Skip to main content
SearchLoginLogin or Signup

ከ60% በላይ የሆኑት የአፍሪካ ነርሶች የታችኛው ጀርባ ህመም አለባቸው፡፡

Amharic translation of DOI: 10.1186/s12891-020-03341-y

Published onJul 16, 2023
ከ60% በላይ የሆኑት የአፍሪካ ነርሶች የታችኛው ጀርባ ህመም አለባቸው፡፡
·

አፍሪካ ውስጥ ባሉ ክሊኒካዊ መቼቶች በሚያገለግሉ ነርሶች ዘንድ የሚከሰት የታችኛው ጀርባ ህመም ፡ የ19 አመታት ጥናቶች ስልታዊ ክለሳ እና ሜታ ትንተና፡

የጀርባ ታሪክ

 ነርሶች በአፍሪካ በአብዛኛዎቹ የጤና እንክብካቤ አገልግሎት ሰጪ ቦታዎች ላይ በመገኘት የተለያዩ እና ሰፊ ተግባራትን የሚያከናውኑ እና በጣም አስፈላጊ የፊት መስመር የጤና እንክብካቤ ሠራተኞች እንደሆኑ አያከራክርም፡፡

እንደዚህ ያሉ ተግባራት በስራ ጫና ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ የሚጠበቁ ናቸው፡፡

ነርስነት የታችኛው ጀርባ ህመምን በማስከተል በከፍተኛ የአደገኛነት ደረጃ ከተዘረዘሩት የሞያ አይነቶች መካከል ይካተታል፡፡

የነርስነት ሞያ ለየታችኛው ጀርባ ህመም አደጋ ተጋላጭ ከሆኑት ዋነኛ አስር ሞያዎች ውስጥ ተመድቧል፡፡

ስለዚህ ይህ ግምገማ ግብ ያደረገውም የታችኛው ጀርባ ህመም በአፍሪካ የጤና እንክብካቤ ሰጪ ቦታዎች ላሉ ነርሶች ጉልህ ስጋት መሆን አለመሆኑን ለማረጋገጥ ነው፡፡

ስልቶች

 የPRISMA ደንብን በመጠቀም እ.ኢ.አ ከመስከረም እስከ ህዳር 2018 ዓ.ም በቀን ያልተወሰኑ የውሂብ ጎታዎች ላይ አጠቃላይ የስነ ጽሁፍ ፍተሻዎች ተካሂደዋል፡፡

የተካተቱት ጥናቶች ጥራት በ12- የንጥል ደረጃ አሰጣጥ ስርአት ተገምግሟል፡፡

የንዑስ ቡድን እና የተጋላጭነት ትንተናዎች ተከናውነዋል፡፡

ልዩነቶችን ለመገምገም Cochran’s Q እና I2ቱ ፈተናዎች ጥቅም ላይ ውለዋል፡፡

የህትመት አድሏዊነት መኖር አለመኖር በኤገር ፈተና እና እይታ የተመረመረ ሲሆን በፈንጠዚያ ሴራዎች ውስጥ ያለውን ሲሜትሪ ገምግሟል፡፡

ውጤት

 በዚህ ክለሳ፣19 ጥናቶች ከተለያዩ የአፍሪካ ክልሎች በአጠቃላይ 6110 መጠን ያለቸው ናሙና ነርሶች ተካትተዋል፡፡

ሁሉም ጥናቶች የተካሄዱት እ.ኢ.አ በ2000 እና 2018 ዓ.ም መካከል ነው፡፡

ከነዚህም መካከል ዝቅተኞቹ እና ከፍተኞቹ መስፋፋቶች በተከታታይ 44.1እና 82.7% ሆነው ተገኝተዋል፡፡

የዘፈቀደ ተጽእኖ ሞዴል በመጠቀም የታችኛው ጀርባ ህመም በነርሶች ዘንድ የመስፋፋቱ ደረጃ ግምት 64.07% ሆኖ ተገኝቷል (95% CI: 58.68–69.46; P-value < 0.0001)፡፡

የተከለሱት ጥናቶች ልዩነቶች I2 = 94.2% እና ልዩነቶች Chi-squared = 310.06 (d.f = 18), P-value < 0.0001ነበሩ፡፡

የንዑስ ቡድን ትንተናዎች ከፍተኛው የ የ.ጀ.ህ መስፋፋት ደረጃ በምእራብ አፍሪካ ክልሎች ባሉ ነርሶች ዘንድ 68.46% (95% CI: 54.94–81.97; P-value < 0.0001) ሲሆን፣ የሰሜን አፍሪካ ክልል ደግሞ በ67.95% የመስፋፋት ደረጃ እንደሚከተል ያሳያሉ፡  (95% CI: 55.96–79.94; P-value < 0.0001)፡፡

