Description
This is a lay summary of the article published under the DOI:
Amharic translation of DOI:
ኢቦላ ቫይረስ (ኢቦ.ቫ) በሽታ በአለም ዞሪያ እውቅና የጋኘ የጤና አደጋ ሲሆን በምእራብ ኢኳቶሪያል አፍሪካ የሚገኝ አካበሽታ ነው፡፡
ኤፒዲሚዮሎጂውን በተለይም የኢቦ.ቫ በሽታን ተለዋዋጭ ንድፍ ለመረዳት እ.ኢ.አ በ2018 እና 2019 ዓ.ም መካከል በዲሞክራቲክ ሪፓብሊክ ኮንጎ (ዲ.ሪ.ኮ) አሁንም እየቀጠለ ባለው ወረርሽኝ በበሽታው እንደተያዙ የታወቁ ሰዎችን እና የህይወት እልፈት ዘገባዎችን ለመተንተን የኢቦ.ቪ ክስተት አመልካች መረጃን እንጠቀማለን፡፡
በስቶቻስቲክ ከፊል የልዩነት እኩልታዎች (ስ.ከ.ል.እ) በመጠቀም ሙሉ በሙሉ የባዬሲያን ጂኦ-ስታትስቲካል ትንተና ማድረግ በእያንዳንዱ የቦታ ጎራ የቦታ ንድፎችን ቁጥር ለይተን እንድናውቅ ይረዳናል፡፡
በተቀናጀ ድርብርብ ላፕላስ ቅርቦሽ (ተ.ድ.ላ.ቅ) ላይ የተመሰረት የመመጠኛ ግምት፡፡
ግኝቶቻችን እንደሚገልጹት በተዘገቡት የኢቦ.ቪ ክስተቶች ፣የህይወት እልፈቶች እና በተጠቁት አካባቢዎች ላይ በነበሩ የብጥብጥ ክስተቶች መካከል ግንኙነት አለ፡፡ በተጨማሪ በሁለቱም አጋጣሚዎች እና የህይወት እልፈቶች ስብስቦች የነበሩ ሲሆን ወደአጎራባች ቦታዎች በተመሳሳይ ሁኔታ ተሰራጭተዋል፡፡
ስለዚህ የጥናቱ ግኝቶች ለበሽታ ምቹ የሆኑ ቦታዎችን ለመለየት እና ቦታ ተኮር የበሽታ ክትትል ለማድረግ እና እርምጃ ለመውሰድ ይጠቅማሉ፡፡
እ.ኢ.አ በ2018 ዓ.ም ዲሞክራቲክ ሪፓብሊክ ኮንጎ (ዲ.ሪ.ኮ) በ40 አመት ውስጥ አስረኛ የኢቦላ ወረርሽኙን አረጋግጧል፡፡
ወረርሽኙ በሃገሩ ትልቁ የኢቦላ ክስተት ሲሆን ከምእራብ አፍሪካ እ.ኢ.አ ከ2014 እስከ 2016 ዓ.ም ወረርሽኝ በመቀጠል ሁለተኛውን ደረጃ ይይዛል፡፡
የአሁኑ ወረርሽኝ ለረጅም ጊዜ በዘለቀው የግጭት ቀጣና ውስጥ እየተከሰተ እንዳለ ተዘግቧል፡፡ ይህ ጥናትም ያተኮረው በዲ.ሪ.ኮ የኢቦላ ክስተት የቦታ ስርጭት እና የብጥብጥ ክስተቶች ስላቸው ተጽእኖ መመርመር ላይ ነው፡፡
በበሽታ በተጠቁት አካባቢዎች ላይ የተከሰቱ ብጥብጦች ከተዘገቡት የኢቦላ በሽታ ክስተቶች ጋር በእጅጉ የተያያዙ እንደሆኑ ተገኝቷል፤ ይህም ለበሽታ ምቹ የሆኑ ቦታዎችን ለመለየት እና ቦታ ተኮር የበሽታ ክትትል ለማድረግ እና እርምጃ ለመውሰድ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡
በዲሞክራቲክ ሪፓብሊክ ኮንጎ ብጥብጥ የኢቦላ ወረርሽኝ ክስተትን ይተነብያል፡፡
