Description
This is a lay summary of the article published under the DOI: 10.1101/2021.02.05.21250735
Amharic translation of DOI: 10.1101/2021.02.05.21250735
ተለይተው ያልታወቁት የሳርስ-ኮቫ-2 ኢንፌክሽኖች በ ከፍተኛ መጠን መገኘት በኬኒያ የወረርሽኙን እድገት ለመከታተል እና የቁጥጥር እርምጃዎችን ለመውሰድ ፈታኝ ሁኔታ ነው፡፡
በኬኒያ 2 የሪፈራል ሆስፒታሎች የቅድመ ወሊድ እንክብካቤ አገልግሎት እያገኙ ካሉ እናቶች ከተወሰዱ ቀሪ የደም ናሙናዎች የ IgG እና የሳርስ-ኮቫ-2 መስፋፋትን አግኝተናል፡፡
የተረጋገጠ የ IgG ELISA ለሳርስ-ኮቫ-2 ዛላ ፕሮቲን የተጠቀምን ሲሆን የንጥረተ ጥናት ትብነትን እና ልዩነትን ለማወቅ ውጤቱን አስተካክለናል፡፡
በኬኒያታ ናይራሮቢ ብሄራዊ ሆስፒታለ በኦገስት 2020 የሲሮ መስፋፋት 49.9% ነበር(95% CI 42.7-58.0 )::
በኪሊፊ አውራጃ ሆስፒታል የሲሮ መስፋፋት ከ1.3% (95% CI 0.04-4.7) በሴፕቴምበር ወደ 11.0% (95% CI 6.2-16.7) በኖቬምበር 2020 አድጓል፡፡
በአንዳንድ የናይሮቢ እና የኪሊፊ አውራጃዎች ጉልህ የሆነ እና ያልተየ የሳርስ-ኮቫ-2 ስርጭት ነበር፡፡
ተመራማሪዎች እንደሚዘግቡት በ2021 በኬንያ ከበርካታ ነፍሰጡር ሴቶች የተወሰዱ ናሙናዎች ውስጥ ኮቪድ-19ን የሚያመጣው ቫይረስ ፀረ እንግዳ አካላት በውስጣቸው ተገኝቷል፡፡
ይህ ማለት ከዛሬ ቀደም ኢንፌክት ተደርገው ወይም በጊዜው ተበክለው ነበር፤ ነገር ግን ብዙዎቹ ኢንፌክሽኖች በፖሊመሬዝ ሰንሰለት ምላሽ (ፖ.ሰ.ም) የሙከራ ውጤቶች ውስጥ አልተገኙም ነበር፡፡
ተመራማሪዎቹ እንደሚሉት በዚህም ምክንያት በኬኒያ የኮቪድ-19 መስፋፋት ከሆነው በታች ዝቅተኛ ግምት ተሰጥቶት ነበር፡፡
በጥቅሉ መንግስታት የቁጥጥር እና የህክምና እርምጃዎችን ለመተግበር ምን ያህል ሰዎች የበሽታው ተጠቂ እንደሆኑ የሚገልጽ ትክክለኛ መረጃ ይፈልጋሉ፡፡
ነገር ግን ኬኒያ ውስጥ ብዙ ሰዎች ለኮቪድ-19 ምርመራ አልሄዱም ነበር፡፡
ይህ የሆነበት ምክንያት ህብረተሰቡ በአንጻሩ ብዙ ወጣቶች ስላሉት እና አብዛኛው ሰው መለስተኛ ምልክቶች ወይም ምንም የበሽታ ምልክቶችን ስላላሰየ ሊሆን ይችላል፡፡
ሳይንቲስቶች እንደሚሉት የሳርስ-ኮቫ-2 የፀረ እንግዳ አካላት መስፋፋትን መለካት አጠቃላይ ኢንፌክሽኑን ለመገመት አንዱ መንገድ ነው፡፡
