Skip to main content
SearchLoginLogin or Signup

በደቡብ አፍሪካ በተሽከርካሪ እቶን ውስጥ የሚገኙ የማንጋኒዝ ማእድኖች ሲሞቁ የሚያወጡት ድምጽ ላይ የሙቀት መጠን እና የመሽከርከር ፍጥነት ያላቸውን ተጽእኖ ለመመጠን የሚጠቅም ዘዴ

This is Amharic translation of DOI: DOI: 10.1007/978-3-030-36540-0_72

Published onJun 20, 2023
በደቡብ አፍሪካ በተሽከርካሪ እቶን ውስጥ የሚገኙ የማንጋኒዝ ማእድኖች ሲሞቁ የሚያወጡት ድምጽ ላይ የሙቀት መጠን እና የመሽከርከር ፍጥነት ያላቸውን ተጽእኖ ለመመጠን የሚጠቅም ዘዴ
·

በደቡብ አፍሪካ በተሽከርካሪ እቶን ውስጥ የሚገኙ የማንጋኒዝ ማእድኖች ሲሞቁ የሚያወጡት ድምጽ ላይ የሙቀት መጠን እና የመሽከርከር ፍጥነት ያላቸውን ተጽእኖ ለመመጠን የሚጠቅም ዘዴ

Abstract

የMn ማዕድናት ማዕድናዊ እና ብረታዊ ባህሪያትን በተመለከተ በፌሮማንጋኒዝ ቅይጥ ብረት ምርት ዙሪያ የእውቀት ማነስ የተለመደ ችግር ነው።

መድቀቅ፤ ማለትም በማሞቅ ጊዜ የጠጣር ቅንጣቶች መሰባበር፤ በቂ ጥናት ያልተደረገበት የማንጋኒዝ ማዕድናት ጠቃሚ የጥራት መለኪያ ነው።

ይህ ስራ ማዕድኖቹ በተሸከርካሪ እቶን ውስጥ ቀድመው ሲሞቁ በመድቀቅ ኢንዴክስ ላይ የተለያዩ መለኪያዎች ያላቸውን ተፅዕኖ ያጠናል።

እነዚህ መመዘኛዎች የእሽክርክሪቱ ፍጥነት፣ የማሞቂያ ፍጥነት፣ ሙቀት እና የማዕድናዊ ስብጥር ናቸው።

ሁለቱ ከተመሳሳይ ቦታ የመጡ ሶስት የደቡብ አፍሪካ ማእድናት በዚህ ጥናት ጥቅም ላይ ይውላሉ፡፡

የዚህ ጽሁፍ አላማ የዘዴ አወቃቀር ላይ ሪፖርት ማቅረብ ነው፡፡

Summary Title

የማንጋኒዝ ማዕድንን ምስጢር ለማግኘት አዲስ ሙከራ፡፡

ተመራማሪዎች በደቡብ አፍሪካ ስለሚመረተው የማንጋኒዝ ማዕድን ባህሪያት ጥያቄዎችን ለመመለስ አዲስ ሙከራ አቅርበዋል።

ተመራማሪዎች በብረት ምርት ጊዜ የማንጋኒዝ መበላሸትን የሚቀንሱ የእቶን ሁኔታዎች የትኞቹ እንደሆኑ ለማወቅ አዲስ ሙከራ አቅርበዋል።

በብረት ምርት ውስጥ አስፈላጊው እርምጃ ማንጋኒዝን በኤሌክትሪክ-አርክ እቶን ውስጥ በማሞቅ ከማዕድኑ ውስጥ መለየት ነው።

በሚያሳዝን ሁኔታ እንደዚህ አይነት ሙቀት ሲያገኝ ማንጋኒዝ የመድቀቅ አዝማሚያ አለው ወይም ተሰባብሮ አቧራ ይሆናል፡፡ እና ይሄ ደግሞ በጋዝ ክምችት ምክንያት ሂደቱ ውጤታማ እንዳይሆን እና ፍንዳታ የማስከተል አቅም እንዲኖረው ያደርጋል።

ይህ ጥናት የማንጋኒዝ ማዕድን መድቀቅን ሊቀንሱ የሚችሉ ሁኔታዎችን ለማወቅ አዲስ የሙከራ ዘዴን ያቀርባል።

ተመራማሪዎቹ ይህን ለመሞከር ተሸከርካሪ እቶንን የመጠቀም ሃሳብ አቅርበዋል፡፡ ይህም የሚሽከረከር እቶን አይነት ሲሆን ማእድኑ በኤሌክትሪክ አርክ እቶን ውስጥ ከመሰራቱ በፊት በቅድሚያ ለማሞቅ ይጠቅማል፡፡

ተመራማሪዎቹ በደቡብ አፍሪካ ከካላሃሪ ማንጋኒዝ እርሻዎች የተገኙ ማዕድናትን ይጠቀማሉ እንዲሁም ትንሽ ተሸከርካሪ እቶን በመጠቀም በቤተ ሙከራ ውስጥ እንዴት ማዕድናቱ እንደሚደቁ ይፈትሻሉ።

ጥናቱ የመድቀቅ ደረጃውን በተለያዩ የእሽክርክሪት ፍጥነት፣ የሙቀት መጠን፣ የማሞቅ ፍጥነት፣ የማዕድኖቹ ቅንጣት መጠን እና የቁራጮቹን ኬሚካላዊ ቅንጅት ይፈትሻል።

ተመራማሪዎቹ፣ የታቀደው ሙከራ ውጤት ለማምጣት ያለውን አቅም ለማጥናት ከዚህ ቀደም የመጀመሪያ ደረጃ ጥናት አድርገዋል።

የተለያዩ የማንጋኒዝ ማዕድኖች ቀድመው ሲሞቁ እንደየ ኬሚካላዊ ቅንጅታቸው በተለያየ ፍጥነት እንደሚደቁ የሚያሳዩ ተስፋ ሰጪ ግኝቶችን አግኝተዋል።

Connections
1 of 5
Comments
0
comment
No comments here
Why not start the discussion?