Description
This is a lay summary of the article published under the DOI: 10.1101/2020.11.28.20240267
Amharic translation of DOI: 10.1101/2020.11.28.20240267
የኮሮና ቫይረስ በሽታ 19 (ኮቪድ-19) ወረርሽኝ በአለም ዙሪያ በፍጥነት እየተስፋፋ እና ከፍተኛ ጉዳት እና ሞት እያደረሰ ይገኛል፡፡
ከኮቪድ-19 ጋር የተጓዳኝ-በሽቶች አብሮ መገኘት በተደጋጋሚ አመርቂ ያልሆነ ትንበያ የማቅረብ አደጋ ምንጭ እንደሆነ ሪፖርት ተደርጓል፡፡
በዚህ ጥናት ለኮቪድ-19 ታማሚዎች የብዙ ጊዜ የሆስፒታል ቆይታ፣ ወደ አይሲዩ የመግባት ወይም የመሞት ውጤቶች ላይ የተጓዳኝ-በሽቶችን ተጽእኖ እና ወሳኝ የሆኑትን ምክንያቶች ለመገምገም አቅደናል፡፡
በዚህ ጥናት አራት መቶ ሰላሳ ዘጠኝ (በጁን እና በጁላይ 2020) ወደ አስዊት እና አስዋን ዩንቨርስቲ ሆስፒታሎች የገቡ አዋቂ ታማሚዎች ተካተዋል፡፡
በግብጽ የጤና ሚንስቴር ድጋፍ መሰረት ሁሉም ተሳታፊዎች በኮቪድ-19 በእርግጠኝነት ወይም በሊሆን ይችላል ኬዝ መያዛቸው ታውቋል፡፡
ሳርስ-ኮቫ-2 አርኤንኤን ለይቶ የማወቅ ስራ የተሰራው በ (TaqMan™ 2019-nCoV የመቆጣጠሪያ ኪት v1 (Cat. ቁ. A47532) ሲሆን፣ የተከፋፈለው ደግሞ በ QIAGEN ጀርመን በተተገበረው የባዮ ሲስተም 7500 ፈጣን ቅ.ቅ ፖ.ሰ.ም ሲስተም ዩናይትድ ስቴትስ ነው፡፡
ተጓዳኝ-በሽቶች ያሏቸው ታማሚዎች ከሁሉም ክስተቶች 61.7% የሚያክለውን ይወክላሉ፡፡
ተጓዳኝ-በሽቶች(P < 0.05) ያሏቸው ታማሚዎች ላይ በተለይም ምያልጊያ እና LRT እንዲሁም ዲስፕኒአ የመሰሉ ኮንስቲቲዩሽናል ምልክቶች በጣም ከፍተኛ ነበሩ::
ተጓዳኝ-በሽቶች ያሏቸው ታማሚዎች ሊታይ በሚችል መልኩ አስከፊ የላብራቶሪ ፓራሜትሮች ነበሯቸው፡፡
ተጓዳኝ-በሽቶች ያሏቸው ታማሚዎች ወደ አይሲዩ የመግባት አድላቸው ከፍተኛ ነበር (35.8%)
ከተለያዩ ተጓዳኝ-በሽቶች መካከል 45.4% የሚሆኑት ከም.ሞ ክስተቶች በመቀጠል የስ.ል.ወ.በ ክስተቶች ወደ አይሲዩ እንዲገቡ ተደርገዋል (40.8%)::
በተጨማሪም፣ ተጓዳኝ-በሽቶች ከሌላቸውታማሚዎች ጋር ሲነጻጸሩ (31 vs.10.7%, P<0.001). ተጓዳኝ-በሽቶች ያሏቸው ታማሚዎች ኢንቬሲቭ ሜካኒካዊ የአየር ማናፈሻ አስፈልጓቸው ነበር፡፡
ጉልህ በሆነ መልኩ ተጓዳኝ-በሽቶች ባሏቸው የኮቪድ-19 ታማሚዎች ላይ አነስተኛ የማገገም ፍጥነት የታየ ሲሆን (59% vs.81%, P<0.001) የሞት መጠን ደግሞ በተለይ ተጓዳኝ-በሽቶች ባሏቸው ኬዞች ላይ ከፍተኛ ነበር (P< 0.001)፡፡
