Skip to main content
SearchLoginLogin or Signup

በዩጋንዳ የእረስ በእርስ ጦርነት እጅ እና እግራቸውን ያጡ ተጎጂዎች እስካሁን ድረስ እርዳታ አላገኙም

Amharic translation of DOI: 10.1101/2020.05.14.095836

Published onMay 24, 2023
በዩጋንዳ የእረስ በእርስ ጦርነት እጅ እና እግራቸውን ያጡ ተጎጂዎች እስካሁን ድረስ እርዳታ አላገኙም
·

በዩጋንዳ በአቾሊ ክፍለ ሃገር ስለ ዋና እጅና እግር ማጣት መስፋፋት እና የቦታ ቅጦች ላይ የተደረገው ሰፊ የክፍል-በክፍል ጥናት፡

የጀርባ ታሪክ

 በሰሜን ዩጋንዳ ከፍተኛ ዋና እጅና እግር ማጣት እንደተከሰተ በሰፊው ተዘግቧል፡፡ ይህም በዋነኝነት የተከሰተው በተራዘመ የእርስ በእርስ ጦርነት ምክንያት እንደሆነ ይታመናል፡፡

የመልሶ ማቋቋም አገልግሎቶች በጣም የተገደቡ ናቸው እና ምን ያህል ሰዎች ዋና የእጅና እግር ማጣት እንዳጋጠማቸው እና ስንቶቹ የህክምና ወይም የመልሶ ማቋቋም አገልግሎት እንዳገኙ ተጠንቶ አያውቅም፡፡

አላማ

በክልሉ የአካል ጉዳት እና ዋና እጅና እግር መጣት የመጀመሪያው የስርጭት ጥናት ሲሆን የዋ.እ.እ.ማ ን የቦታ ቅጦች ገምግሟል፡፡

ንድፍ

ሰፊ የክፍል-በክፍል ጥናት፡፡

መቸት

ይህ ጥናት የተካሄደበት መቸት በማህበረሰቡ ውስጥ ነው(በተጠኒዎቹ ቤት፡፡)

የህዝብ ብዛት

በሰሜን ዩጋንዳ አቾሊ ክፍለሃገር በዘፈቀደ የተመረጡ 7864 ቤቶች፡፡

ስልቶች

 ይሄ ጥናት ሁለት መጠይቆችን አካቶ ነበር፡፡ የመጀመሪያው እንደናሙና በተመረጡት በእያንዳንዱ ቤቶች ውስጥ በቤቱ ሃላፊ የሚጠቃለል ሲሆን (ቁ=7864) ሁለተኛው ደግሞ ዋና እጅና እግር ማጣት ሰለባ በሆነ በማንኛውም የቤተሰብ አባል ይሞላል፡፡

የሞራን አይ ስታትስቲክስን በመጠቀም የቤቶቹ መገኛዎች ለቦታ እርስ በእርስ ተዛምዶ ተመርምረዋል፡፡

ከመላው ህብረተሰብ ጋር ሲነጻጸር ዋና የእጅና እግር ማጣት ያጋጠማቸውን ሰዎች ለይቶ ለማውጣት የX^2 የብቃት ጥሩነት ስታትስቲክስ ጥቅም ላይ ውሏል፡፡

ውጤቶች

 እንደእኛ ጥንቁቅ ግምት የረጅም ጊዜ የመልሶ ማቋቋም አገልግሎቶች የሚያስፈልጓቸው ሐ.10117 ያህል ዋና እጅና እግር ማጣት ሰለባ የሆኑ ሰዎች በክልሉ ይገኛሉ (ሐ.0.5% የህዝብ ብዛት) እና ሐ.150512 ሰዎች ከዋ.እ.እ.ማ (ሐ.8.2% የህዝብ ብዛት)ሌላ የአካል ጉዳት ያለባቸው፡፡

ዋና የእጅና እግር ማጣት ሰለባ የሆኑ ሰዎች በክልሉ ተሰራጭተው ይገኛሉ (በተወሰኑ ቦታዎች ላይ ከመወሰን በተቃራኒ)፡፡ እና ባልተመጣጠነ መልኩ ከመላው ህዝብ ጋር ሲወዳደር ወንዶች፣ በእድሜ የገፉ እና በትምህርታቸው ብዙም ያልገፉ ሰዎችን ያካትታል፡፡

