Skip to main content
SearchLoginLogin or Signup

የወባ ትንኞች የወባ ጥገኛ ተውሳኮችን ወደ ሰዎች ማሰራጨቱን እየተካኑበት ሳይሄዱ አልቀሩም፡፡

Amharic translation of DOI: 10.1371/journal.pone.0230984

Published onAug 14, 2023
የወባ ትንኞች የወባ ጥገኛ ተውሳኮችን ወደ ሰዎች ማሰራጨቱን እየተካኑበት ሳይሄዱ አልቀሩም፡፡
·

ፓይሬትሮይድን በማብላላት ተጋትሮ ላይ በደም በላተኛው ዋና የአፍሪካ የወባ አስተላላፊ አኖፌሊስ ፈኒስተስ ላይ የGST- እና በP450 ላይ የተመሰረተ ተጽእኖ

ጸረ-ተባይ መድሃኒቶችን የሚቋቋሙ ጂኖች አብዛኛውን ጊዜ በተለያዩ የትንኝ የህይወት ታሪክ ባህሪያት ላይ ካላቸው ፕሊዮትሮፒክ  ተጽእኖ ጋር ይዛመዳሉ፡፡

ነገር ግን በትንኞች የደም አመጋገብ ስርአት ውስጥ የጸረ-ተባይ መድሃኒቶች ተጋትሮ ስላለው ተጽእኖ  የተገኘው መረጃ እጅግ አነስተኛ ነው ፡፡

እዚህ ጋር ሁለት በዋናው የወባ አስተላላፊ  አ.ኖ ፊኒስተስ ውስጥ በቅርቡ የተገኙ ዲኤንኤ-መር የማብላላት አመላካቾችን በመጠቀም፣የማብላላት ተጋትሮ ያላቸው ጂኖች እንዴት የደም ምግብ ፍጆታ ላይ ተጽእኖ እንደሚያሳድሩ መርምረናል፡፡

ሁለቱንም የፊልድ F1 እና የላብራቶሪ F8 የአኖፌሊስ ፈኒስተስ ዝርያዎች በሰው ክንድ ላይ ለ30 ደቂቃ እንዲመገቡ ከፈቀድን በኋላ ፣የደም አመጋገብ ሂደት ቁልፍ መለኪያዎችን ማለትም፣የመመርመሪያ ጊዜ፣የአመጋገብ ቆይታ ፣የደም አመጋገብ ስኬታማነት፣የደም ምግብ መጠን፣እና የግሉታቲዮን ኤስ-ትራንስፈሬዝ አመላካቾችን (L119F-GSTe2) እና በሳይቶክሮም P450 (CYP6P9a_R) የተቀናጀ የማብላላት ተጋትሮ መካከል ያለውን  ዝምድና ገምግመናል፡፡

የትንኞቹም የደም አመጋገብ ሂደት መለኪያዎች ከ L119F-GSTe2  የጂን አወቃቀር ጋር አልተያያዙም ነበር፡፡

በአንጻሩ ለሆሞዛይጎስ ተጋላጭ (OR= 3.3; CI 95%: 1.4–7.7፤ P = 0.01) ከሆኑት ትንኞች ይልቅ የCYP6P9a_R ሆሞዛይጎስ ተቋቋሚ ትንኞች በእጅጉ የበለጠ የደም-ምግብ መመገብ ችለዋል ፡፡

በተጨማሪም በ CYP6P9a-SS ትንኞች የተወሰደው የደም መጠን ከCYP6P9a-RS (P<0.004) እና ከCYP6P9a-RR (P<0.006) ይልቅ ያነሰ ነበር፡

ይህ CYP6P9a ጂን ከአ.ኖ ፈኒስተስ የአመጋገብ ስኬት እና ከደም ምግብ መጠን ጋር እንደሚያያዝ ያሳያል፡፡

ይሁን እንጂ በ CYP6P9a መገለጫ እና የደም ምግቡ ስርአት ውስጥ ተሳታፊ በሆኑት በምራቅ ውስጥ ባሉ ፕሮቲኖች የጂን ኮድ አደራረግ ጋር ምንም አይነት ዝምድና አልተገኘም፡፡

ይህ ጥናት በ P450- ላይ የተመሰረተ የማብላላት ተጋትሮ በአኖፌሊስ ፈኒስተስ የወባ ትንኝ የደም አመጋገብ ሂደት እና፣የወባ ጥገኛ ተህዋስያንን በማስተላለፍ ችሎታው ላይ ተጽእኖ ሳይኖረው እንደማይቀር ያመለክታል፡፡


የወባ ትንኞች የወባ ጥገኛ ተውሳኮችን ወደ ሰዎች ማሰራጨቱን እየተካኑበት ሳይሄዱ አልቀሩም፡፡

አንዳንድ የወባ ትንኞች እነሱን ለመግደል የታሰቡትን ጎጂ ኬሚካሎች (ጸረ-ተባይ መድሃኒቶችን) መቋቋም ተለማምደዋል፡፡

ተመራማሪዎቹ በአኖፌሊስ ፈኒስተስ ትንኞች ውስጥ የሚገኙት ይህን የጸረ-ተባይ መድሃኒት ተጋትሮ የሚያመጡት የጄኔቲክ ለውጦች፣ የሰዎችን ደም በበለጠ እንዲመገቡ ሳያስችላቸው አልቀረም ይላሉ፡፡

