Description
This is a lay summary of the article published under the DOI: 10.1007/978-3-319-92798-5_5
Amharic translation of DOI: 10.1007/978-3-319-92798-5_5
ምንም እንኳ የአየር ንብረት ለውጥ በዚምባቡዌ ሰፊ የተለያዩ ዘርፎች ላይ ተጽእኖ ሊያሳድር ቢችልም፣የሃገሪቱ የኢኮኖሚ መሰረት እንደመሆኑ፣በግብርናው በኩል ያለው አደጋ በጣም የጎላ ነው፡፡
በተጨማሪም፣ለእነዚህ አደጋዎች እንዴት ምላሽ መስጠት እንደሚችሉ ፣የአነስተኛ ገበሬዎችን የእርሻ ዘዴ እና መተዳደርያን ስለማገዝ ያለው መረጃ አነስተኛ ነው፡፡
በሰብል ምርት ላይ፣የሚጠበቁ የዝናብ ስርአቶች (ቅጦች) መቀያየርን፣በካርቦን ዳይኦክሳይድ (ካ.ዳ) የታቀደ ጭማሪ እና የሙቀት መጠን ተጽእኖዎችን ለመወሰን፣የውሳኔ ድጋፍ ስርአት ለአግሮ ቴክኖሎጂ ቅብብል/ሽግግር (DSSAT) እና የግብርና ምርት ስርአት አስመሳይ ሞዴል (APSIM)የተባሉ፣ሁለት ሂደት ላይ የተመሰረቱ የእህል ሞዴሎች ተጠቅመናል፡፡
ሞዴሎቹ፣ ነጠላ እና ጥምር የአየር ንብረት ተጽእኖዎችን፤በበቆሎ እና በለውዝ የእህል እና የገለባ ምርት አፈጻጸም በሶስት የአፈር አይነቶች ላይ ለመገምገም የተወጠኑ እና የተረጋገጠላቸው ናቸው፡፡
ሁለቱ ሞዴሎች ባጠቃላይ የተለያዩ የአየር ንብረት ሁኔታዎች በሁለቱም በበቆሎ እና በለውዝ ላይ ባላቸው ተጽእኖ ቢስማሙም፣ የተጽእኖው መጠን ግን ይለያያል፡፡
ለምሳሌ፣ የበቆሎ እህል ምርት መቀነስ በ (APSIM) ሞዴል የበለጠ ጉልህ ሆኖ ሲታይ በ (DSSAT) ሞዴል ደግሞ የበቆሎ ገለባ ምርት መቀነስ ጎልቶ ይታያል፡፡
ሁለቱም ሞዴሎች ፣የጥምር አየር ንብረት የተጽእኖ ምክንያቶችን ሲገመገሙ፣ ለውዝ ከፍ ባለ የካርቦን ዳይኦክሳይድ (ካ.ዳ) ክምችት ስር ምርታማነትን በማሳየት የሙቀት መጨመር ተጽእኖዎችን እንደተቃረነ አሳይተዋል፡፡
ሆኖም ግን በDSSAT ሞዴል፣ ለሁለቱም ለለውዝ እህል እና ገለባ ፣ የምርት መጨመሮች የበለጠ ጉልህ ናቸው፡፡
ቁልፉ ግኝት አፈሮች በሰብል-አየር ንብረት መስተጋብር ላይ አስፈላጊ ሚና እንደሚጫወቱ ሲሆን፡ የአየር ንብረት ተጽእኖዎችን ሊቀንሱ ወይም ሊያባብሱ ይችላሉ፡፡
ይህ ጥናት፣ በዚምባብዌ የሰብል ምርት ላይ የአየር ንብረት ተጽእኖን አስመስሎ ተሰርቷል፡፡ እናም፣ የሙቀት መጠን ለውጦች፣ ዝናብ፣እና ካርቦን ዳይኦክሳይድ በምርት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እንዳላቸው አግኝቷል፡፡
ሆኖም ግን፣የሰብል ምርቶችን ለመጠበቅ በተሻሻለ የአፈር ጥራት ላይ ማተኮር፣ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽእኖን ያስታግሳል፡፡
የአየር ንብረት ለውጥ፣የሃገሪቱ የኢኮኖሚ መሰረት በሆነው በዚምባቡዌ የግብርና ዘርፍ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ማሳደሩ አይቀሬ ነው፤ ነገር ግን አነስተኛ ገበሬዎች ለአደጋዎቹ ምላሽ መስጠት እንዲችሉ የሚረዳ የመረጃ እጥረት አለ፡፡
