Skip to main content
SearchLoginLogin or Signup

በ2በ2021 ተመራማሪዎች ብዙ የኢትዮጵያ ነዋሪዎች ማህበራዊ ርቀትን መጠበቅ እና እጅን መታጠብ አለም አቀፋዊ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ያስከሰተው የሳርስ-ኮቫ-2 ቫይረስን መስፋፋት እንደሚከላከል ያውቁ ነበር፡፡

Amharic translation of DOI: 10.1371/journal.pone.0234585

Published onSep 30, 2023
በ2በ2021 ተመራማሪዎች ብዙ የኢትዮጵያ ነዋሪዎች ማህበራዊ ርቀትን መጠበቅ እና እጅን መታጠብ አለም አቀፋዊ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ያስከሰተው የሳርስ-ኮቫ-2 ቫይረስን መስፋፋት እንደሚከላከል ያውቁ ነበር፡፡
·

በኢትዮጵያ ነዋሪዎች የኮቪድ-19 ወረርሽኝን የመከላከል እውቀት እና አተገባበር፡፡

የመስመር ላይ ሰፊ የክፍል በክፍል ጥናት

የጀርባ ታሪክ፦

በኖቭል ኮሮና ቫይረስ የሚከሰተው በሽታ (ኮቪድ-19) የአለም አቀፍ አደጋ ተደርጎ የሚቆጠር ሲሆን፣ የአለም ጤና ድርጅት (አ.ጤ.ድ) እንደ ወረርሽኝ በሽታ አውጆታል፡፡

ዓላማ

የዚህ ጥናት አላማ በኢትዮጵያ ነዋሪዎች የኮቪድ-19 ወረርሽኝን የመካላከል እወቀት እና ልምምዶችን መዳሰስ ነው፡፡

ዘዴዎች፦

በጸሃፊው እንደ ፌስቡክ፣ ቴሌግራም እና ኢሜይል የመሰሉ ማህበራዊ መድረኮች ላይ በተፈጠሩ ግንኙነቶች አማካኝነት በተገኙ የኢትዮጵያ ነዋሪ ናሙናዎች የመስመር ላይ ሰፊ የክፍል በክፍል ጥናት ተካሂዷል፡፡

ተሳታፊዎችን ለመልመል የስኖቦል የናሙና አወሳሰድ ዘዴ ተተግብሯል፡፡

ይህንንም በማድረግ የ341 ተሳታፊዎች ምላሾችን በተሳካ ሁኔታ ከኤፕሪል 15 እስከ 22፣ 2020 ሰብስበናል፡፡

የተሰበሰቡት መረጃዎችም በSTATA 14ተኛ ስሪት ሶፍትዌር የተገመገሙ ሲሆን፣ በኮቪድ-19 ዙሪያ የማህበረሰቡን እውቀት እና ልምምዶች አጠቃሎ ለማቅረብ ዘጋቢ ስታትስቲክሶች  ጥቅም ላይ ውለዋል፡፡

ውጤቶች፡-

አብዛኛዎቹ መላሽ የሰጡት ሰዎች፣ 80.5% ያህሉ ወንዶች ነበሩ፡፡

ከተሳታፊዎቹ 91.2% የሚሆኑት ስለ ኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሰምተው ነበር፡፡

በተጨማሪም ከ341 ተሳታፊዎች 90.0% እና 93.8% የሚሆኑት በቅደም ተከተል ማህበራዊ ርቀት በመጠበቅ እና እጅን ደጋግሞ በመታጠብ ኮቪድ-19ን መከላከል እንደሚቻል ያውቁ ነበር፡፡

ይህ የሚያሳየው ተሳታፊዎቹ ማህበራዊ ርቀትን በመጠበቅ እና ደጋግሞ እጅን በመታጠብ ኮቪድ-19ን መከላከል እንደሚቻል ያላቸው እውቀት ከፍተኛ እንደሆነ ነው፡፡

ነገር ግን ከ341 ተሰታፊዎች በቅደም ተከተል 61% እና 84% ብቻ የሚሆኑት ኮቪድ-19ን ለመከላከል ማህበራዊ ርቀት መጠበቅን እና ደጋግሞ እጅ መታጠብን ተግብረዋል፡፡

ማጠቃለያ፡-

ከተሳታፊዎቹ አብዛኞቹ እራሳቸውን ከኖቭል ኮሮናቫይረስ (ኮቪድ-19) እንዴት እንደሚጠብቁ ያውቁ ነበር፤ ነገር ግን ይህንን የመከላከል እውቀት ወደተግባር መቀየሩ ላይ ከባድ ችግር ነበር፡፡

ይህ የሚያሳየው የኮቪድ-19ን መከላከያ መንገዶች በማወቅ  እና እወቀቱን  በማህበረሰብ ውስጥ የኮቪድ-19 መስፋፋትን ለመከላከል ወደ ተግባር በመቀየር መካከል ክፍተት እንዳለ ነው፡፡

ስለዚህ ነገሩ የሚመለከተው አካል የመከላከል እውቀትን እንዴት መተግበር እንደሚቻል ማህበረሰቡን ማስተማር እና ማሳወቅ ላይ ማተኮር አለበት፡፡


በ2በ2021 ተመራማሪዎች ብዙ የኢትዮጵያ ነዋሪዎች ማህበራዊ ርቀትን መጠበቅ እና እጅን መታጠብ አለም አቀፋዊ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ያስከሰተው የሳርስ-ኮቫ-2 ቫይረስን መስፋፋት እንደሚከላከል ያውቁ ነበር፡፡

