Skip to main content
SearchLoginLogin or Signup

በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት ለእንስሳት ህክምና ተማሪዎች የተሻለ የኦንላይን ወይም የመስማር ላይ አስተምሮ

Amharic translation of DOI: 10.20944/preprints202006.0130.v2

Published onOct 02, 2023
በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት ለእንስሳት ህክምና ተማሪዎች የተሻለ የኦንላይን ወይም የመስማር ላይ አስተምሮ
·

የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በእንስሳት ህክምና ተማሪዎች የትምህርት አወሳሰድ ጥራት ላይ ያለው ተጽእኖ

Abstract

ብዙ በአለም ዙሪያ የሚገኙ ዪንቨርስቲዎች እና ኮሌጆች በኖቭል ኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በክፍል ውስጥ ትምህርት መስጠት ያቆሙ ሲሆን ወደ ኦንላይን ወይም የመስመር ላይ ትምህርት ተዘዋውረዋል፡፡

የአሁኑ ሰፊ የክፍል በክፍል ጥናት የተካሄደው  በኮሮና ቫይረስ በሽታ 2019  (ኮቪድ-19) ምክንያት በተደረገው የእንቅስቃሴ እገዳ የእንስሳት ህክምና ተማሪዎች እና ተመራማሪዎች የትምህርት አወሳሰድ ጥራት ላይ ያደረሰውን ተጽእኖ ለመገምገም ነው፡፡

የእንስሳት ህክምና ተማሪዎች እና ተመራማሪዎች የኦን ላይን ወይም የመስመር ላይ የጎግል መጠይቅ ፎርም እንዲሞሉ ተጋብዘው ነበር፡፡

በአጠቃላይ ከ92 የተለያዩ ሃገሮች 1398 ተሳታፊዎች በ94.52% መልስ የመስጠት ምጥነት ለመጠይቁ መልስ ሰጥተው ነበር፡፡

መረጃው እንዳሳየው የኮቪድ-19 የእንቅስቃሴ እገዳ የአብዛኛዎቹ ተሳታፊዎች የትምህርት አወሳሰድ ጥራት ላይ በተለያየ መጠን ተጽእኖ አድርጓል (96.7%)፡፡

ለኦንላይን ወይም ለመስመር ላይ ትምህርት አማካይ የግምገማ ውጤቱ በጥቅሉ 5.06 ± 2.43 ሲሆን በተግባር ላይ ለዋሉት ክፍሎች ደግሞ፣ 3.62± 2.56 ነበር፡፡

የኦንላይን ትምህርት በእራስ ለመማር አድሉን ቢከፍትም ፡፡

በእንስሳት ህክምና ሳይንስ ውስጥ የኦንላይን ወይም የመስመር ላይ ትምህርት የሚያጋጥመው ዋና ተግዳሮት የተግባር ትምህርት እንዴት መስጠት እንደሚችል ነው፡፡

አብዛኛዎቹ የትምህርቱ ርዕሰ ጉዳዮች ተግባራዊ በመሆናቸው ኦንላይን ወይም መስመር ላይ ለመማር ቀላል አይደሉም፡፡

ተማሪዎቹ የእንስሳት ህክምና የብቃት ማረጋገጫዎችን በኦንላይን ወይም በመስመር ላይ የትምህርት ሲሰተም ብቻ ማሟላት ይከብዳል ብለው ያስባሉ ፡፡

የኦንላይን ወይም የመስመር ላይ ትምህርትን ለማሻሻል፣ የበለጠ የእርስ በእርስ ግንኙነቶችን በመጨመር፣ የህክምና ሂደቶችን በአውነተኛ አጋጣሚዎች በማሳየት፣ ግልጽ እና ጥርት ያለ መረጃ በመስጠት እና ከእውነተኛ አጋጣሚዎች ጋር የሚመሳሰሉ የ3ዲ ምናባዊ መሳሪያዎችን ማቅረብ ጥሩ ይሆናል፡፡


በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት ለእንስሳት ህክምና ተማሪዎች የተሻለ የኦንላይን ወይም የመስማር ላይ አስተምሮ

የትምህርት ዘርፉ በተግባር እየሰሩ መማርን ስለሚጠይቅ ለእንስሳት ህክምና ሳይንስ ተማሪዎች እና ተመራማሪዎች በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት በኦንላይን መማር ከባድ ነበር፡፡

