Skip to main content
SearchLoginLogin or Signup

በታንዛኒያ በምግብ እና በእርሻ ዘርፎች የጸረ ተህዋስ መድሃኒት ጥቅም ፣ቅሪቶች፣ የመቋቋም ሃይል እና አስተዳደር

This is Amharic translation of DOI: https://www.mdpi.com/2079-6382/10/4/454#

Published onJul 24, 2023
በታንዛኒያ በምግብ እና በእርሻ ዘርፎች የጸረ ተህዋስ መድሃኒት ጥቅም ፣ቅሪቶች፣ የመቋቋም ሃይል እና አስተዳደር
·

በታንዛኒያ በምግብ እና በእርሻ ዘርፎች የጸረ ተህዋስ መድሃኒት ጥቅም ፣ቅሪቶች፣ የመቋቋም ሃይል እና አስተዳደር

Abstract

ሁሉም ኢንፌክሽኖች የመነሾ ወኪሎቻቸው ለጸረ ተህዋስ መድሃኒቶች ተገዢ እስከሆኑ ድረስ መዳን የሚችሉ ናቸው፡፡

እየጨመረ የመጣው የጸረ ተህዋስ መድሃኒቶች ውጤታማነት መቀነስ በጣም አሳሳቢ አለም አቀፍ የጤና አደጋ እየሆነ ነው፡፡ይህም በሽታን ለመከላከል የሚጠቅሙንን ጸረ ተህዋስ መድሃኒቶች ከጥቅም ውጪ እንዳያደርጋቸው ያሰጋል፡፡

እየጨመረ የመጣው የእንስሳት ተዋጽኦ የምግብ ጥያቄ በተለይም እንቁላል፣ ስጋ፣ እና ወተት የተጠናከሩ የንግድ ምርት ስርአቶችን አስከትለዋል፡፡ ይህም እጅግ የበዛ እና አግባብነት የጎደለው የጸረ ተህዋስ መድሃኒቶች አጠቃቀምን ሊያበረታታ ይችላል፡፡

የጸረ ተህዋስ መድሃኒቶች መደበኛ ትምህርት ባልወሰዱ ገበሬዎች እና እንስሳትን በሚጠብቁ ሰዎች እንዲያዙ ሲደረግ ቅድመ ዝንባሌያቸው ሊሆን የሚችለው፣ ትክክለኛ ያልሆነ መጠን መስጠት፣ ያላግባብ መጠቀም፣ ልክ ባልሆነ መንገድ መተግበር እና መድሃኒቶቹ መወሰድ ለሌለባቸው ጊዜያት አለመታዘዝ ነው፡፡

ይህ ጥናት የተካሄደው፣ የጸረ ተህዋስ መድሃኒቶችን የቁጥጥር ሚናዎች እና አስተዳደርን ለማጥናት ነው፡፡ የአጠቃቀማቸውንም መጠን እና የአካሄድ ስርአታቸውን መሰረት በማስያዝ፣የጸረ ተህዋስ መድሃኒት ቅሪቶችን እና የመቋቋም ሃይልን ለምግብነት በሚውሉ እንስሳት እና በእርሻ ሰብል የዋጋ ሰንሰለቶች ላይ ይገመግማል፡፡ እነዚህንም ግኝቶች ከነባሮቹ ስልቶች ጋር በማዛመድ በታንዛኒያ የተከሰተውን የጸረ ተህዋስ መድሃኒት ተቃርኖን ይዋጋል/ይከላከላል፡፡

ብዙ አይነት ዘዴዎችን የተከተለ አካሄድ (የቢሮ ውስጥ ግምገማ፣የመስክ ጥናት እና ቃለ መጠየቅ) በስራ ላይ ውሏል፡፡

ተዛማጅነት ያላቸው ተቋማትም ተጎብኝተዋል፡፡

ለ ፔኒሲሊን ጂ፣ ለክሎራምፊኒኮል፤ ለስትሬፕቶማይሲን፤እና ለኦክሲቴትራሳይክሊን መድሃኒቶች ከፍተኛ የመቋቋም ደረጃ እንዳለ ተመዝግቧል፡፡ በተለይም ለ አስቲኖባክተር ፓዮጄኒስ በማስቲቲስ ከተያዙ ሰዎች እና ከብቶች ስታፊሎካከስ ሃይከስ፣ስታፊሎካከስ ኢንተርሚዲየስ እና ስታፊሎካከስ ኦሪየስ ተገኝተዋል፡፡

በዶሮ እርባታው ስፍራ ተመሳሳይ አዝማሚያዎች እንቁላል እና ስጋን በሚበክሉት የኢሸሪኪያ ኮላይ ዘሮች ላይ ተገኝተው ነበር ፡፡ ኢሸሪኪያ ኮላይም አሞክሲሲሊን +ክላቩላኔት፣ ሰልፋሜቶክሳዞልን እና ኒዮማይሲንን መድሃኒቶችን ይቋቋማል፡፡

