሬዎች ያገቡ እንደሆኑ ነው፤ ከእነዚህም 23% የሚሆኑት መደበኛ ትምህርት ያልተከታተሉ ሲሆኑ አማካይ እድሜያቸው ደግሞ 43 ዓመት ነው፡፡

በሁሉም ቦታዎች ሴት ገበሬዎቹ ድ.ተ የበቆሎ አይነትን በአንደኛ ደረጃ መርጠውታል፡፡

ስለዚህ ሴት ገበሬዎች በእርሻ ፈጠራዎች አሰራር እና ሙከራዎች ላይ መሳተፍ እንዳለባቸው ይመከራል፤ ይህም የምግብ ደህንነትን ለማረጋገጥ እና የእርሻ ምርትን በማሳደግ ዘላቂ አድገትን ለማምጣት ይረዳል፡፡


ድርቅ ተከላካይ በቆሎዎች በሚመረቱበት እና በሚሞከሩበት ጊዜ ሴት ገበሬዎች ይካተቱ

ብዙውን ጊዜ እርሻ  ነክ ውሳኔዎችን ከመውሰድ የሚገለሉት ከናይጄሪያ የመጡ ሴት ገበሬዎች የትኞቹን ድርቅ ተከላካይ (ድ.ተ) የበቆሎ ዘሮች ጥሩ ሆነው እንዳገኟቸው እና በዚህም ምክንያት እንዴት የበለጠ ትርፋማ መሆን እንደሚችሉ ለማረጋገጥ የተደረገ የእርሻ- ላይ ሙከራ ላይ ተሳትፈዋል፡፡

በናይጄሪያ ከ70% በላይ የሚሆኑትን ሰብሎች የሚያመርቱት አነስተኛ ይዞታ ያላቸው ገበሬዎች ናቸው፡፡

የማህበረሰቡን የምግብ ደህንነት ለማስጠበቅ ከፍተኛ ሚና ቢጫወቱም እንኳ የዚህ ቡድን 50% ያህል የሚሆኑት ሴት ገበሬዎች የግብርና ልማት ውሳኔዎች ላይ ብዙም አይሳተፉም እንዲሁም አይካተቱም፡፡

ድ.ተ በቆሎ በማንኛውም የድርቅ ወይም የደረቁ ጊዜዎች መብቀል ስለሚችል ሴት ገበሬዎች ድርቅ ተከላካይ (ድ.ተ) በቆሎ ማብቀል ከቻሉ ፍሬያማ የሰብል ምርት ሊያገኙ ይችላሉ፡፡

ስለዚህ ተመራማሪዎች የትኞቹ የድ.ተ ዝርያዎች በሴት ገበሬዎች  እንደሚመረጡ ለማወቅ የድ.ተ በቆሎን ለመምረጥ በተደረጉ የእርሻ ለይ ሙከራዎች አሳትፈዋቸዋል፡፡

ከ7 ከናይጄሪያ ደቡብ ጊኒ ሳቫና አግሮ ኢኮሎጂካል ዞን ለመጡ የሴት ገበሬ ቡድኖች 2 የበቆሎ ድ.ተ ዝርያዎች እና 1 መደበኛ የእርሻ ዝርያ ለማብቀል አነስተኛ መሬቶች ተስጥቷቸው ነበር፡፡

በጥቅሉ 80 ሴት ገበሬዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

ተመራማሪዎቹ እነዚህን መሬቶች አትክልቶቹ በማደግ ላይ እያሉ እና በድጋሚ ማበብ ሲጀምሩ የሰብል ምርቱን ለማሰስ ጎብኝተዋቸዋል፡፡

ተመራማሪዎቹ ከገበሬዎቹ እድሜ፣ የጋብቻ ሁኔታ እና የትምህርት ደረጃ ጋር የተያያዙ መረጃዎችን መጠይቆችን በመጠቀም ሰብስበዋል፤ እንዲሁም የእርሻ በጀቶችን እና ትርፎችንም ዳሰዋል፡፡

ሁሉም ያገቡ ሴት ገበሬዎች እድሚያቸው በአማካይ 43 ዓመት ሲሆን የድ.ተ ዝርያዎቹን ከመደበኛ ዝርያዎች አስበልጠው መርጠዋል፡፡

ሆኖም ግን በተለያዩ አካባቢዎች የተለያዩ የድ.ተ ዝርያዎች ተመራጭ ሆነዋል፡፡

ሴት ገበሬዎቹ የድ.ተ ዝርያዎችን የበለጠ ትርፋማ ሆነው አግኝተዋቸዋል፡፡

ተመራማሪዎች እና ገበሬዎች የድ.ተ በቆሎ የምግብ ደህንነትን ለማገዝ አስፈላጊ እንደሆነ ግንዛቤ ያላቸው ሲሆን ሴቶች የግብርና ምርትን እና የቤት ውስጥ የምግብ ደህንነትን ለማስጠበቅ ከፍተኛ ሚና ይጫወታሉ፡፡

ይህ ጥናት የድ.ተ ዝርያዎችን ለመፈተን በሚደረጉ የእርሻ ሙከራዎች ላይ ሴቶችን በማሳተፍ እነዚህን ሁለት ሃሳቦች አጣምሯል፡፡

ተመራማሪዎቹ እንደሚሉት ሴቶችን በግብርና ልማት እና ሙከራ ውስጥ የሚያካትቱ ፕሮግራሞች እና ፖሊሲዎች መተዋወቅ አለባቸው፤ ነገር ግን ይህንን ማስፈጸም የመንግስታት ሃላፊነት ነው፡፡

በቆሎ ከሰሃራ በታች አፍሪካ በጣም ወሳኙ እና በስፋት የሚበቅል  የምግብ ሰብል ነው፡፡

የአየር ንብረት መቀየር የምግብ ደህንነቱን አደጋ ላይ እየጣለው ሲሆን የድ.ተ በቆሎ መመረት ትርፋማ የምግብ ምርትን ለማስጠበቅ ወሳኝ ነገር ነው፡፡

በዚህ ጥናት ውስጥ የተሳተፉት ሁሉም ተመራማሪዎች ናይጄሪያ ላይ የተመሰረቱ ሲሆን ተሳታፊዎቹ ሴት ገበሬዎች እንዳለ ናይጄሪያዊ ነበሩ፡፡


Connections
1 of 5
Comments
0
comment
No comments here
Why not start the discussion?