Skip to main content
SearchLoginLogin or Signup

ስርአት ተኮር አቀራረብ ቁልፍ የኤችፒቪ- ፖዘቲቭ የማህጸን በር ካንሰር ተቆጣጣሪዎችን ለይቶ ያወጣ

This is Amharic translation of DOI: 10.1101/2020.05.12.20099424

Published onJun 20, 2023
ስርአት ተኮር አቀራረብ ቁልፍ የኤችፒቪ- ፖዘቲቭ የማህጸን በር ካንሰር ተቆጣጣሪዎችን ለይቶ ያወጣ
·

ስርአት ተኮር አቀራረብ ቁልፍ የኤችፒቪ- ፖዘቲቭ የማህጸን በር ካንሰር ተቆጣጣሪዎችን ለይቶ ያወጣል

Abstract

በአለም ዙሪያ ባሉ ሴቶች ላይ የማህጸን በር ካንሰር በጣም የተስፋፋው እና ገዳይ የሆነ ማሊግናንሲ ሲሆን፣ እ.ኢ.አ በ2019 ዓ.ም. ከ 250,000 በላይ ሞቶችን አስከስቷል፡፡

ዘጠና አምስት በመቶ ያህል የማህጸን በር ካንሰር ክስተቶች ከማያቋርጥ ከፍተኛ ስጋት ካለው ሂዩማን ፓፒሎማ ቫይረስ (HPV) ጋር የተቆራኙ ሲሆን፣ ከእነዚህ ሰባ በመቶ የሚሆኑት አስተናጋጁ ውስጥ ካሉ የቫይረስ ውህደቶች ጋር ይያያዛሉ፡፡

የHPV ኢንፌክሽን በተቆጣጣሪው ድህረ መረብ ላይ የትንበያ እና የምርመራ ጥቅም ያላቸው የተለከፉ የካንሰር ህዋሶች ላይ ልዩ ለውጦችን ያስከስታል፡፡

እዚህ፣ በስረአቶች ደረጃ የተቆጣጣሪ አውታረ መረቦች ለውጥ እና HPV ፖዘቲቭ የማህጸን በር ካንሰር ውስጥ ያሉ ተያያዥ ተቆጣጣሪ ፕሮቲኖች ላይ ትንተና አድርገናል፡፡

የHPV ፖዘቲቭ ካንሰሮች በብዙ የህዋሳት ሂደቶች መዛባት ተለይተው እንደሚታወቁ በተለይም ከህዋስ ኡደት፣ ሚቶሲስ፣ ሲይቶኪን እና ከተከላካይ ህዋሳት ምልክት ሰጪ ጋር የተያያዙትን ለማሳየት ተግባራዊ የመንገድ ትንተናን ተጠቅመናል፡፡

የስሌት ትንበያዎችን በመጠቀም፣ የ HPV ፖዘቲቭ የማህጸን በር ካንሰሮች SOX2፣ E2F፣ NANOG፣ OCT4፣ እና MYCን በሚያካትቱ የትራንስክሪፕሽን ፋክተሮች ቁጥጥር የሚደረግባቸው ሲሆን፣ እነዚህም፣ የተለያዩ እንደ የካንሰር ግንድ ህዋስ እድሳትን እና የእጢ ህዋሶችን መስፋፋት እና ልዩነት የሚቆጣጠሩ ናቸው፡፡

ወደላይ ተቆጣጣሪ ኪናሲስ ትንተና መሰረት፣ በሚቶጂን የነቃውን ኪናሲስ ፕሮቲን ከሌሎች በተጨማሪ MAPK1፣ MAPK3 ፣ MAPK8 እና በሳይክሊን ላይ ጥገኛ የሆነውን ኪናሲስ ከሌሎች ተጨማሪ CDK1፣ CDK2 እና CDK4 በ HPV ፖዘቲቭ የማህጸን በር ካንሰሮች ላይ የኪናሲስን የባዮሎጂ ሂደት የሚቆጣጠሩት ዋናዎቹ እንደሆኑ አግኝተናል፡፡

አንድ ላይ ሲወሰዱ፣ በHPV ፖዘቲቭ የማህጸን በር ካንሰሮች ቁልፍ የቁጥጥር መንገዶች እና ፕሮቲኖችን ገጽታ እንገልጣለን፡፡ ሁሉም ለተጨማሪ ቴራፒዩቲክስ ማራኪ የመድሃኒት ኢላማዎችን ይሰጣሉ፡፡

Summary Title

ከHPV ጋር ለተያያዘ የማህጸን በር ካንሰር ሊሆኑ የሚችሉ የመድሃኒት ኢላማዎች ተገኝተዋል፡፡

ተመራማሪዎች አንዳንድ የተወሰኑ ሞሊኪዮሎች እና መንገዶች ከሂዩማን ፓፒሎማ ቫይረስ (HPV) ጋር የተያያዘውን የማህጸን በር ካንሰር የያዛቸውን ሴቶች ለማከም ሊረዱ የሚችሉ የመድሃኒት ኢላማዎች እንደሆኑ ለይተዋል፡፡