እየጨመረ በመሄድ ላይ የሚገኘው ብዙ መድሃኒቶችን የመቋቋም አዝማሚያ በኢ ኮላይ፣ክሌብሲዬላ ኒሞኒዬ፣ስታፍሎካከስ ኦሪየስ እና ሳልሞኔላንም ጨምሮ ለመብል በሚውሉ እንስሳት ውስጥ ተገኝተዋል፡፡

ሜቲሲሊንን የመቋቋም ሃይል በስታፍሎካከስ ኦሪየስ(MRSA) እና በኤክስቴንድንድ ስፔክትረም ቤታ-ላክታሜዝ (ESBL) ላይ መጨመር፣በታንዛኒያ የእንስሳት እርባታ ዘርፍ ተዘግበዋል፡፡

በእንስሳት ውስጥ ብቻ የሚገኙት በሽታ አምጪ ተህዋሲያን አምፒሲሊንን፣ኦግመንቲንን፣ጄንታማይሲንን፣ ኮ ትራይሞክሳዞልን፣ቴትራሳይክሊንን ፣አሞክሲሲሊንን፣ስትሬፕቶማይሲንን ፣ ናሊዲክሲክ አሲድን፤ አዚትሮማይሲንን፣ክሎራምፌኒኮልን፣ ታይሎሲንን፤ ኤሪትሮማይሲንን፣ሲፉሮክክሲምን፣ ኖርፍሎክሳሲንን፣ እና ሲፕሮፍሎክሳሲንን የመቋቋም ሃይል ነበራቸው፡፡

የጸረ ተህዋስ መድሃኒቶችን በሽታ አምጪ የሆኑ ተህዋሲያንን ለመከላከል እና ለህክምና በብዛት መጠቀም ይስተዋላል፡፡ ይህም የእንስሳትን እርባታ ለማበረታታት እና በውሃ ውስጥ ከሚኖሩ እጽዋት እና እንስሳት(አኳካልቸር) በቂ ምርትን ለማግኘት ውሏል፡፡

በታንዛኒያ በምግብ እና ግብርና ዘርፎች፤የጸረ ተህዋስ መድሃኒትቶችን የመቋቋም ሃይል (AMR) ለመዋጋት አንድ ወጥ የጤና ስልታዊ አካሄድ ይመከራል፡፡

ተግባራዊ ምክሮቹም እነዚህን ያካትታሉ (ሀ) ህግጋቱን መገምገም እና መተግበር፤ (ለ) የጸረ ተህዋስ መድሃኒት አጠቃቀም፤ (AMU)፣ AMR፣ እና የጸረ ተህዋስ መድሃኒት ቅሪቶች (AR) በእሴት ሰንሰለቱ ውስጥ የባለድርሻ አካላት ግንዛቤ እና ግልጽ ድጋፍ፤ (ሐ) በጸረ ተህዋስ መድሃኒት አጠቃቀም AMU፣ AMR እና AR ፕሮግራሞች ላይ ቅርብ ክትትል ማድረግ እና ስልታዊ ግምገማን ማጠናከር፤ (መ) የተሻለ ልማት እና ፈጣን እና ፈጠራን የተሞሉ የምርመራ መፈተኛዎች፤ እንዲሁም ሰዎችን ከጎጂ ተህዋሲያን ለመጠበቅ የሚረዱ ሂደቶችንና እርምጃዎችን (ባዮ ሴኪዩሪቲን) ማስተዋወቅ፤ እና (ሰ) ጥሩ የእርባታ ልምምዶች፡፡

የዚህ መረጃ ጥቅም ላይ መዋል የህዝብን የጤና ፖሊሲዎች ለማሻሻል እና የAMR ሸክምን ለመቀነስ ይረዳል፡፡

Summary Title

በታንዛኒያ የተሻሉ ዘዴዎችን በመጠቀም የጸረ ተህዋስ መድሃኒትን የመቋቋም ሃይል መቀነስ ይቻላል

በታንዛኒያ የጸረ ተህዋስ መድሃኒትን የመቋቋም ደረጃ ከፍ ያለ ሲሆን፣ ይህ ደግሞ ህዝቡ በባክቴሪያ የሚፈጠሩ ኢንፌክሽኖችን ለሚዋጉ መድሃኒቶች የሚሰጠውን ምላሽ እንደነገሩ ያደርገዋል፡፡

ተመራማሪዎች የጸረ ተህዋስ መድሃኒትን የመቋቋም ሃይል ሊያመጡ ይችላሉ ያሏቸውን ምክንያቶች በጥልቀት እያጤኑ ሲሆን ፣ይህንን የመቋቋም ሃይል ለመቀነስ በምግብ እና በእርሻው ዘርፍ ላሉ መጥፎ ልምምዶች መፍትሄ መስጠት ግድ መሆኑን ደርሰውበታል፡፡

ጸረ ተህዋስ መድሃኒቶችን የእንስሳት ተዋጽኦ በሆኑ የምግብ ምርቶች ላይ በሰፊው መጠቀም ብቻ ሳይሆን ፣ በጤናው መስክ ከተደነገገው በላይ ስራ ላይ መዋላቸው ውጤታማነታቸውን አናሳ አድርጎታል፡፡