ፀረ እንግዳ አካላት ለተለያዩ በሽታዎች ምላሽ ለመስጠት በሰውነት ውስጥ የሚመረቱ የተወሰኑ ፕሮቲኖች ሲሆኑ መኖራቸው የሚጠቁመው አንድ ሰው ከዛሬ በፊት ለበሽታው ተጋልጦ እንደነበረ ወይም ኢንፌክት እንደተደረገ ነው፡፡
በዚህ ጥናት ተመራማሪዎቹ በኬኒያ በኪሊፊ እና በናይሮቢ በ2 ሆስፒታሎች ውስጥ ባሉ ነፍሰጡር ሴቶች የሳርስ-ኮቫ-2 ረ ፀረ እንግዳ አካላት ተንሰራፍተው እንደሚገኙ ጠቁመዋል፡፡
ከሴቶቹ የደም ናሙናዎች ውስጥ የሳርስ-ኮቫ-2 ፀረ እንግዳ አካላትን መርምረዋል፡፡
በእነዚሁ አካባቢዎች ከጤና ሚኒስተር ያገኟቸውን በፖ.ሰ.ም የተረጋገጡ የሳርስ-ኮቫ-2 ኢንፌክሽኖችን ካገኟቸው አሉታዊ የናሙና መጠኖች ጋር አወዳድረዋል፡፡
ተመራማሪዎቹ በተጨማሪ የጤና ሪኮርዶችን ገምግመው ናሙናዎቹ መቼ እንደተሰበሰቡ እና እድሜያቸውን፣ መገኛቸውን፣ የእርግዝና ወቅት አና የኮቪድ-19 ምልክቶች መኖር አለመኖራቸውን ዘግበዋል፡፡
በናይሮቢ ግማሾቹ ናሙናዎች ለሳርስ-ኮቫ-2 ፀረ እንግዳ አካላት አሉታዊ ውጤት ያስመዘገቡ ሲሆን በኪሊፊ ደግሞ 1.3% እና 10% አስመዝግበዋል፡፡
በሁለቱም አካባቢዎች በፖ.ሰ.ም የተረጋገጡ ኢንፌክሽኖች ከ1% ያነሱ ነበሩ፤ ይህም የሚያሳየው የኢንፌክሽኑ እውነተኛ ቁጥር ከነበረው ቀንሶ እንደተዘገበ ነው፡፡
በተጨማሪም 7% የሚሆኑት ሴቶች ብቻ ከኮቪድ-19 ጋር የተያያዙ ምልክቶችን ሪፖርት ያደረጉ ሲሆን፣ ይህ ማለት ብዙዎቹ ኢንፌክሽኖች ምንም ምልክት የሌለባቸው ነበሩ፡፡
ተመራማሪዎቹ የሳርስ-ኮቫ-2 ፀረ እንግዳ አካላት ምርመራዎችን ማድረግ በኬኒያ ኢንፌክት የተደረጉ ሰዎችን ትክክለኛ ቁጥር ለማወቅ ይረዳል ብለው ይመክራሉ፡፡
ነገር ግን ስም አልባ መረጃ እንደተጠቀሙ እና በዚህም ምክንያት ግኝቶቻቸውን ከሌሎች ምንጮች ጋር ማወዳደር እንዳልቻሉ ያሳስባሉ፡፡
ተመራማሪዎቹ አጠቃላይ የኢንፌክሽን ቁጥርን ለመገመት ወሳኝ የሆነው የፀረ እንግዳ አካላት ማጣት ላይ መረጃ ማግኘት እንዳልቻሉ ገልጸዋል፡፡
ይህጥናትበኬኒያፀረእንግዳአካላትንተጠቅሞሳርስ-ኮቫ-2ን የመቆጣጠርየሌላትልቅፕሮግራምአካልሲሆንየተመራውምበKEMRI ዌልካምትረስትየምርምርፕሮግራምነው፡፡
Hausa translation of DOI: 10.1101/2021.02.05.21250735
Luganda translation of DOI: 10.1101/2021.02.05.21250735
Northern Sotho translation of DOI: 10.1101/2021.02.05.21250735