Skip to main content
SearchLoginLogin or Signup

በህክምና ላይ ያሉ የኤችአይቪ ፖዘቲቭ ሰዎች ከሰፊው ህብረተሰብ ጋር ሲነጻጸር የኮቪድ-19 ከባድ ምልክቶችን የማሰየት እና በበሽታው የመሞት እድላቸው አነስተኛ ነው፡፡

Amharic translation of DOI: 10.1101/2020.06.04.20122606

Published onJun 17, 2023
በህክምና ላይ ያሉ የኤችአይቪ ፖዘቲቭ ሰዎች ከሰፊው ህብረተሰብ ጋር ሲነጻጸር የኮቪድ-19 ከባድ ምልክቶችን የማሰየት እና በበሽታው የመሞት እድላቸው አነስተኛ ነው፡፡
·

የኮቪድ-19 እና የኤችአይቪ የጋራ-ኢንፌክሽን: 

የአሁኑ ምርምር ሕያው ስልታዊ ማስረጃ ካርታ

አለም በአሁኑ ጊዜ ሁለት አስከፊ ወረርሽኞችን እየተጋፈጠች ትገኛለች፡፡

እነዚህም፣ አዲሱ ከባድ አጣዳፊ የመተንፈሻ አካላት ድምረ ህመም ኮሮና ቫይረስ 2/የኮሮና ቫይረስ በሽታ 2019 (ሳርስ-ኮቫ-2/ ኮቪድ-19) እና የበፊቱ ሂዩማን ኢሚዮኖ  ዴፊሸንሲ ቫይረስ/ አኳየርድ ኢሚዩን ዴፊሸንሲ ድምረ ህመም (ኤችአይቪ/ኤድስ) ወረርሽኞች ናቸው፡፡

የእነዚህን አለም  አቀፋዊ መቅሰፍቶች ውህደት የሚመለከቱ ጽሁፎች በፍጥነት እየተስፋፉ ይገኛሉ፡፡

ኮቪድ-19 እና ኤችአይቪ የጋራ-ኢንፌክሽንን አስመልክተው ያሉ ጽሁፎች ዙሪያ ስልታዊ ፍለጋ ተካሂዷል፡፡

የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከጀመረ ከ አምስት ወሮች  በኋላ ቢያንስ ከ አስራ ሶስት ሃገሮች ሰላሳ አምስት ጥናቶች ሪፖርት ተደርገው ነበር፡፡

እነዚህም ጥናቶች ከተናጥል የጉዳይ ሪፖርቶች እስከ ተከታታይ እና ጥምር ጥናቶች ድረስ አካተዋል፡፡

በመላው ህብረተሰብ ላይ ሊተገበሩ በሚችሉ ጥናቶች መሰረት፣ የተጨቆነ የኤችአይቪ ቫይረስ ጭነት ያሏቸው እና የጋራ-ኢንፌክሽን ተጠቂ የሆኑ ግለሰቦች ያልተመጣጠነ የኮቪድ-19 ህመም እና ሞት አላጋጠማቸውም፡፡

በኤችአይቪ የተያዙ ቢያንስ አዲስ አራት ታማሚዎች ከኮቪድ-19 አገግመዋል፡፡

አሁን ያለው መረጃ እንደሚያመለክተው የጋራ- ኢንፌክሽን ተማማዊች ልክ እንደ ሰፊው ህብረተሰብ መታከም አለባቸው፡፡

ይህ ቀጣዩ ሕያው ስልታዊ ማስረጃ ካርታ የወቅቱ አንደኛ ደረጃ የሳርስ-ኮቫ-2 እና የኤችአይቪ የጋራ- ኢንፌክሽን ምርምር ለተመራማሪዎች፣ ለፖሊሲ አውጪዎች፣ ለክሊኒክ ባለሞያዎች እና ለሌሎችም ተገቢ ግንዛቤዎችን በፍጥነት እንዲያገኙ እና እንዲገነቡ መድረክ ይከፍታል፡፡


በህክምና ላይ ያሉ የኤችአይቪ ፖዘቲቭ ሰዎች ከሰፊው ህብረተሰብ ጋር ሲነጻጸር የኮቪድ-19 ከባድ ምልክቶችን የማሰየት እና በበሽታው የመሞት እድላቸው አነስተኛ ነው፡፡

በአለም ዙሪያ የተደረጉ ብዙ ጥናቶች እንደሚያሳዩት በህክምና ላይ ያሉ የኤችአይቪ /ኤድስ ታማሚዎች የከፋ የኮቪድ-19 ምልክቶች ወይም ውጤቶች ሰለባ አይሆኑም፡፡

በአሁኑ ጊዜ በዚህ ርእሰ ጉዳይ ላይ ያሉ ሳይንሳዊ ጥናቶችን የገመገሙት ተመራማሪዎች እንደሚሉት፣ የኤችአይቪ ታማሚዎች እንደማንኛውም ህምመተኛ ለኮቪድ-19 ህክምና ማግኘት እንደሚችሉ መረጃዎቹ ይጠቁማሉ፡፡