ከዚህ ቀደም CVD እና የኒውሮሎጂካዊ በሽታዎች ባሉባቸው ኬዞች የማገገም ሁኔታ በሽታ ከሌለባቸው ሰዎች ጋር ሲነጻጸር አነስተኛ ነበር፡፡ (ይህም በቅደም ተከተል P<0.002 እና 0.001 ነው፡፡)
ከፍተኛ የደም ግፊት ወይም ኒዩሮሎጂካዊ በሽታዎችን ጨምሮ የስርአተ ልብ ወቧንቧ ተጓዳኝ-በሽታ ክስተቶች ከኮቪድ-19 ኢንፌክሽኖች ጋር እንድ ላይ ሲከሰቱ የመሞት እድልን ይጨምራሉ፡፡
ነገር ግን እንደ ስኳር በሽታ፣ ስር የሰደደ ፕልሞናሪ ወይም የኩላሊት በሽታዎችን የመሰሉ ሌሎች ተጓዳኝ-በሽቶች ለኮቪድ-19 መባባስ አስተዋጽኦ ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡
ይሄ ጥናት ሪፖርት እንዳደረገው እንደ ከፍተኛ የደም ግፊት፣ የስኳር በሽታ፣ የሳንባ፣ የኩላሊት እና የልብ በሽታ አይነት ሌሎች በሽታዎች ያሉባቸው የኮቪድ-19 ታማሚዎች የከፉ በሽታዎችን የመታመም አደጋቸው የበለጠ ከፍተኛ ስለሆነ በሆስፒታሎች ውስጥ ለየት ያለ እንክብካቤ አስፈልጓቸው ነበር፡፡
በጥቅሉ ከአንድ በላይ በሽታ ወይም ኮንዲሽን ያላቸውን ታማሚዎች ማከም ከባድ እና ውድ ነው፡፡
እነዚህ ሌሎች ወይም ተጓዳኝ በሽታዎች በአጠቃላይ ተጓዳኝ-በሽቶች ይታወቃሉ፡፡
ተጓዳኝ-በሽቶች ባሏቸው ታማሚዎች ላይ ኮቪድ-19ም እንደሚባባስ ዶክተሮቹ ሪፖርት ያደርጋሉ፡፡
በ2020 የጀመረው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በአለም ዙሪያ ብዙ ሰዎችን የገደለ ሲሆን፣ ሆስፒታሎች በጣም ከፍተኛ አደጋ ላይ ለነበሩ ታማሚዎች የአይሲዩ እና የአልጋ እጥረት ነበረባቸው፡፡ እጥረት ነበረባቸው፡፡
በዘህም ምክንያት ዶክተሮቹ በአስቸኳይ ወደ አይሲዩ መግባት ያለባቸውን ታማሚዎች በፍጥነት ለይተው የሚያውቁበትን መንገድ እየፈለጉ ነበር፡፡
በዚህ ጥናት ተመራማሪዎች ተጓዳኝ-በሽቶች በኮቪድ-19 ታማሚዎች ላይ በእርግጠኝነት ምን አይነት ተጽእኖዎችን እንደሚያደርሱ መርምረዋል፡፡
በተጨማሪም ታማሚዎች ለረጅም ጊዜ ሆስፒታል ውስጥ እንዲቆዩ፣ ወደ አይሲዩ እንዲገቡ ወይም በኮቪድ-19 እንዲሞቱ ሊዳርጓቸው የሚችሉትን ምክንያቶች ፈትሸዋል፡፡
ተመራማሪዎቹ በግብጽ በሚገኙት 2ቱ ትልልቅ ሆስፒታሎች ውስጥ ለህክምና የገቡትን የኮቪድ-19 ታማሚ አዋቂዎች የቃኙ ሲሆን፣ የጤና ረኮርዳቸውን፣ የህዝበ ነክ ጥናት መረጃቸውን እና የላብራቶሪ እና የደረት ኤክስሬይ (ራጅ) ውጤታቸውን ፈትሸዋል፡፡
በተጨማሪም ታማሚዎቹ ሙሉ በሙሉ ማገገማቸውን፣ አይሲዩ እንዲገቡ መደረጋቸውን ወይም መሞታቸውን ሪኮርድ አድርገዋል፡፡
ተመራማሪዎቹ ተጓዳኝ-በሽቶች ያሏቸውን ታማሚዎች ከሌላቸው ታማሚዎች ጋር አወዳድረዋል፡፡