መደምደሚያ

ምንም እንኳ ከምእራቡ እና ከእስያውያን ጥናቶች ጋር ሲነጻጸር፣ የአሁኑ ጥናት አጠቃላይ መስፋፋት ዝቅተኛ ቢሆንም፣በነርሶች ዘንድ ያለው የታችኛው ጀርባ ህመም መስፋፋት እጅግ የበዛ መሆኑን ይጠቁማል፡፡


ከ60% በላይ የሆኑት የአፍሪካ ነርሶች የታችኛው ጀርባ ህመም አለባቸው፡፡

ከ60% በላይ የሆኑት የአፍሪካ ነርሶች የታችኛው ጀርባ ህመም አለባቸው፡፡

 የጤና እንክብካቤ ምንጮች እምብዛም በሆኑበት በአፍሪካ፣ ነርሶች እጅግ አስፈላጊ የፊት መስመር ሠራተኞች ናቸው፡፡

ይህ ጥናት፣ በአፍሪካ ከ60% በላይ የሚሆኑ ነርሶች በየታችኛው ጀርባ ህመም (የ.ጀ.ህ) እንደሚሰቃዩ የሚያሳየውን እና19 አመታት የፈጀውን ምርምር ገምግሟል፡፡

 ነርሶች በአፍሪካ መተኪያ የለሽ ናቸው፤ የስራው ጫና ግን ሰውነታቸውን ይጎዳዋል፡፡

በአለም አቀፍ ደረጃ ለየ.ጀ.ህ አደጋ የመጋለጥ ጉዳይ ሲለካ፣ ነርስነት ከዋነኞቹ 10 ሞያዎች አንዱ ነው፡፡

እንደ እውነቱ ከሆነ፣ የ.ጀ.ህ በአውስትራሊያ 63% ፣በቻይና 56% እና በአንዳንድ የአፍሪካ ሃገሮች 82.7% በሚሆኑ ነርሶች ላይ ከፍተኛ እንደሆነ ተዘግቧል፡፡

ተመራማሪዎቹ እንዴት የ.ጀ.ህ በአፍሪካ ባሉ ነርሶች ላይ እንደተስፋፋ ለመገንዘብ 19 አመት የፈጀውን ጥናት ቃኝተዋል፡፡

 በተለያየ የጊዜ ልዩነት እና ስፋት በ2000 እና 2018 መካከል የታተሙትን ጥናቶች፣ ለማግኘት፣ በተለያዩ የውሂብ ጎታዎች የሚገኙትን ሳይንሳዊ ስነ ጽሁፎችን ፈትሸዋል ፡፡

ተመራማሪዎቹ ይህንን ስልታዊ ክለሳ ጥናት እ.ኢ.አ ከመስከረም እስከ ህዳር 2018 ዓ.ም አካሂደዋል፡፡

 ጥናቱ ከመላው አፍሪካ ከተለያዩ ክልሎች የተሰበሰቡ 6110 ነርሶች የተካተቱባቸውን 19 ጥናቶች ተጠቅሟል፡፡

በአፍሪካ 64.07% ነርሶች በየታችኛው ጀርባ ህመም ይሰቃያሉ፡፡

ጥናቱ ፣ምእራብ አፍሪካ በየ.ጀ.ህ በሚሰቃዩ ነርሶች ቁጥር ከፍተኛውን 68.46% ሲይዝ፣ሰሜን አፍሪካ ደግሞ በ67.95% እንደሚከተል ደርሶበታል፡፡

ተመራማሪዎቹ እንደሚሉት የ.ጀ.ህ እንዴት በአፍሪካ ዙሪያ ባሉ ነርሶች ላይ እንደተስፋፋ ለመመርመር ይህ ጥናት የመጀመሪያው ስልታዊ ክለሳ እና ሜታ ትንተና ነው፡፡

በሚያሳዝን ሁኔታ፣በአፍሪካ ባሉ ጥቂት ክልሎች ውስጥ መረጃ ስላልተገኘ፣በዚህ ጥናት የተዘገቡትን አንዳንድ ውጤቶች ሳያዛባቸው አይቀረም፡፡

ምንም እንኳ እዚህ የተዘገቡት ቁጥሮች በምእራቡ እና በእስያ ከተደረጉት ጥናቶች ጋር ሲነጻጸሩ አነስተኛ ቢሆኑም፣አሁንም በአሳሳቢ ደረጃ ከፍ ያሉ ናቸው፡፡

ተመራማሪዎቹ እንደሚመክሩት፣በአፍሪካ ያሉ ሆስፒታሎች እና መንግስታት የተሻሉ የሥራ ሁኔታዎችን እና የጭንቀት ቅነሳ ዘዴዎችን ማስተዋወቅ እና የ.ጀ.ህ አደጋን በከፍተኛ ደረጃ ለመቀነስ ስልጠናዎችን ለነርሶች መስጠት ይገባቸዋል፡

Connections
1 of 5
Comments
0
comment
No comments here
Why not start the discussion?