Description
Lay summary of the article published under the DOI: 10.1101/2020.05.28.121301
This is Amharic translation of DOI: 10.1101/2020.05.28.121301
ዓላማ:
በ ሪ.አ ታማሚዎች የስረአተ ልብ ወቧንቧ ክስተቶች በስርዓተ እብጠት ምክንያት በላተመጣጠነ መልኩ ጨምረዋል፡፡
ተያያዥ አውቶኢሚዩን ሲትሩሊኔሽን በዘህ (ኦጀን) አወቃቀር እና በደም ስር ውስጥ ደም የማርጋት አቅም ላይ ያለው አንጻራዊ ተጽእኖ እስካሁን አይታወቅም፡፡
ስለዚህ ከመረጃ ጠቋሚ ዝርዝሮች ውስጥ የሪ.አ ታማሚዎች የደም ቧንቧ ተግባራትን፣ እብጠትን፣ የደም መርጋትን እና የዘህ የደም መርጋት ቅንብርን ከጤነኛ የቁጥጥር ናሙናዎች ጋር አወዳድረናል፡፡ የእርስ በእርስ መለኪያ ግንኙነቶችንም መርምረናል፡፡
ስልቶች፡፡
የደም ናሙናዎች ከ30 የ ሪ.አ ታማሚዎች እና ከ 25 እድሜ እና ጾታቸው ከሚጣጣሙ ጤነኛ በጎ ፍቃደኞች ተሰብስበዋል፡፡
የ SAA፣ CRP፣ ICAM-1 እና VCAM-1ደረጃዎች የሳንድዊች የበሽታ መከላከያ ምርመራን በመጠቀም ተለክተዋል፡፡
ሙሉ የደም መርጋት ትሮምቦላስቶግራፊን በመጠቀም ተገምግሟል፡፡
የዘህ የደም መርጋት መረቦች እና የድር መዋቅር በቃኚ የኤሌክትሮን ማይክሮስኮፒ ተመርምረዋል፡፡
በተከሰቱት የዘህ ደም መርጋቶች ሲትሩሊኔሽንን መለየት እና መጠናቸውን ማወቅ የተከናወነው በፍሎረሰንት ምልክት በተደረገበት የሲትሩሊን ሞኖክሎኒክ አንቲቦዲ በኮንፎካል ማይክሮስኮፒ ነው፡፡
ውጤቶች፡፡
ከቁጥጥር ቡድኖቹ ጋር ሲነጻጸር በ ሪ.አ ታማሚዎች ውስጥ ያሉት የSAA፣ CRP እና ICAM-1ስብስቦች በከፍተኛ ሁኔታ ጨምረዋል፡፡
ከደም መርጋት አጀማመር (R እና K) ጋር የሚዛመዱ የ TEG መለኪያዎች፣ የዘህ አገናኝ ፍጥነት (α-አንግል) እና ከፍተኛ ርጉ ደም ለማመንጨት የሚፈጀው ጊዜ (TMRTG) በ ሪ.አ ታማሚዎች ላይ ተዳክሟል፡፡
በቁጥጥር ቡድኖቹ እና በ ሪ.አ መሃል ያሉ ከደም መርጋት ጥንካሬ ጋር የሚያያዙ መለኪያዎች (MA፣ MRTG፣ TGG) በስታትስቲክስ አይለያዩም፡፡
የሎጅስቲክስ ሪግሬሽን ሞዴሊንግ አጣዳፊ ደረጃ ምላሽ ሰጪዎች (CRP፣ SAA) ከኢንዶቴሊያል ተግባር አመልካቾች ይልቅ ከ TEG መለኪያዎች ጋር ጠንካራ ግንኙነት እንዳላቸው ገልጧል፡፡
የአጉሊ መነጽር ትንታኔ እንደገለጸው፣ ከቁጥጥር ቡድኖች ጋር ሲነጻጸር የ ሪ.አ ታማሚዎች ጥቅጥቅ ያሉ የዘህ ድር መረቦች አሏቸው፡፡ [[[[ሜዲያን (መካከለኛ ክልል) በnm ቅደም ተከተል 214 (170-285) ከ 120 (100-144) ጋር ሲነጻጸር፣ p<0.0001፣ አንጻራዊ ይሆንታ ውድር=22.7)