የጸረ ተህዋስ መድሃኒትን የመቋቋም ሃይል አለም አቀፍ የጤና ስጋት ነው፡፡

ጸረ ተህዋስ መድሃኒቶችን ያለልክ በእንስሳት ላይ መጠቀም በዝቅተኛ የትምህርት ደርጃ ምክንያት እነዚህን መድሃኒቶች በትክክል ለማስተዳደር ብቁ ካልሆኑ ገበሬዎች እና ሌሎች ከእንስሳት ጋር ከሚሰሩ ሰዎች ጋር ተያያዥነት ሊኖረው ይችላል፡፡

ይህ ጥናት መሰረት ያደረገው በታንዛኒያ የጸረ ተህዋስ መድሃኒት አጠቃቀም ዙሪያ ያለው መንግስታዊ ደንብ ምን ያህል ውጤታማ እንደሆነ መመርመር ላይ ነው፡፡

በተጨማሪ ተመራማሪዎቹ የጸረ ተህዋስ መድሃኒቶቹ ምን ያህል ከድንጋጌው በላይ እንደተወሰዱ ለመረዳት ከእንስሳት እና ከሰብል ዋጋ ሰንሰሎቶች ውስጥ ቅሪቶቻቸውን ለማየት ሞክረዋል፡፡

አላማቸውም በሃገሪቱ ውስጥ ያለውን የጸረ ተህዋስ መድሃኒት የመቋቋምን ሃይል ለመግታት የሚያስችል ስልት ማቅረብ ነበር፡፡

ተመራማሪዎቹ ሰነዶችን መርምረዋል፤ የጸረ ተህዋስ መድሃኒቶች ይሰጡባቸው የነበሩ ቦታዎችንም ጎብኝተዋል፡፡

በተጨማሪም 32 ሰዎችን ቃኝተዋል፤ ቃለ መጠይቅም አድርገዋል፡፡ እንዲሁም፣ ከ83 የዶሮ እርቢ አርሶ አደሮች ጋር ትልቅ የቡድን ውይይት አካሂደዋል፡፡

ለጸረ ተህዋስ መድሃኒት ፔኒሲሊን ጂ፣ ለክሎራምፊኒኮል፣ ለስትሬፕቶማይሲን እና ለኦክሲቴትራሳይክሊን መድሃኒቶች ፣ከፍተኛ የመቋቋም ደረጃ እንዳለ ጥናቱ ደርሶበታል፡፡

እነዚህ ወሳኝ የጸረ ተህዋስ መድሃኒቶች ማስቲቲስ የተባለውን የሚያሰቃይ የጡት ኢንፌክሽን በሰዎች እና በላሞች ላይ እንደሚያስከትለው ስታፊሎኮከስ ኦውሪየስ አይነት በሽታ አምጪ ተህዋሲያን ላይ ጥቅም ላይ ውለዋል፡፡

በታንዛኒያ ሌሎች የሚያሰጉ ውጤቶችን በእንስሳት እርባታው ዘርፍ ላይ አግኝተው ነበር፡፡ ለምሳሌ፣ በጨጓንጀት (ጨጓራ እና አንጀት) ላይ ከቀላል እስከ ከባድ ህመም ሊያስከትል የሚችለው ኢሸሪኪያ ኮላይ (ኢ ኮላይ) ላይ ከፍተኛ የጸረ ተህዋስ የመቋቋም ደረጃን አግኝተዋል፡፡

ገበሬዎች ጸረ ተህዋስ መድሃኒቶችን እንደ ፕሮፊላክሲስ (በሽታ መከላከያ መንገድ) እና የእንስሳቶችን እድገት ለማፋጠን በሚያሰጋ መጠን እየተጠቀሙበት መሆኑን ተመራማሪዎቹ አስጠንቅቀዋል፡፡

ተመራማሪዎቹ የጸረ ተህዋስ መድሀኒት የመቋቋም ሃይልን ለመዋጋት በታንዛኒያ የምግብ እርሻ ዘርፎች ፣የአካባቢውን አየር ንብረት፣ እንስሳትን እና ለበሽታው መስፋፋት ተሳታፊ የሆኑ ሰዎችን ከግምት ውስጥ ያስገባ አንድ ወጥ የጤና አካሄድን እንዲጠቀሙ መክረዋል፡፡

ጥናቱ በታንዛኒያ የግብርና ህግጋትን መገምገም እና ተግባራዊነቱንም ማረጋገጥ እንደሚገባ ሃሳብ ያቀርባል፡፡

ተመራማሪዎቹ ይህንን ያልታቀደ የጸረ ተህዋስ መድሃኒቶችን አጠቃቀም ለመቀነስ እና ፈጣን የምርመራ ሙከራዎችን ተጠቅሞ የእንስሳቱን ጤና እና ደህንነት ለማረጋገጥ፣ ለተሻሉ የእንስሳት አረባብ ልምምዶች ይሟገታሉ፡፡

Connections
1 of 5
Comments
0
comment
No comments here
Why not start the discussion?