Skip to main content
SearchLoginLogin or Signup

በኬንያታ ዩኒቨርሲቲ ላሉ ሴት ተማሪዎች በቂ ጤናማ የምግብ አማራጮች የሉም።

Amharic translation of DOI: 10.21203/rs.2.13949/v1

Published onMay 18, 2023
በኬንያታ ዩኒቨርሲቲ ላሉ ሴት ተማሪዎች በቂ ጤናማ የምግብ አማራጮች የሉም።
·

በኬንያታ ዩኒቨርሲቲ ኬንያ ውስጥ የመጀመሪያ ዲግሪ ሴት ተማሪዎች የአመጋገብ ልምምዶች እና የአመጋገብ ሁኔታ ሰፊ የክፍል በክፍል ትንታኔ

ዓላማ፡

ይህ ጥናት የአመጋገብ ልማዶችን ለመመስረት ያለመ ሲሆን በሰውነት ክብደት መጠን ጠቋሚ ላይ የተመሰረተ የአመጋገብ ሁኔታን እና በኬንያ ውስጥ በኬንያታ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ዲግሪ የሚማሩ ሴት ተማሪዎች የአመጋገብ ልዩነት እና የአመጋገብ ሁኔታ መካከል ያለውን ግንኙነት ለመገምገም ያለመ ነው።

ስልቶች:

 ጥናቱ ከኬንያታ ዩኒቨርሲቲ በዘፈቀደ የተመረጡ 422 ሴት የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎችን ያካተተ ሰፊ የክፍል በክፍል የትንታኔ ንድፍን ተጠቅሟል።

ዝቅተኛው የአመጋገብ ልዩነት – የሴቶች እና የምግብ ድግግሞሽ መጠይቅ የሴት ተማሪዎችን የአመጋገብ ልምዶች ለመገምገም ጥቅም ላይ ውሏል።

የሴት ተማሪዎችን የአመጋገብ ሁኔታ ለመገምገም ክብደት እና ቁመት ተለክቷል።

የተገኘው መራጃ የተተነተነው በስታትስቲክስ ፓኬጅ ለማህበራዊ ሳይንሶች (SPSS) ስሪት 22 ነው።

ውጤቶች:

 ውጤቶቹ እንደሚያሳዩት ከተሳታፊዎች ውስጥ 64.0% የሚሆኑት ≥ 5 የምግብ ቡድኖችን ሲበሉ 36% ደግሞ በ24 ሰዓታት ውስጥ <5 የምግብ ቡድኖችን እንደበሉ አሳይተዋል።

በሥነ-ምግብ ሁኔታ መሰረት 68.4% ከተሳታፊዎቹ መደበኛ የሰውነት ክብደት መጠን ጠቋሚ ሲኖራቸው 23.9% ከመጠን ያለፈ ክብደት፣ 5.55% ከመጠን ያለፈ ዝቅተኛ ክብደት እና 2.3% ከመጠን ያለፈ ውፍረት ያላቸው ናቸው።

ዝቅተኛው የአመጋገብ ልዩነት – የሴቶች ከአመጋገብ ሁኔታ ጋር በእጅጉ የተቆራኘ ነው (p=0.044)።

ምክር፡

 ውጤቶቹ ቁጥራቸው ቀላል በማይባሉ ሴት ተማሪዎች መካከል ጤናማ ያልሆነ የአመጋገብ ልማድ እና በበቂ መልኩ ያልተመጣጠነ የምግብ ሁኔታን ያሳያል።

ፖሊሲ አውጪዎች በመውለድ ዕድሜ ላይ ያሉ ሴቶች በተለይም የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን የአመጋገብ ልምዶችን ለማሻሻል የሚረዱ ጣልቃገብነቶችን ማሳደግ አለባቸው።


በኬንያታ ዩኒቨርሲቲ ላሉ ሴት ተማሪዎች በቂ ጤናማ የምግብ አማራጮች የሉም።

በኬንያታ ዩኒቨርሲቲ ላሉ ሴት ተማሪዎች በቂ ጤናማ የምግብ አማራጮች የሉም።

የኬንያ ኬንያታ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የመጀመሪያ ዲግሪ በሚማሩ ሴት ተማሪዎች ላይ ከሚታየው የጤና መቃወስ እና ከፍተኛ ውፍረት በስተጀርባ ደካማ የምግብ ምርጫ እና የምግብ አይነት እጥረት እንዳለ ተመራማሪዎች ተናግረዋል።