በቁጥጥር ቡድን ናሙናዎች ላይ ብዙም ያልተስፋፉት (p<0.05, OR=2.2) በ ሪ.አ ታማሚዎች የዘህ የደም መርጋት መዋቅር ውስጥ የሚገኙ ብዙ የሲትሪሉኔትድ ክልሎችን መለየት ፡፡
መደምደሚያ፡፡
ከሌሎች የእብጠት ክስተቶች ጋር ከሚገናኙ አጠቃላይ ግኝቶች፣ ንቁ ሪ.አ ያላቸው ታማሚዎች ከሌሎች ጋር የማይመሳሰል የደም መርጋት መገለጫ አሳይተዋል፡፡
ከአውቶኢሚዩን ጋር በሚዛመድ ሲትሩሊኔሽን የፕሮቲን መዋቅሮች ላይ የሚከሰተው ለውጥ፣ በ ሪ.አ ታማሚዎች ላይ የዘህ አወቀቀርን ለመወሰን እና በደም ስር ውስጥ ደም የመርጋት አደጋን ለመጨመር ሚና ይጫወታል፡፡
በሪዩማይቶይድ አንጓ ብግነት ዙሪያ የተደረገው አዲስ ምርምር ይሀ ሁኔታ ከከፍተኛ የስርአተ ልብ ወቧንቧ በሽታ አደጋ ጋር ስላለው ግንኙነት የተሻለ ግንዛቤ ሰጥቷል፡፡
ሪዩማይቶይድ አንጓ ብግነት (ሪ.አ) የሚያሰቃይ እና የሚያስፈራ የአውቶኢሚዩን ክስተት ሲሆን፣ በመጋጠሚያዎች እና በመላ ሰውነት ውስጥ ከሚከሰት እብጠት ጋር ይያያዛል፡፡
ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ ሳይንቲስቶች የበሽታው ተጠቂዎች ለከፍተኛ የስርአተ ልብ ወቧንቧ በሽታ (ስ.ል.ቧ.በ) ውጤቶች ለሆኑት ስትሮክ እና ልብ ድካም በ50% ከፍ ያለ ተጋላጭነት እንዳላቸው ተገንዝበዋል፡፡
ለዚህ አደጋ ዋነኛው ምክንያት እብጠት በደም መርጋት ሂደት ውስጥ ያለው ተጽእኖ ነው፡፡
በዚህ ጥናት ተመራማሪዎች ሪ.አ ለምን የስ.ል.ቧ.በ አደጋን እንደሚጨምረው በትክክል ለማወቅ ይህንን ግንኙነት መርምረዋል፡፡
በተለይም ተመራማሪዎቹ የእብጠት እና የመዋቅራዊ ለውጦች ከደም መርጋት ጋር የሚያያዙት እና ዘህ የሚባሉትን ልዩ ፕሮቲኖች ላይ ያላቸውን ተጽእኖ መርምረዋል፡፡
እነዚህ ፕሮቲኖች የሚከሰቱት በደም መርጋት ውስጥ መሰረታዊ የ “ፍርግርግ-ስራውን” የሚሰሩት ረጅም ሰንሰለቶች ላይ ሲሆን፣ በዘሆቹ ላይ የሚከሰቱት ለውጦች በአጠቃላይ የደም መርጋቱ ሂደት ውስጠ ቀጥተኛ ያልሆኑ ድምር ተጽእኖዎች ሊኖራቸው ይችላል፡፡
ተመራማሪዎቹ ከሪ.አ በሽተኞች የተወሰዱ የደም ናሙናዎችን ከጤነኛ ግለሰቦች ከተወሰዱ ናሙናዎች ጋር አወዳድረዋል፡፡
በእያንዳንዱ ሁኔታ ተመራማሪዎቹ እብጠት በሚያሳይ ደም ውስጥ ያሉ “መለያዎችን” እየፈለጉ ነበር፡፡ በተጨማሪም፣ የስ.ል.ቧ.በ አደጋን ሊጨምሩ የሚችሉ የተለመደው የመርጋት ሂደት ውስጥ የሚከሰቱ ያልተለመዱ ልዩነቶችን አይተዋል፡፡
በዘህ ፕሮቲናቸው ላይ የተከሰተቱን ለውጦች ለማወቅ የደምርጋታዎቹ እራሳቸው ላይ የአጉሊ መነጽር ትንተና ተደርጎባቸዋል፡፡