ይህ በምላሹ ወባን የማሰራጨት አቅማቸውን ሊጨምረው ይችላል፡፡

አንዳንድ የወባ ትንኞች እነዚህን ኬሜካሎች በሰውነታቸው ውስጥ በተሻለ ሁኔታ በማብላላት ወይም በመፍጨት የጸረ-ተባይ መድሃኒቶቹን ገዳይ ጉልበት መቋቋም ይችላሉ፡፡

ይህ አይነቱ ጸረ-ተባይ መድሃኒቶችን የመቋቋም ችሎታ በጄኔቲክ መላመዶች የሚመራ ነው፤ነገር ግን በእነዚሁ ተመሳሳይ የጄኔቲክ መላመዶች ምክንያት ትንኞቹ ያገኙት ሌላ ምን ጥቅም እንዳለ ብዙም የታወቀ ነገር የለም፡፡

በዚህ ጥናት ተመራማሪዎቹ ከዚህ ጸረ-ተባይ መድሃኒቶችን በማብላላት ከሚመጣ ተጋትሮ ጀርባ ያሉት ጂኖች የአመጋገብ ሂደታቸውንም አሻሽለው እነደሆነ ማወቅ ይፈልጋሉ፡፡

ለምሳሌ እነዚህ የመቋቋም ችሎታ ያላቸው ትንኞች በምግብ መመገቢያቸው ጊዜ  በፍጥነት መመገብ እና ተጨማሪ ብዙ ደም መውሰድ ይችሉ እንደሆነ ለማወቅ ፈልገው ነበር፡፡

ተመራማሪዎቹ ሁለት የተለያዩ የአኖፌሊስ ፈኒስተስ ትንኝ አይነቶች በሰው ክንድ ላይ ለ30 ደቂቃ እንዴት እንደሚመገቡ አስተውለዋል፡፡

የደም ምግብ ሂደቶቹን ገጽታ ማለትም ትንኞቹ ለምን ያህል ጊዜ እንደተመገቡ እና ምን ያህል ደም እንደመጠጡ ለክተዋል፡፡

በተጨማሪም ልዩ የአመጋገብ ባህሪ የጸረ-ተባይ መድሃኒቶች ተጋትሮን ከሚያረጋግጡ ከሁለት ልዩ ጄኔቲካዊ ቅይርታዎች ጋር ይገናኝ እንደሆነ ለማየት  የትንኞቹን ስነ ባህሪይ ገምግመዋል፡፡

ውጤቶቻቸው እንደሚያሳዩት ከተከላካይ ጂኖች አንዱ የአመጋገብ ባህሪ ላይ ተጽእኖ ያሳድራል፡፡

ይህ የተለየ የጂን ቅይርታ ያላቸው ትንኞች የሰውነት ክብደታቸው ዝቅተኛ ሲሆን ከሌሎች ምንም ከሌላቸው ጋር ሲነጻጸሩ ብዙ ደም መመገብ ችለዋል፡፡

ይሁን እንጂ የጂን ቅይርታ የአመጋገብን ጊዜ የሚቀይር አይመስልም፤ እንዲሁም ትንኝ ደም ለመመገብ የሚጠቀምባቸውን የአንዳንድ ፕሮቲኖች ደረጃ ከፍ ወይም ዝቅ ሊያደረግ አይችልም፡፡

ይህ ጥናት የጸረ-ተባይ መድሃኒቶች ተጋትሮን ያመጡት የጂን ቅይርታዎች ሌሎች የመላመድ ባህሪያትን ሊያስከትሉ እንደሚችሉ ማስረጃ ያቀርባል፡፡

በዚህኛው አጋጣሚ ተመራማሪዎቹ ተመሳሳይ ጂን በወባ ትንኝ አመጋገብ ባህሪ ላይ ተጽእኖ ሊያሳድር  እንደሚችል አረጋግጠዋል፡፡

ይህ አስፈላጊ ነው ምክንያቱም ትንኞች በሚመገቡበት ጊዜ የወባ ጥገኛ ተውሳኮችን ወደ ሰዎች ያስተላልፋሉ፡፡

ተመራማሪዎቹ እንደሚሉት ወደፊት የሚደረጉ ጥናቶች እነዚህ ጂኖች የአመጋገብ ባህሪ ላይ እንዴት ተጽእኖ እንደሚያደርሱ እና በትንኞች የስሪያ እና ወባን የማሰራጨት መንገድ ላይ እንዴት ተጽእኖ እንደሚያሳድሩ ሊዳስሱ ይገባል፡፡

በጥናታቸው የተደረጉት አንዳንዶቹ ሙከራዎች ስኬታማ እንዳልነበሩ እና በውጤታቸው ላይም ተጽእኖ እንዳሳደሩ ያሳስባሉ፡፡

እነሱን ለመቆጣጠር በምናደርገው እንደ ጸረ-ተባይ መድሃኒቶችን በስፋት እና በተደጋጋሚ የመጠቀም ጥረት፣የትንኞች የጄኔቲክ እና የባህሪ ለውጥ እንዴት ምላሽ እንደሚሰጥ መረዳት አስፈላጊ ነው፡፡

የዚህጥናትአዘጋጆችመቀመጫቸውካሜሩንሲሆንለዚህምርምርጥቂትትንኞችንለናሙናነትከዚያውተጠቅመዋል፡፡

Connections
1 of 5
Comments
0
comment
No comments here
Why not start the discussion?