ኢቦላ ቫይረስ በሽታ (ኢቦ.ቫ) በጣም አደገኛ እና ተላላፊ በሽታ ሲሆን በዲሞክራቲክ ሪፓብሊክ ኮንጎ (ዲ.ሪ.ኮ) እየተካሄደ ባለው ብጥብጥ ምክንያት እየተባባሰ መጥቷል፡፡
አሁን ላይ ተመራማሪዎች የጥቃት ክስተት መረጃዎችን ተጠቅመው የ ዲ.ሪ.ኮ ወረርሽኞች የት እንደሚከሰቱ መተንበይ ችለዋል፡፡
ኢቦላ በምእራብ እና በአፍሪካ ኢኳቶሪያል ክልሎች የሚገኝ አካበሽታ ሲሆን በአለም ዙሪያ ህዝባዊ የጤና ድንገተኛ አደጋ ተደርጎ ይቆጠራል፡፡
በቅርብ ጊዜ በ ዲ.ሪ.ኮ የተከሰተው ወረርሽኝ በምእራብ አፍሪካ እስከዛሬ ከተመዘገቡ ክስተቶች በሁለተኛ ደረጃ ትልቁ ነው፡፡
በዚህ ሃገር የትጥቅ ግጭቶች ለተላላፊ በሽታዎች መከሰት እና መስፋፋት አመቺ ሁኔታን ይፈጥራሉ፤ ይህም የሚሆነው የተፈጥሮ ሃብት እና የጤና መሰረተ ልማቶች ስለሚደመሰሱ እና ሰዎች ስለሚፈናቀሉ ነው፡፡
በዚህ ጥናት ተመራማሪዎች በዲ.ሪ.ኮ እ.ኢ.አ በ2018 እና 2019 ዓ.ም ግጭት በተዘገበባቸው ቦታዎች በኢቦላ በሽታ መስፋፋት እና በጂኦግራፊያዊ ቦታዎች መሃል ስላለው ግንኙነት ፈትሸዋል፡፡
በቤይስ ቲዎሪ ላይ ያተኮሩ የስታስተኪስ ዘዴዎች ላይ ተመስርቶ ሌላ ክስተት መቼ እና የት እንደሚፈጠር ለመተንበይ የተበታኑ መረጃዎችን ይጠቀማል፡፡
ኢቦላ ቀጥሎ የት እንደሚከሰት ለመተንበይ በተወሰኑ አካባቢዎች የተነሱ ብጥብጦች ላይ የሚያተኩሩ መረጃዎችን ተጠቅመዋል፡፡
ጥናቱ እንዳገኘው በብጥብጥ ክስተቶች የተጎዱ አካባቢዎች ከተዘገቡ የኢቦላ ኢንፌክሽኖች እና የህይወት እልፈቶች ጋር ተያይዘው ነበር፣ ወደ ጎረቤት ሃገሮችም ተዛምተዋል፡፡
አሁንም እየቀጠለ ባለው ብጥብጥ ምክንያት ተመራማሪዎቹ መረጃ ያልተሰበሰባባቸው የኢቦላ ክስተቶች እና የህይወት እልፈቶችንም ቆጥረዋል፡፡
ለመጀመሪያ ጊዜ ይህ ጥናት እንዳሳየው በዲ.ሪ.ኮ የባዬሲያን የቦታ ሞዴሊንግ መረጃ ሊጠፋ የሚችልባቸውን እና ለኢቦላ መዛመት ምቹ የሆኑ ቦታዎችን ለመለየት ይጠቅማል፡፡
ነገር ግን ተመራመሪዎቹ የብጥብጥ ክስተት አይነቶችን እና እንዴት በተለየ ሁኔታ የጤና አጠባበቅ ስርአቱ ላይ ተጽእኖ እንደሚያደርጉ ለይተው ማወቅ አልቻሉም፡፡
የኢቦላ ወረርሽኝ መቼ እንደሚከሰት በእርግጠኛነት መተንበይ በሚያስችል መልኩ የብጥብጥ ክስተት መረጃዎችን አላገኙም ፡፡
ተመራማሪዎቹ እንደሚመክሩት የዲ.ሪ.ኮ ባለስልጣናት በተጎዱ አካባቢዎች እና በእርግጥ በሁሉም የሃገሪቱ ክፍሎች ቀደም ብሎ ለማወቅ እና የበሽታውን ስርጭት ለመቀነስ እና ለመቆጣጠር ጠንካራ የበሽታ ክትትል እና ምላሽ ስረአትን ይዘረጋሉ፡፡
Hausa translation of DOI:
Luganda translation of DOI: