Description
This is a lay summary of the research article published under the DOI: 10.1101/2020.06.04.20119594
Amharic translation of DOI: 10.1101/2020.06.04.20119594
የኮቪድ-19 ኢንፌክሽን እና ሞት በጤና አጠባበቅ ሠራተኞች (ጤ.አ.ሠ) ላይ ከአለም አቀፋዊ እይታ አንጻር መገመት፡፡
የፍለጋን ስፋት መገምገሚያ መንደፍ፡፡
ሁለት ትይዩ አካዳሚክ የማውጫ መጽሃፍ የመረጃ ጎታ እና የግራጫ ስነ-ጽሁፍ ፍተሻዎች ተካሂደዋል፡፡
በተቻለ መጠን ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ከመንግስታት ጋር ግንኙነት ተደርጓል፡፡
በግምገማው ጊዜ -ተኮር ባህሪ ምክንያት እና ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የሚሄደውን ሁኔታ በጣም ወቅታዊ በሆነ መረጃ ሪፖርት ለማድረግ ካለው ፍላጎት የተነሳ፣በቋንቋ፣ጥቅም ላይ በዋሉ የመረጃ ምንጮች፣በህትመት ሁኔታ እና በማስረጃ ምንጮች ላይ ምንም አይነት ገደቦች አልነበሩም፡፡
የAACODS ማመሳከሪያ ዝርዝር እያንዳንዱን የማስረጃ ምንጭ ለመገምገም ስራ ላይ ውሏል፡፡
የህትመት ባህሪያት፣ አገር-ተኮር የመረጃ ነጥቦች፣የኮቪድ-19 ልዩ መረጃ፣ የተጎዱ የጤ.አ.ሠ ስነ-ህዝብ እና የተወሰዱ የህዝብ ጤና እርምጃዎች
ባጠቃላይ152,888 ኢንፌክሽኖች እና 1413 ሞቶች ተዘግበዋል፡፡
ኢንፌክሽኖቹ በዋነኝነት በሴቶች (71.6%) እና በነርሶች (38.6%) ላይ ነበሩ፡፡ ነገር ግን ሞት በዋነኝነት የተከሰተው በወንዶች ላይ ነበር፤ (70.8%) እና በዶክተሮች (51.4%)፡፡
የተወሰነ መረጃ እንደሚያመለክተው አጠቃላይ ሃኪሞች እና የአእምሮ ጤና ነርሶች ለሞት ከፍተኛ ተጋላጭነት ያላቸው ልዩ ባለሞያዎች ናቸው፡፡
ከ70 በላይ በሆኑ የጤና አጠባበቅ ሠራተኞች ውስጥ ከ100 ኢንፌክሽኖች 37.17 ሞት ተዘግቧል፡፡
(119628) በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር እና (712) ሞት የተመዘገበበት አውሮፓ ከፍተኛ ቁጥር ነበረው፡፡ ነገር ግን የምስራቅ ሜድትራንያን አካባቢ ከ100 ኢንፌክሽኖች የተዘገበው ከፍተኛ የሞት ቁጥር (5.7) ነበረ፡፡
የጤ.አ.ሠ ኮቪድ-19 ኢንፌክሽን እና ሞት አጠቃላይ የአለም ህዝብን ተሞክሮ ይመስላል፡፡፡፡
ልክ እንደ አፍሪካ እና ህንድ ዝቅተኛ የመጠን ሪፖርቶች ሁሉ የጾታ እና የመስክ ልዩነት ምክንያቶች ተጨማሪ ዳሰሳን ይጠይቃሉ፡፡
ምንም እንኳ በተወሰኑ የሥራ መስኮች ውስጥ የተሰማሩ ሃኪሞች ከአፍ እና ከአፍንጫ በሚወጡ ፈሳሾች መጋለጥ ምክንያት እንደ ከፍተኛ ተጋላጭ ሊቆጠሩ ቢችሉም፣ በሌሎች ዘርፎች ያሉትም አደጋዎች መቃለል የለባቸውም፡፡
አረጋዊ ጤ.አ.ሠ ለአደጋ ተጋላጭነታቸው አነስተኛ ወደሆኑት በስልክ የርቀት ምርመራ የማድረግ (ቴሌሜድሲን) ወይም የአስተዳደር ቦታዎች ላይ መመደብ ሊያስፈልጋቸው ይችላል፡፡
የኛ ተግባራዊ አካሄድ አጠቃላይ አዝማሚያዎችን ያሳያል፡፡ እንዲሁም በጤ.አ.ሠ ውስጥ ኢንፌክሽኖችን ለመመርመር እና ለመዘገብ የሁሉአቀፍ መመሪያዎችን አስፈላጊነት ያጎላል፡፡
በኮቪድ-19 እጅጉን የተጠቁ የጤና አጠባበቅ ሠራተኞች እና አጠቃላይ ሃኪሞች፡፡