መደምደሚያ

 ይሄ ምርምር ለመጀመሪያ ጊዜ በጥናት ክልሉ ዋና እጅና እግር ማጣት ሰለባ የሆኑ ሰዎች ምን ያህል የረጅም ጊዜ የመልሶ ማቋቋም አገልግሎቶች እንደሚያንሷቸው ያሳያል፡፡

ሰዎች የህክምና እና የመልሶ ማቋቋም አገልግሎቶች የማያገኙበትን ምክንያት በተመለከተ አዲስ ግንዛቤ እንሰጣለን፡፡ እና የተሳካውን የ‘የአዳራሽ ክሊኒክ ሞዴል’ በማሳየት ወደፊት እንዴት መቀጠል እንደሚቻል መንገድ እንጠቁማለን፡፡

ክሊኒካዊ የመልሶ ማቋቋም ተጽእኖ

ዋና የእጅና እግር ማጣት ሰለባዎች የቦታ ቅጥ መገኘት እና አዳራሽ ክሊኒክ ሞዴልን ማሳየት መቻሉ በግሎባል ደቡብ የሩቅ እና የገጠር ክልልሎች ለተመሳሳይ ተጨማሪ አገልግሎቶች እና ተያያዥ የፖሊሲ ማእቀፎች አስፈላጊነት አሳማኝ መከራከሪያ ያቀርባል፡፡


በዩጋንዳ የእረስ በእርስ ጦርነት እጅ እና እግራቸውን ያጡ ተጎጂዎች እስካሁን ድረስ እርዳታ አላገኙም

 ለመጀመሪያ ጊዜ ተመራማሪዎች በሰሜን ዩጋንዳ በአቾሊ ክፍል ሃገር ውስጥ ዋና እጅና እግር ማጣት (ዋ.እ.እ.ማ) እና ሌላ የአካል ጉዳቶች የደረሱባቸውን ሰዎች ዳሰሱ፡፡

መረጃውን መንግስት እና ሌሎች ተቋማት ሰዎች ክሊኒካዊ አገልግሎቶችን በጣም በሚፈልጉባቸው ቦታዎች ላይ አገልግሎት ለመስጠት ይጠቀሙበታል ብለው ተስፋ ያደርጋሉ፡፡

 በሰሜን ዩጋንዳ የሚገኘው የአቾሊ ክፍለ ሃገር ለ20 አመታት የቆየ የእርስ በእርስ ጦርነት ሰለባ ሲሆን ጦርነቱ እ.ኢ.አ በ2005 ዓ.ም አብቅቷል፡፡

በጦርነቱ ብዙ ሰዎች እጅ እና እግራቸውን ያጡ ሲሆን ክልሉ እንደደኸየ ቀርቷል፡፡

በሚያሳዝን ሁኔታ የአካባቢው መንግስት እና አለምአቀፍ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እስካሁን ድረስ በአካባቢው ምን ያህል ሰዎች ከባድ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው እና የህክምና ወይም የመልሶ መቋቋም አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉ በቅጡ አያውቁም፡፡

 ይህ በአቾሊ ክፍለ ሃገር የዋ.እ.እ.ማ መስፋፋትን ለመመርመር የተደረገ የመጀመሪያው ጥናት ነው፡፡

ይሄ ጥናት የተዘረጋው በዚህ የሰሜን ዩጋንዳ ክልል በህዝቡ ውስጥ የሚገኙትን የተለያዩ የአካል ጉዳት አይነቶችን እና ዋና እጅና እግር ማጣትን ለመዘገብ ነው፡፡ በተጨማሪም ለመንግስት እና ለሌሎች ድርጅቶች የጤና ተቋማት በተለይ የት ቦታ እንደሚያስፈልጉ የሚጠቁም ካርታ ለመስጠት ነው፡፡