ይህ ጥናት ያጋጠሟቸውን ልዩ ቨርቹዋል ተግዳሮቶች እና መፍትሄዎቻቸውን ለይቶ አውጥቷል፡፡

በአለም ዙሪያ ያሉ  ዩኒቨርሲቲዎች በወረርሽኙ ወቅት የኮቪድ-19 መስፋፋትን ለመቀነስ ወደ ኦንላይን ወይም የመስመር ላይ ክፍለ  ጊዜዎች ተዘዋወሩ፡፡

በተለየም አነስተኛ ኢንተርኔት የማግኘት እድል ያላቸው ብዙ ተማሪዎች አሉታዊ ተጽእኖ ደርሶባቸው ነበር፡፡

ጥናቱ በአለም ዙሪያ እንዴት የኦንላይን ትምህርት የእንስሳት ህክምና ተማሪዎች ላይ ተጽእኖ እንዳደረገ መጠይቅን በመጠቀም ለማወቅ ፈልጎ ነበር፡፡

በተጨማሪም ተመራማሪው ለእነዚህ ተግዳሮቶች መፍትሄ ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮችን ለማወቅም ፈልጎ ነበር፡፡

ከተሳታፊዎቹ የህዝበ ነክ ጥናቶች እና የኦንላይን ትምህርት በትምህርት አወሳሰዳቸው ላይ ካለው ተጽእኖ ጋር የተያያዙ ጥያቄዎችን የያዘ ስም አልባ የኦንላይን መጠይቅ አዘጋጅተው ነበር፡፡

ተመራማሪው ጥቅም ላይ ሰለዋሉት የመማሪያ መሳሪያዎች፣ በቀን ውስጥ በኦንላይን ወይም በመስመር ላይ ትምህርት የሚጠፋውን ጊዜ፣ የኦንላይን ወይም የመስመር ላይ ትምህርት ተግባራዊ እና ቀመራዊ የሆኑ የትምርት አይነቶች ላይ ያለውን ተጽእኖ እና በኦንላይን ወይም በመስመር ላይ ትምህርት ጊዜ ስለሚከሰቱ ችግሮች ጥያቄዎችን ጠይቋል፡፡

ተሳታፊዎቹም መፍትሄ ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮችን ጠቁመዋል፡፡

ከ92 ሃገራት ከመጡት 1398 ተሳታፊዎች ግማሽ የሚሆኑት የትምህርት አወሳሰድ ጥራታቸው በወረርሽኙ ምክንያት ከፍተኛ ተጽእኖ እንደደረሰበት ገልጸዋል፡፡

ተመራማሪው ለእንስሳት ህክምና ተማሪዎች በኦንላይን መማር የተወሰኑ ጥቅሞች እንዳሉት ያገኘ ሲሆን ነገር ግን ኢንተርኔት ከማግኘት ጋር፣ የኦንላይን መረጃዎችን ከማግኘት ጋር እና ከአንዳንድ የትምህርቱ ርዕሰ ጉዳዮች ተግባራዊ ባህሪ ጋር ተያይዘው የሚመጡ ብዙ ተግዳሮቶች ነበሩ፡፡

ጥናቱ ተማሪዎች የበለጠ የእርስ በእርስ ግንኙነትን የሚያጠናክሩ መሳሪያዎች እንደሚያስፈልጓቸው እና ተግባራዊ ለሆኑት የትምህርቱ ርዕሰ ጉዳዮች ደግሞ እርስበራሳቸው እና ከአስተማሪዎቻቸው ጋር የበለጠ ግንኙነት ማድረግ እንዳለባቸው ሃሳብ ያቀርባል፡፡

ሌሎች ጥናቶች ወረርሽኙ እንዴት የሌሎች የህክምና ተማሪዎችን ትምህርት እንዳስተጓጎለ እና የእንስሳት ህክምና ባለሞያዎች እንዴት አሉታዊ ተጽእኖ እንደደረሰባቸው አጉልተው አሳይተዋል፡፡

እዚህ የቀረቡት መፍትሄዎች በተለይም ተግባራዊ ለሆኑት ሁሉም የመስክ የትምህርት አይነቶች የኦንላይን አስተምሮ እንዴት ለወደፊቱ መሻሻል እንደሚችል እነዛ ጥናቶች ላይ አክለው ይሰራሉ፡፡

ነገር ግን ተመራማሪው የዳሰሳ ጥናቱ በቂ ግብአት እንደሌለው ጠቁሟል፤ ይህም አንዳንድ ሃገሮች በሚገባ እንዳይወከሉ አድርጓል፡፡

ከዚህጥናትጀርባየነበረውተመራማሪየተመሰረተውግብጽላይነበር፡፡

Connections
1 of 5
Comments
0
comment
No comments here
Why not start the discussion?