ተመራማሪዎቹ የ ሪ.አ ታማሚዎች ላይ ያሉ የደምርጋታዎች ከጤነኛ ሰዎች ጋር ሲነጻጻሩ በፍጥነት እንደሚከሰቱ አስተውለዋል፡፡ በተጨማሪም የሚሰሩባቸው የፕሮቲን ክሮች ከተለመዱት ዘሆች ጉልህ በሆነ መልኩ ይወፍራሉ፡፡
የዘህ ፕሮቲኖቹን የሚሰሯቸው አሚኖ አሲዶች ላይ ለውጥ የነበረ ሲሆን ይህም የሰውነት በሽታ የመከላከል ምላሽን ስላነሳሳው ተጨማሪ እብጠት እንዲከሰት አድርጓል፡፡
ሌሎች ተመራማሪዎች ከዛሬ በፊት የሪ.አ ታማሚዎች መጋጠሚያ ውስጥ ያሉ የአሚኖ አሲድ መዋቅሮች ላይ ለውጦችን አስተውለዋል፡፡ ነገር ግን ተመራማሪዎች በደም ውስጥ ተመሳሳይ ተጽእኖ ያገኙት ለመጀመሪያ ጊዜ ነው፡፡
ግኝቶቹ በደም እርጋት ውስጥ ከሚታዩት ሌሎች ለውጦች ጋር አንድላይ በመሆን፣ ሳይንቲስቶች በ ሪ.አ እና በስ.ል.ቧ.በ መካከል ስላለው ግንኙነት እና እንዴት የእነዚህን በሽታዎች መነሻ ምልክቶች መለየት እንደሚቻል ጥልቅ ግንዛቤ እንዲያዳብሩ ሊረዷቸው ይችላሉ፡፡
ምንም እንኳ እነዚህ ጅማሪ ግኝቶች ተስፋ ሰጪ ቢሆኑም፣ ለጥናቱ የተወሰደው ናሙና በአንጻራዊ ሁኔታ ሲታይ አነስተኛ እንደነበር ልብ ሊባል ይገባል፡፡
ተመራማሪዎቹ በተጨማሪ፣ የአሚኖ አሲድ ለውጦችን በፕሮቲን ውስጥ ለማየት የተጠቀሙት ዘዴ ሌሎች ተዛማችነት የሌላቸው ንጥረ ነገሮች ውጤት ሊያነሱ እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡ ይህ ማለት ውጤቱን ወደፊት ለማረጋገጥ ዘሆች ላይ ያነጣጠሩ ልዩ ሙከራዎችን ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
እነዚህን በሽታዎች ይበለጥ ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመለየት እና ለማከም መማር እና በ ሪ.አ እና በጨመረው የ ስ.ል.ቧ.በ አደጋ መሃል ያለውን ውስብስብ ግንኙነት መረዳት፣ በረጅም ጊዜ ለ ሪ.አ ታማሚዎች የተሻለ ውጤትን ሊያስገኝ ይችላል፡፡
በደቡብ አፍሪካ የህክምና ምርምር ካውንስል የገንዘብ ድጋፍ በተደረገለት በዚህ ጥናት ላይ የደቡብ አፍሪካ፣ የዴንማርክ እና የዩናይትድ ኪንግደም ተመራማሪዎች ተሳትፈዋል፡፡
This is a Yoruba translation of DOI: 10.1101/2020.05.28.121301
This is Zulu translation of DOI: 10.1101/2020.05.28.121301
This is Northern Sotho translation of DOI: 10.1101/2020.05.28.121301
This is Hausa translation of DOI: 10.1101/2020.05.28.121301
This is a Luganda translation of DOI: 10.1101/2020.05.28.121301