 ተመራማሪዎቹ በጥናት ክልል ውስጥ በዘፈቀደ ከተመረጡ 7864 ቤቶች ለሰዎች ቃለ ምልልስ ያደረጉ ሲሆን፣ የእያንዳንዱን ቤት ሃላፊ እና 181 የዋ.እ.እ.ማ ታማማዊዎችን ከሁለቱ አንዱን ቃለመጠይቅ እንዲመልሱ ጠይቀዋቸዋል፡፡

የሁሉንም ቤት መገኛ መዝግበዋል፡፡ የ ሞራን አይ ስታስቲካል ዘዴን በመጠቀም ዋ.እ.እ.ማ በተለይ የት እንደተስፋፋ እና አገልግሎቶች በብዛት የት ቦታ እንደሚያስፈልጉ ለማወቅ ተጠቅመውበታል፡፡

 ተመራማሪዎቹ ሁሉንም ቤት እየዞሩ መጎብኘት ስላልቻሉ መላውን ህዝብ ይወክላለሉ ብለው ያሰቧቸውን የቤት ናሙናዎች መምረጥ አስፈልጓቸው ነበር፡፡

የዋ.እ.እ.ማ ታማሚዎች ያሉባቸው ቤቶች የቀረውን ህዝብ በሚገባ እንደሚወክሉ ለማረጋገጥ፣ “ቺ ካሬ (X^2) የብቃት ጥሩነት” የተባለ የስታትስቲክስ ዘዴን ተጠቅመዋል፡፡

 ተመራማሪዎቹ በግምት ከህዝቡ 0.5% የሚሆኑት የዋ.እ.እ.ማ ሰለባዎች እንደሆኑ እና የረጅም ጊዜ የመልሶ ማቋቋም አገልግሎት እንደሚያስፈልጋቸው አስልተዋል፡፡

በተጨማሪም 8.2% የሚሆኑት እና እዛ የሚኖሩት ሰዎች ሌላ የአካል ጉዳቶች እንዳለባቸው አግኝተዋል፡፡

 ጥናቱ የዋ.እ.እ.ማ ታማሚዎች በክልሉ ተሰራጭተው እንደሚገኙ እና በተወሰኑ ቦታዎች ላይ እንዳልተወሰኑ ይጠቁማል፡፡

ብዙ የዋ.እ.እ.ማ ታማሚወች በአብዛኛው ወንድ እና በእድሜ የገፉ እና ከመላው ህዝብ ጋር ሲወዳዳር ዝቅተኛ የትምህርት ደረጃ ያላቸው ናቸው፡፡

በአቾሊ ክፍለ ሃገር ግጭቱ ያበቃው ከ15 ዓመት በፊት ቢሆንም እነዚህ ውጤቶች የዋ.እ.እ.ማን መስፋፋት በስርአቱ ለመገመት የመጀመሪያወቹ ናቸው፡፡

በሚያሳዝን ሁኔታ፣ ተመራማሪዎቹ ከ5 አመት በላይ በሆነው የህዝብ ቆጠራ መረጃ ላይ መተማመን ነበረባቸው፡፡ እያደገ ለመጣው የስደተኞች ቁጥር መረጃ አልነበራቸውም፡፡

 እነዚህ ገደቦች ቢኖሩም፣ ይህ ዳሰሳ በአቾሊ ክፍለ ሃገር ያሉ የመልሶ መቋቋሚያ አገልግሎቶች ዋና እጅና እግር ማጣጥ ሰለባ የሆኑ ሰዎችን መርዳት እንድላቻሉ ያሳያል፡፡

ተመራማሪዎቹ ለመንግስት እና አለም አቀፍ ድርጅቶች መረጃ የሚሰጠውን አዲስ ክሊኒዊ አዳራሽ ሞዴልን ይመክራሉ፡፡ይህም የመልሶ ማቋቋም አገልግሎታቸው በጣም ጠቃሚ የሚሆነው የት እንደሆነ ይገልጻል፡፡

በተጨማሪ በግሎባል ደቡብ እና ሌሎች በጦርነት በወደሙ የገጠር ክልሎች የመልሶ ማቋቋም አግልግሎቶቹ ሊያስፈልጉ ይችላሉ ይላሉ፡፡

Connections
1 of 5
Comments
0
comment
No comments here
Why not start the discussion?