የኤችአይቪ ታማሚዎች የደከመ የበሽታ መከላከያ ስርዓቶች ስላሏቸው በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጊዜ ለከፋ ህመም እና ሞት ሊዳረጉ ይችላሉ ብለው ሰግተው ነበር፡፡

የኤችአይቪ/ኤድስ ታማሚዎች ለኮቪድ-19 ኢንፌክሽን ህክምናዎች ምን አይነት ምላሽ እምደሚሰጡ የሚዳስሱ ግላዊ ጥናቶችን በማየት ተማራማሪዎቹ ሌሎች ተመራማሪዎች፣ መንግስታት እና ዶክተሮች በኮቪድ-19 የተበከሉ የኤችአይቪ/ኤድስ ተማማዎች እንዴት መታከም እንዳለባቸው አጠቃለይ ውሳኔ እንዲወስዱ ያግዛቸዋል ብለው ተስፋ ያደርጋሉ፡፡

 ”ኤችአይቪ“ “ኤድስ” ”ኮሮና ቫይረስ“ እና “ኮቪድ-19“ አይነት ቁልፍ ቃላትን የያዙ እና በጃንዋሪ እና በጁን፣ 2020 መካከል የተለቀቁ የምርምር ወረቀቶችን ዳሰዋል፡፡

ተመራማሪዎቹ  በተለይ የጸረ-ኤችአይቪ ህክምና እየወሰዱ ያሉ እና በኮቪድ-19 አውንታዊ የህክምና ውጤት ያገኙ በኤችአይቪ የተያዙ ግለሰቦች ወይም ኤድስ ያለባቸው ሰዎች ላይ የተደረጉ ዘገባዎችን ሲፈልጉ ነበር፡፡

ተመራማሪዎቹ ከፍለጋቸው  ከ13 ሃገራት 35 ወረቀቶችን ያገኙ ሲሆን፣ የመጀመሪያው የኮቪድ 19-እና የኤችአይቪ የጋራ-ኢንፌክሽን ሪፖርት የተደረገው ቻይና ውስጥ ነበር፡፡

ኤችአይቪ/ኤድስ የኮቪድ-19 በሽታን የሚያባብስ እንደማይመስል አስተውለዋል፤ እና አዲስ የተመረመሩ የኤችአይቪ  ታማሚዎችም ከኮቪድ-19 ያገገሙ መሆኑን ደርሰውበታል፡፡

ተመራማሪዎቹ በተጨማሪ ታማሚዎቹ እንደ ሳል፣ ትኩሳት፣ የትንፋሽ ማጠር፣ ድካም፣ የማሽተት እና የጣእም ማጣት እና ተቅማጥ የመሰሉ የተለመዱ የኮቪድ-19 ምልክቶች እንደነበራቸው አግኝተዋል፡፡

አንድ ታማሚ ብቻ እንፍርፍሪት ነበረው፡፡

በጥቅሉ የኤችአይቪ/ኤድስ ታማሚዎች ለኮቪድ-19 እንደማንኛውም ሌላ በሽተኛ አይነት ምላሽ የመስጠት አዝማሚያ አላቸው፡፡

ነገር ግን፣ የኮቪድ-19 አደጋ የሚጨምረው ታማሚዎቹ እነደ ከፍተኛ የደም ግፊት፣ ስኳር፣ ከልክ ያለፈ ውፍረት እና የኩላሊት በሽታ አይነት ሌሎች በሽታዎች ተጠቂ ሲሆኑ ብቻ ነው፡፡

ተመራማሪዎቹ በተጨማሪ የኤችአይቪ/ኤድስ መድሃኒት የሆነው ዳሩናቪር የኮሮና ቫይረስ ኢንፌክሽንን እንደማይከላከል ደርሰውበታል፡፡

ፍለጋቸው እንዳረጋገጠው፣  የኩላሊት እና የጉበት ንቅለ ተከላ የነበራቸው በጋራ-ኢንፌክሽን የተጠቁ ታማሚዎች ከኮቪድ-19 አገግምዋል፡፡

ተመራማሪዎቹ ማግኘት የቻሉት በእንጊሊዘኛ የተጻፉ ጥናቶችን ብቻ ስለሆነ መደምደሚያቸው ወገንተኛ ሊሆን እንደሚችል አስጠንቅቀዋል፡፡

ኮቪድ-19 እንዴት ሳንባነቀርሳ እና የሳንባ ምች  ከመሳሰሉ ሌሎች በሽታዎች ጋር እንደሚገናኝ እና የጋራ-ኢንፌክሽኖች የታማሚዎች የስነልቦና ጤንነት ላይ እንዴት ተጽእኖ እንደሚኖራቸው ተጨማሪ ምርምሮች እንዲደረጉ ይመክራሉ፡፡

ይሄግምገማየተጠናቀረውኤችአይቪ/ኤድስከፍተኛየጤናሸክምበሆነበትበደቡብአፍሪካተመራማሪዎችነው፡፡

Connections
1 of 5
Comments
0
comment
No comments here
Why not start the discussion?