በአለም ዙሪያ ያሉ የጤና አጠባበቅ ሠራተኞች ከአውዳሚው ኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሌሎችን ለማትረፍ የራሳቸውን ሕይወት አደጋ ላይ ጥለዋል፡፡
ይህ ጥናት የጤና አጠባበቅ ሙያ በወረርሽኙ ምን ያህል በአስከፊ ሁኔታ እንደተመታ እና ባለሙያዎቹ ለኢንፌክሽኑ እና ለሞት አደጋ በእጅጉ እንደተጋለጡ ለመገምገም የመጀመሪያው ነው፡፡
በታህሳስ ወር እ.ኢ.አ በ2019 ዓ.ም መጨረሻ በቻይና ዉሃን ውስጥ ካለው ባህላዊ የህዝብ መገበያያ(ጉሊት) ጋር የተያያዙ የሳንባ ምች ምልክቶች ካሉባቸው ታካሚዎች ስብስብ፣የኮሮና ቫይረስ በሽታ (ኮቪድ-19) በፍጥነት ወደ ሙሉ አለም አቀፍ ወረርሽኝነት ተቀይሯል፡፡
ይህ ጥናት በተደረገበት ወቅት፣ እ.ኢ.አ በግንቦት 2020 ዓ.ም ከአምስት ሚሊዮን ህዝብ በላይ ተበክሏል፤ እንዲሁም ከ300,000 ህዝብ በላይ ሞቷል፡፡
በዚህ አለም አቀፍ ቀውስ ቁጥራቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን በጠና የታመሙ ታካሚዎች የሚመረምሩ እና የሚያክሙ ግንባር ቀደም የጤና አጠባበቅ ሠራተኞች (ጤ.አ.ሠ) ብዙ ጊዜ በብርቱ አካላዊ እና ስነ ልቦናዊ ጫና ስር ሆነው ከባድ ውሳኔዎችን መውሰድ አለባቸው፡፡
ይህም ጤ.አ.ሠን ለከፍተኛ ኢንፌክሽን እና የሞት አደጋ ያጋልጣቸዋል፡፡ ነገር ግን የተጎዱት ሰዎች ትክክለኛ ቁጥር አልታወቀም፡፡
ስለዚህ ይህ ጥናት አለም አቀፍ የጤ.አ.ሠን የኮቪድ-19 የኢንፌክሽን እና የሞት ክስተት ቁጥሮችን ገምቷል፡፡
ተመራማሪዎቹ ከአካዳሚክ ስነ-ጽሁፍ እና ከሌሎችም ድብልቅ ምንጮች (ግራጫ ስነ-ጽሁፍ በመባል የሚታወቁት)ከመላው አለም መንግስታት ከቀረበው ማስረጃ ጨምሮ ከሚዲያ ድረ-ገጾች እና ከmedRxiv ድህረ ገጽ ቅድመ ህትመቶች መረጃን ፈልገዋል፡፡
ጥናቱ 152 888 ጤ.አ.ሠ በኮቪድ-19 እንደተያዙ እና1413 በበሽታው እንደ ሞቱ ደርሶበታል፡፡
ኢንፌክሽኖቹ በዋነኝነት በሴቶች (71.6%) እና በነርሶች (38.6%) ላይ ነበሩ፡፡ ነገር ግን ሞት በዋነኝነት የተከሰተው በወንዶች ላይ ነበር፤ (70.8%) እና በዶክተሮች (51.4%)፡፡
ካለው መረጃ እንደሚታየው ከሃኪሞች መካከል አጠቃላይ ሃኪሞች (ጠ.ሃ ) ለከፍተኛ የሞት አደጋ ተጋላጭ ሲሆኑ፣ከነርሶች ደግሞ ከፍተኛው የሞት አደጋ በአእምሮ የጤና ዘርፎች ውስጥ እንደነበር ጥናቱ ደርሶበታል፡፡
ተመራማሪዎቹ እስከሚያውቁት ድረስ፣ በአለም አቀፍ ደረጃ በ ጤ.አ.ሠ መካከል የኮቪድ-19 ኢንፌክሽን እና ሞትን ለመመርመር ይህ የመጀመሪያው ጥናት ነው፡፡
ሆኖም ግን ሥራቸው ተንሰራፍተው በሚገኙት እና ከተለያዩ የመረጃ ምንጮች በሚገኙት መረጃዎች የተገደበ ነው፡ ይህም ማነጻጸርን አስቸጋሪ አድርጎታል፡፡
የተለያዩ ሃገሮችም መረጃዎችን በሚሰበስቡበት ጊዜ በተለያዩ የወረርሽን ደረጃቸው ላይ ነበሩ፡፡
በጤና አጠባበቅ ሠራተኞች ውስጥ ያለው የኮቪድ-19 ኢንፌክሽን እና ሞት አጠቃላይ የአለም ህዝብን ተሞክሮ ይመስላል፡፡
ልክ እንደ አፍሪካ እና ህንድ ዝቅተኛ የመጠን ሪፖርቶች ሁሉ የጾታ እና የመስክ ልዩነት ምክንያቶች ተጨማሪ ዳሰሳን ይጠይቃሉ፡፡
Hausa translation of DOI: 10.1101/2020.06.04.20119594
Luganda translation of DOI: 10.1101/2020.06.04.20119594
Northern Sotho translation of DOI: 10.1101/2020.06.04.20119594