 በኬንያ ውስጥ የአኗኗር ዘይቤ ለውጦች እና ልማዶች በአጠቃላይ ከመጠን በላይ የውፍረት በሽታ እንዲጨምር ምክንያት ሆኗል፤ እና በተለይ ለተማሪዎች እንዲህ ያለው የአመጋገብ ምርጫ በቀሪው ሕይወታቸው ጤና ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል።

በናይሮቢ ውስጥ በመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች መካከል የተደረገ ጥናት እንደሚያሳየው ከተማሪዎቹ 22.9% ከመጠን ያለፈ ክብደት እና ውፍረት ያለባቸው ሲሆን 5.5% የሚሆኑት ደግሞ ከመጠን ያለፈ ዝቅተኛ ክብደት ያላቸው ናቸው።

 ይህ ጥናት በተለይ በኬንያታ ዩኒቨርሲቲ የሴት ተማሪዎችን አመጋገብ እና ጤና አስሷል።

ተመራማሪዎች ለውፍረት በሽታ እና ለጤንነት መጓደል ሊዳርጉ የሚችሉ ምግቦችን ለይተው ማወቅ ፈልገው ነበር።

 ተመራማሪዎቹ በኬንያታ ዩኒቨርሲቲ በዘፈቀደ የተመረጡ 422 ሴት የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች ላይ ሰፊ የክፍል በክፍል ጥናት አድርገዋል።

በአመጋገባቸው ውስጥ ስላለው ልዩነት እና በምን ያህል ጊዜ እንደሚመገቡ ለተማሪዎቹን ቃለ መጠይቅ አድርገዋል።

 ጥናቱ እንደሚያሳየው 64.0% ሴት ተማሪዎች 5 የምግብ ቡድኖችን ሲመገቡ 36% ደግሞ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ5 ያነሰ የምግብ ቡድኖችን ይጠቀማሉ።

በተሳታፊዎች በብዛት የተበሉት የምግብ ቡድኖች 92% የእህል ምርቶች እና 78.4% አትክልቶች ናቸው።

በትንሹ ለውዝ እና ዘሮች 18.4% ተበልተዋል።

 ጥናቱ እንደሚያሳየው ከተሳታፊዎቹ 68.4% መደበኛ የሰውነት ክብደት መጠን ጠቋሚ፣ 23.9% ከመጠን ያለፈ ክብደት፣ 5.55% ከመጠን ያለፈ ዝቅተኛ ክብደት እና 2.3% ከመጠን ያለፈ ውፍረት ያላቸው ናቸው።

ተመራማሪዎቹ አብዛኛቹ (68.4%) ተማሪዎች በጥሩ ጤንነት ላይ መሆናቸውን ደርሰውበታል።

 ተመራማሪዎቹ ለምን ሴት ተማሪዎችን ብቻ እንደተመለከቱ አይገልጹም።

ስለ ማህበረ-ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎች ወይም ሴቶቹ ሊያጋጥሟቸው ስለሚችሉ ችግሮች ለምሳሌ እንደ ተደራሽነት እና ውድ ጤናማ ምግብ ወዘተ ያሉትን ማንኛውም ነገር ይጠቅሳሉ።

ተመራማሪዎቹ የመውለድ ዕድሜ ላይ ያሉ ሴቶች በተለይም የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን አመጋገብ ለማሻሻል ፖሊሲ አውጪዎች የአመጋገብ ጤና ፕሮግራሞችን ማሳደግ እንዳለባቸው ይመክራሉ።

 ጥናቱ የዩኒቨርሲቲው የመመገቢያ ስፍራዎች ገንቢ፣ የተለያዩ እና ምቹ የሆኑ የምግብ ማራጮችን እንዲያቀርቡ ይመክራል።

ይህም ተማሪዎች ጤናማ ባልሆኑ ፈጣን ምግቦች ላይ ጥገኛ እንዳይሆኑ መበረታታቸውን ያረጋግጣል።


Comments
0
comment
No comments here
Why not start the discussion?