በታማሚ መረጃ እና በስሌት ትንበያዎች ላይ በመመስረት፣ የህዋስ እድገት እና ክፍፍል ሂደትን የሚቆጣጠሩ ብዙ የትራንስክሪፕሽን ፋክተሮችን እና ሌሎች ምልክት ሰጪ ፕሮቲኖችን ይጠቁማሉ፡፡ እነዚህም፣ በቴራፒዎች በአንድ ጊዜ ሊነጣጠሩ ይችላሉ፡፡

ወደ 90% የሚጠጉ የማህጸን በር ካንሰር ጉዳዮች የሚከሰቱት የበሽታው ሸክም ባለተመጣጠነ መልኩ ከፍተኛ በሆነባቸው በታዳጊ ሃገራት ላይ ነው፡፡

አለም አቀፍ ደረጃ በአመት ከ300,000 በላይ ሴቶችን የሚገል እጅግ ገዳዩ የሴቶች ካንሰር ነው፡፡

ከዚህ ጥናት በፊት፣ ከሌሎች ጥናቶች መሃል የካንሰር ጄኖም አትላስ ፕሮጀክት፣ በማህጸን በር ካንሰር ላይ ተሳታፊ የሆኑትን ጂኖች እና ፕሮቲኖች በዝርዝር ዘግበዋል፡፡

በሞሊኪዩላዊ ደረጃ ካንሰር ያለበት የማህጸን በር ገጽታ ከጤነኛ የማህጸን በር እንዴት እነደሚለይ በዝርዝር አሳይተዋል፡፡

ይሄ ጥናት እነዚህ ልዩነቶች እንዴት እንደሚፈጠሩ በትክክል ለማሳየት ሞክሮ ነበር፡፡ በሌላ አነጋገር፣ በማህጸን በር ዕጢዎች ውስጥ የተካተቱት ጂኖች እና ፕሮቲኖች አንዴት እንደሚነቁ እና እንደሚጠፉ ወይም ወደላይ እና ወደታች እንደሚሉ፡፡

በአውታረ መረቡ ውስጥ የሚሳተፉትን ጂኖች እና ፕሮቲኖች የሚቆጣጠሩትን ዋነኛ ሞሊኪዮሎችን በመለየት፣ ተመራማሪዎች ልዮ መንገዶቻቸውን የሚያግዱ መድሃኒቶችን መስራት ይችላሉ፡፡

እነዚህን ተቆጣጣሪ ሞሊኪዮሎች እና መንገዶቻቸውን ለመለየት፣ ከዛምቢያ እና ከደቡብ አፍሪካ የመጡ ተመራማሪዎች ለ HPV ፖዘቲቭ የሆኑ የማህጸን በር ካንሰር ለ HPV ኔጋቲቭ ከሆኑ እና እንዲሁም የማህጸን በር ካንሰር ከሌለባቸው ታካሚዎች ጄነቲካዊ መረጃዎች ጋር አወዳድረዋል፡፡

በHPV ፖዘቲቭ ቡድን ውስጥ ጉልህ ልዩነቶችን ለይተው ካወጡ በኋላ፣ የተሳታፊ ቁጥጥር መንገዶችን እና ሞሊኪዮልችን ለመተንበይ ሃይለኛ ሶፍትዌር ተጠቅመዋል፡፡

ዋና ግኝታቸው፣ HPV በህዋስ እድገት እና ክፍፍል ላይ የሚሳተፉት መንገዶች ላይ ተጽእኖ እንደሚያደርግ ነው፡፡ ስለዚህ ጸኃፊዎቹ የማህጸን በር ካንሰር እነዚህ መንገዶች ላይ ለሚያነጣጥሩ መድሃኒቶች ምላሽ ሊሰጡ እንደሚችሉ ጠቁመዋል፡፡

ይህ፣ የማህጸን በር ካንሰሮች የህዋስ ኡደት ሂደቶችን አስረው ለሚይዙ መድሃኒቶች ከፍተኛ ቴራፒዩቲክ ምላሽ እንደሚሰጡ የሚያሳዩ ነባር ክሊኒካዊ ግኝቶችን ይደግፋል፡፡

በእብጠት እና በበሽታ መከላከል ውስጥ የተሳተፉ መንገዶች በዚህ ጥናት ውስጥ ተጠቁመዋል፡፡

ተመራማሪዎች በተለያዩ የካንሰር ንኡስ አይነቶች መሃል ያለውን የሞሊኪዩላዊ መንገዶች ልዩነት ለማወቅ ተጨማሪ ስራ ያስፈልጋል ይላሉ፡፡

95% የሚያህሉት የማህጸን በር ካንሰር ክስተቶች ከከፍተኛ የማያቋርጥ HPV ኢንፌክሽን ጋር የተቆራኙ ሲሆን፣ በሽታው በሰውነት ውስጥ ካሉ ሞሊኪዮሎች ጋር እንዴት እንደሚገናኝ ለይቶ ማወቅ በአፍሪካ እና በአለም ውስጥ ላሉ ሴቶች የተሻለ ቴራፒን ለመስጠት ቁልፍ ነገር ነው፡፡

Connections
1 of 5
Comments
0
comment
No comments here
Why not start the discussion?