ጥናቱ እንዳገኘው የልብ እና የስኳር በሽታዎች ዋነኞቹ ሆነው ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ተማሚዎች ተጓዳኝ-በሽቶች ነበሩባቸው፡፡
ተጓዳኝ-በሽቶች ያሉባቸው ታማሚዎች የከፋ የላብራቶሪ ውጤቶች የነበራቸው ሰሆን፣ ከኮቪድ-19 የማገገም አድላቸው እጅግ አነስተኛ ነበር፡፡
በተጨማሪ ተጓዳኝ-በሽቶች ያሏቸው ታማሚዎች በተለየም የልብ እና የስኳር በሽተኞች ወደ አይሲዩ የመግባት እድላቸው እጅግ ከፍተኛ ከመሆኑ ባሻገር መተንፈስ እንዲችሉ እገዛ አስፈልጓቸው ነበር፡፡
ውጤቶቹ በተለይም በእድሜ የገፉ ሰዎች በኮቪድ-19 የመሞት እድላቸው ከፍተኛ እንደሆነ አሳይተዋል፡፡
እዚህ ከተጠኑት ተጓዳኝ-በሽቶች ሁሉ ተመራማሪዎቹ እንዳገኙት ፣የልብ ህመም፣ ከፍተኛ የደም ግፊት እና የስኳር በሽታ በጣም አስጊዎቸ ነበሩ፤ ከእድሜ መግፋት ወይም ከማርጀት ጋርም ተያይዘዋል፡፡
ተመራማሪዎቹ በስኳር በሽታ እና በኮቪድ-19 በሽተኞች መሞት ላይ ምንም አይነት ግንኙነት አላገኙም፡፡
ከዚህ በፊት የተደረጉ ጥናቶች የተጓዳኝ በሽቶች ተጽእኖ ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮችን ሪፖርት ያደረጉ ሲሆን፣ ይሄ ጥናት ብዙ ተጓዳኝ-በሽቶች የኮቪድ-19 በሽታ አደጋን እንደሚጨምሩ እና ለከፉ ውጤቶች እንደሚዳርጉ አረጋግጧል፡፡
ተመራማሪዎቹ የዚህ ጥናት ውጤቶች የተገደቡ ሊሆኑ እንደሚችሉ ይገልጻሉ፤ ለዚህም ምክንያቱ ከታማሚዎቻቸው ስር የሰደደ ጨጓራ፣ ኩላሊት፣ ገንባፍርስ፣ ኒዮሮሎጂካዊ፣ ዝግ እጢ እና አውቶኢሚዩን ተጓዳኝ-በሽቶች የነበራቸው አነስተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች መሆናቸው ነው፡፡
በጥናቱ ወቅት በህክምና ፕሮቶኮል፣ በቅበላ ፖሊሲ እና በሆስፒታል ሪኮርዶቹ ላይ የተወሰኑ አለመጣጣሞችን እንዳስተዋሉ የገለጹ ሲሆን ይህም ውጤቶቹ ላይ ተጽእኖ አድርጎ ሊሆን ይችላል ብለዋል፡፡
ተመራማሪዎቹ በተጨማሪም የአንዳንድ ታማሚዎች ውጤት በግልጽ ሳይታወቅ ጥናቱ እንደተጠናቀቀ ገልጸዋል፡፡
ተመራማሪዎቹ በዛ ያሉ ታማሚዎችን በመጠቀም ሰፋ ያሉ የተጓዳኝ-በሽቶች ዝርያዎችን እና ረዘም ያሉ የጥናት ጊዜዎችን አካቶ የበለጠ ምርምር ማድረግ እንደሚያስፈልግ ይመክራሉ፡፡
Zulu translation of DOI: DOI: 10.1101/2020.11.28.20240267
Yoruba translation of DOI: 10.1101/2020.11.28.20240267
Northern Sotho translation of DOI: 10.1101/2020.11.28.20240267