የአየር ንብረት ለውጥ፣ የአዘናነብን ስርአት የመቀየር እና የሚገኘውን የካርቦን ዳይኦክሳይድ መጠን የመለወጥ አቅም አለው፤ ስለዚህም የሰብል ምርት ላይ ተጽእኖ ያሳድራል፡፡
ግን የነዚህ ለውጦች ትክክለኛ ተጽእኖዎች በዚምባቡዌ በሚገባ አልተጠኑም፡፡
ስለዚህ ይህ ጥናት፣ የዝናብ ለውጥ ፣የካርቦን ዳይኦክሳይድ (ካ.ዳ) መጨመር እና በአየር ንብረት የሚጠበቁ ለውጦች፣ በሰብል ምርት ላይ ያላቸውን ተጽእኖዎች ሁለት የሂሳብ ሞዴሎችን በመጠቀም ተመልክቷል፡፡ተመራማሪዎቹ በዚምባቡዌ ኒካይ ክልል ውስ
ጥ ፣ነጠላ እና ጥምር የአየር ንብረት ለውጥ ምክንያቶች በለውዝ እና በበቆሎ ምርታማነት ላይ ያላቸውን ተጽእኖ ለመወሰን ሁለቱን ሞዴሎች ተጠቅመዋል፡፡
እንደ ውሃ ኡደት እና ናይትሮጅን ኡደት የመሰሉ የተለያዩ የአፈር ሂደቶችን ሚና ለማወቅ እና ሰብሉ ቀኑን ሙሉ ሊፈራረቅበት ስለሚችለው ከፍተኛ እና ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ጨምሮ የተለያዩ ወቅቶችን ለማስመሰል ሞዴሎቹን ተጠቅመውባቸዋል፤
ተመራማሪዎቹ የአየር ንብረት ለውጥ፣ በበቆሎ እና በለውዝ ጥራጥሬዎች፣እንዲሁም ብዙውን ጊዜ በአጨዳው ወቅት በመስኩ ላይ በሚቀሩት(ገለባ) በሚባሉት ግንድ እና ቅጠሎች ላይ ያለውን ተጽእኖ ለመመርመር ሞዴሎቹን ተጠቅመውባቸዋል፡፡
ሁለቱ ሞዴሎች፣ የተለያዩ የአየር ንብረት ምክንያቶች በበቆሎ እና በለውዝ ላይ ባላቸው ተጽእኖዎች ላይ ቢስማሙም፣ የተጽእኖው መጠን ግን መለያየቱን ጥናቱ ደርሶበታል፡፡
የAPSIM ሞዴል የበቆሎ አህል ምርቶች ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር መቀነሳቸውን ሲያሳይ፣የDSSAT ሞዴል ደግሞ የበቆሎ ገለባ ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር በእጅጉ መቀነሱን አመልክቷል፡፡
ሁለቱም ሞዴሎች የለውዝ ምርት፣በከፍተኛ የካርቦን ዳይኦክሳይድ(ካ.ዳ) ደረጃዎች መጨመሩን አሳይተዋል:: ነገር ግን የDSSAT ሞዴል እንዳሳየው፣ የለውዝ እህል እና ገለባ ሁለቱም በከፍተኛ ሙቀት እና ከፍተኛ የካርቦን ዳይኦክሳይድ (ካ.ዳ) ደረጃዎች የተሻለ ተስማሚ ምርት ያስገኛሉ፡፡
ተመራማሪዎቹ፣ ሰብሉ ከሚለዋወጠው ዝናብ እና ሙቀት ጋር እንዴት መላመድ እንደሚችል ለመወሰን፣ አፈሩ የሚጫወተው ሚና አስፈላጊ እንደሆነ አግኝተዋል፡፡
ውጤቶቹ፣ ጥራት ያለው አፈር የአየር ንብረት ለውጥ በሰብል ምርት ላይ ያለውን ተጽእኖ ለመቀነስ ቁልፍ መሆኑን አሳይተዋል፡፡
ተመራማሪዎቹ ፣ ገበሬዎች እና የአፍሪካ መንግስታት ራሳቸውን ከአየር ንብረት ለውጥ ተጽእኖ ለመጠበቅ፣ አፈራቸውን በማሻሻል ላይ ማተኮር እንደሚገባቸው ይመክራሉ፡፡
Northern Sotho translation of DOI:10.1007/978-3-319-92798-5_5
Luganda translation of DOI: 10.1007/978-3-319-92798-5_5
Yoruba translation of DOI:10.1007/978-3-319-92798-5_5
Hausa translation of DOI: 10.1007/978-3-319-92798-5_5
Zulu translation of DOI: