Description
Lay summary of the article published under the DOI: https: 10.1186/s12902-020-0534-5
Amharic translation of DOI: 10.1186/s12902-020-0534-5
የስኳር በሽታ (ስ.በ) ትልቅ የኢኮኖሚ ጫና ሊፈጥር የሚችል አለም አቀፍ የጤና አጠባበቅ ችግር ነው፡፡
ዳያቤቲክ ፐሪፈራል ኒውሮፓቲ (ዳ.ፐ.ኒ) በስ.በ ያለ የተለመደ በመቁሰል እና በመቆረጥ ምክንያት የበሽታ እና የአካል ጉዳት የመጨመር አቅም ለው የማይክሮ ቫስኩላር ጣጣ ነው፡፡
ምንም እንኳ በአፍሪካ ውስጥ የዳ.ፐ.ኒን መስፋፋት በተመለከተ በ ስ.በ ላይ በተደረጉ የመጀመሪያ ጥናቶች ውስጥ ከፍተኛ መጠን ያለው ልዩነት ቢኖርም፤
ስለዚህም ይህ ጥናት ዳ.ፐ.ኒ በአፍሪካ ውስጥ በስ.በ ታማሚዎች ላይ ያለውን አጠቃላይ ስርጭት ለመገመት ያቀደ ነው፡፡
በመስመር ላይ ተዛማጅ ጽሁፎችን ለማግኘት ስልታዊ በሆነ መንገድ ፐብሜድ፣ስኮፐስ፣ ጉግል ስኮላር፣ በመስመር ላይ ያሉ አፍሪካዊ መጽሄቶች፣ የአ.ጤ.ድ የአፍሪካ ላይብረሪ እና የኮክሬን ግምገማ ተፈትሸው ነበር፡፡
ለስልታዊ ግምገማ እና ለሜታ-ትንተና (ተ.ዘ.እ.ስ.ሜ.ት) መመሪያዎች የተመረጡትን የዘገባ እቃዎች ተከትለዋል፡፡
በተካተቱት ጥናቶች ውስጥ ያለው ልዩነት በ አለመመጣጠን ጠቋሚ (I2) ተገምግሟል፡፡
የህትመት አድሏዊነት በፈነል ፕሎት እና በኤገር የመመለስ ሙከራ ተመርምሯል፡፡
በአፍሪካ በሽተኞች መካከል የተሰበሰበውን የዳያቤቲክ ፐሪፈራል ኒውሮፓቲን ስርጭት ለመገመት የዘፈቀደ- ውጤት በቂ ነበር፡፡
የሜታ-ትንተናው የተካሄደው፣ ስቴታ™ ስሪት 14 ሶፍትዌርን በመጠቀም ነው፡፡
በሜታ-ትንተናው ውስጥ 269,691 ተሳታፊዎችን ያካተቱ ሃያ ሶስት ጥናቶች ተካትተዋል፡፡
አጠቃላዩ የዳያቤቲክ ፐሪፈራል ኒውሮፓቲን ስርጭት 46% ነበር፡ (95% CI:36.21–55.78%).
በንኡስ ቡድን ትንታኔ መሰረት በምእራብ አፍሪካ በስ.በ ታካሚዎች ውስጥ ከፍተኛው የዳያቤቲክ ፐሪፈራል ኒውሮፓቲን ስርጭት በ49.4% ተዘግቧል (95% CI: 32.74, 66.06)፡፡
ይህ ጥናት እንደሚያመለክትው በአፍሪካ አጠቃላይ የዳያቤቲክ ፐሪፈራል ኒውሮፓቲን ስርጭት በአንጻራዊነት ከፍተኛ ነው፡፡
ስለዚህ ዳ.ፐ.ኒ ለየሃገሩ ብቻ የተወሰኑ ፣ ሁኔታን መሰረት ያደረጉ ጣልቃ ገብነቶች እና የመከላከያ ስልቶች ያስፈልጉታል፡፡
ለዳያቤቲክ ፐሪፈራል ኒውሮፓቲ መከሰት ተያያዥ ምክንያቶችን ለመለየት ተጨማሪ የሜታ-ትንተና ያስፈልጋል፡፡
በአለም ከየትኛውም ቦታ ይልቅ በአፍሪካ ውስጥ በስኳር ህመምተኞች ውስጥ አስደንጋጭ የሆነ የነርቭ ጉዳት መስፋፋት አለ፡፡
ተመራማሪዎቹ የአፍሪካ ሃገራት ለዚህ አዳካሚ በሽታ ተጨማሪ ሀብት እና ትኩረት መስጠት አለባቸው ይላሉ፡፡
ዳያቤቲክ ፐሪፈራል ኒውሮፓቲ (ዳ.ፐ.ኒ) የሰው አካል የደም ስኳር መጠንን በትክክል መቆጣጠር በማይችልበት በስኳር በሽታ (ስ.በ) ምክንያት በሚከሰት የነርቭ መጎዳት የሚመጣ ድክመት፣ መደንዘዝ፣እና ህመም ነው፡፡
ብዙ ጥናቶች የዳያቤቲክ ፐሪፈራል ኒውሮፓቲን መስፋፋት አስሰዋል፡፡ ነገር ግን ውጤቶቹ በስፋት ይለያያሉ፤ እንደ ምሳሌ ለመግለጽ፣ በቻይና 8.4% ፣በስሪላንካ፣ 48.1% እና በህንድ፣ 29.2%፡፡
በአፍሪካም ዘገባዎቹ በስፋት ይለያያሉ ፤ ለምሳሌ የነርቭ ጉዳት ህመም በናይጄሪያ 71.1% ፣በጋና 16.6% እና በኢትዮጽያ 29.5% ተዘግበዋል፡
በዚህ ጥናት ተመራማሪዎቹ ስለትክክለኛው መስፋፋት የተሻለ ግንዛቤን ለማግኘት ከአፍሪካ እንዲህ ያሉ ዘገባዎችን ተንትነዋል፡፡
ተመራማሪዎቹ ተዛማጅ የምርምር ጽሁፎችን ለማግኘት ከዲጂታል ቤተ-መጻህፍት ፐብሜድ፣ስኮፐስ፣ ጉግል ስኮላር በመስመር ላይ ያሉ አፍሪካዊ መጽሄቶች፣ የአ.ጤ.ድ የአፍሪካ ላይብረሪ እና የኮክሬን ግምገማን ፈትሸዋል፡፡
ጥናቱ በብዙ የስታትስቲክስ ዘዴዎች በመገልገል ሁሉንም ጥናቶች በጥንቃቄ ለማወዳደር፣ ተመራጭ የዘገባ እቃዎች ለስልታዊ ግምገማ እና ሜታ ትንተና(ተ.ዘ.እ.ስ.ሜ.ት) መመሪያዎችን ተጠቅሟል፡፡
በድምሩ 269 691 ተሳታፊዎችን ያካተቱ 23 ጥናቶችን መርጠዋል፡፡
ተመራማሪዎቹ 10 ከናይጄሪያ፣4 ከኢትዮጽያ፣2 ከካሜሩን፣ 2 ከሱዳን፣2 ከግብጽ፣ እንዲሁም ከጋና፣ከዩጋንዳ፤እና ከታንዛኒያ ከእያንዳንዳቸው 1 አንድ ጥናቶችን ተጠቅመዋል፡፡
ባጠቃላይ የዳያቤቲክ ፐሪፈራል ኒውሮፓቲ መስፋፋት በአፍሪካ አህጉር 46% ሲሆን ከፍተኛው ስርጭት የሚገኘው በምእራብ አፍሪካ 49.4% የስኳር በሽተኞች ላይ ነው፡፡
ይህ ግኝት በሌላው ታዳጊ ሀገር በኢራን ከተደረገው 53% መስፋፋትን ካሳየው ትንታኔ ጋር የሚስማማ ነው፡፡
በአንጻሩ ባደጉት ሃገሮች የተካሄደ ትንታኔ 35.78% ብቻ መስፋፋቱን ዘግቧል፤ ታዳጊ ሃገሮች የስኳር በሽተኞች የነርቭ ጉዳትን ለመከላከል ይችሉ ዘንድ የደማቸውን ስኳር ለመቆጣጠር የሚያግዙ ተጨማሪ አገልገሎቶችን መስጠት እንደሚኖርባቸው ጠቁመዋል፡፡
ተመራማሪዎቹ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ጽሁፎችን ብቻ በመመልከታቸው እንደ ስፓኒሽ፣ፈረንሳይኛ ወይም ፖርቹጊዝ ባሉ ሌሎች ቋንቋዎች የተጻፉ የታካሚ ዘገባዎች ሊያመልጧቸው እንደሚችሉም አምነዋል፡፡
ሌላው የጥናት ገደብ ተመራማሪዎቹ ሆስፒታልን ብቻ መሰረት ያደረገ መረጃ ብቻ መጠቀማቸው ነው፤ ይህም ከፍተኛ መጠን ያለው የስኳር ህመምተኛ ማህበረሰቦችን ሳያስስ ይቀራል፡፡
ይህ ጥናት በአፍሪካ ያሉ አብዛኛዎቹ የስኳር በሽታ ታማሚዎች ከበሽታቸው ጋር በተያያዘ የነርቭ ጉዳት እንደሚሰቃዩ ገልጧል፡፡
በዚህ ውጤትም ተመራማሪዎቹ የአፍሪካ ሃገሮች የስኳር ህመምተኞችን ለመርዳት ሁኔታን መሰረት ያደረጉ ጣልቃ ገብነቶችን እና የመከላከያ ስልቶችን እንዲተገብሩ ይመክራሉ፡፡
Northern Sotho translation of DOI: 10.1186/s12902-020-0534-5
Hause translation of DOI: 10.1186/s12902-020-0534-5
Luganda translation of DOI: 10.1186/s12902-020-0534-5