በ2በ2021 ተመራማሪዎች ብዙ የኢትዮጵያ ነዋሪዎች ማህበራዊ ርቀትን መጠበቅ እና እጅን መታጠብ አለም አቀፋዊ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ያስከሰተው የሳርስ-ኮቫ-2 ቫይረስን መስፋፋት እንደሚከላከል ያውቁ ነበር፡፡

በ2021 ተመራማሪዎች ብዙ የኢትዮጵያ ነዋሪዎች ማህበራዊ ርቀትን መጠበቅ እና እጅን መታጠብ አለም አቀፋዊ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ያስከሰተው የሳርስ-ኮቫ-2 ቫይረስን መስፋፋት እንደሚከላከል ያውቁ ነበር፡፡

ግን ተመራማሪዎች እንዳሉት አብዛኞቹ እነዚህን መፍተሄዎች በተግባር እያወሉም ነበር፡፡ ስለዚህ  ሰዎች ለእነዚህ መከላከያ መንገዶች እንዲገዙ ለማድረግ ህጋዊ አካላት ጠንክረው እንዲሰሩ ያበረታታሉ፡፡

ኮቪድ-19 በፍጥነት በአለም ዙሪያ በመስፋፋት የጤና ሲስተሞችን እና እንደ ኢትዮጵያ የሉ ታዳጊ ሃገሮች ኢኮኖሚን የማጨናነቅ ስጋትን የጣለ አደገኛ የመተንፈሻ አካል በሽታ ነው፡፡

መንግስት እንደ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አካል የቫይረሱን መስፋፋት እጆችን ደጋግሞ በመታጠብ እና እርስ በእርስ ማህበራዊ ርቀትን በመጠበቅ መከላከል እንደሚቻል ለዜጎቹ መረጃ አቅርቧል፡፡

ይህ ጥናት የኢትዮጵያ ነዋሪዎች ስለእነዚህ መከላከያ ዘዴዎች ያላቸውን እውቀት  እና እውቀታቸውን በትክክሉ እየተገበሩ እንደሆነ ለመገምገም የዳሰሳ ጥናት አድርጓል፡፡

ተመራማሪዎቹ የመስመር ላይ መጠይቅ ሰርተው በማህበራዊ ሚዲያ ላይ አጋርተውታል፡፡

ሰዎች ስለኮቪድ-19 ወረርሽኝ እና ስለመከላከያ እርምጃዎች ከዚህ ቀደም መስማታቸውን እና በእርግጥ እጃቸውን ይታጠቡ እና ማህበራዊ ርቀታቸውን ይጠብቁ እንደሆነ ለማወቅ የህዝበ ነክ ጥናት ጥያቄዎችን ጠይቀዋቸዋል፡፡

341 ሰዎች የመስመር ላይ የዳሰሳ ጥናቱን ያጠናቀቁ ሲሆን ከእነዚህም 80% ያህሉ ወንዶች ነበሩ፡፡

ተመራማሪዎቹ እንዳሉት አብዛኞቹ ከከተማ የመጡ እና በደንብ የተማሩ መልስ ሰጪዎች ማህበራዊ ርቀትን የመጠበቅ፣ ፊትን ያለመንካት እና ያለመተቃቀፍ አይነት መከላከያዎች ኢንፌክሽኑን ለመከላከል እንደሚረዱ ያውቁ ነበር፡፡

በአጠቃለይ የዳሰሳ ጥናት የተደረገባቸው ከ90% በላይ የሚሆኑ ሰዎች የኮቪድ-19 መስፋፋትን እንዴት አድረገው መከላከል እንደሚችሉ ያውቁ ነበር፡፡ ከእነዚህም 61% የማህበራዊ ርቀት መጠበቅን እንደተገበሩ ተናግረዋል፡፡ 84% የሚሆኑት ደግሞ እጃቸውን ደጋግመው እንደታጠቡ አሳውቀዋል፡፡

በዚህ ጥናት ዜጎቻቸው ስለ ኮቪድ-19 እና የመከላከያ መንገዶቹ ምን ያህል ንቁ እንደሆኑ ካሰሱ ሌሎች ብዙ ሃገሮች ጋር ኢትዮጵያ ተቀላቅላለች፡፡

ነገር ግን ተመራማሪዎቹ ይህ ንቁነት በተለይ እንዴት ወደ ተግባር እንደተቀየረ የሚገልጹ ሌሎች ብዙ ጥናቶችን ማግኘት አልቻልንም ብለዋል፡፡

እንዲያውም እውቀት ወይም ንቁ መሆን ወዲያውኑ የባህሪ ለውጥ ያመጣል ማለት አይደለም ብለዋል፡፡

ተመራማሪዎቹ መጠይቆቹ የተሰጡት ኢንተርኔት እና ማህበራዊ ሚዲያ ላላቸው ሰዎች ብቻ ስለሆነ  ውጤቶቻቸው መላውን ህብረተሰብ ላይወክሉ እንደሚችሉ ያሳስባሉ፡፡

ሆኖም ግን ህጋዊ አካላት ህብረተሰቡ እንዴት ኮቪድ-19ን መከላከል እንደሚቻል መረጃ ከመስጠት አልፈው ዜጎች እውቀቶቻቸውን ወደ ተግባር እንዲቀይሩ ማበረታታት አለበቻው፡፡

ይህንጥናትያካሄዱትሁሉምተመራማሪዎችከኢትዮጵያዩኒቨርሲቲዎችየመጡሲሆንተሳታፊዎቹበሙሉደግሞየኢትዮጵያዜጎችናቸው፡፡

Connections
1 of 5
Comments
0
comment
No comments here
Why not start the discussion?