Description
This is a lay summary of the article published under the DOI: 10.1101/2021.02.08.21251393)
Amharic translation of DOI: 10.1101/2021.02.08.21251393
የሳርስ-ኮቫ-2 ጂኖሚያዊ ክትትል ወደብ የለሽ በሆነችው ትንሿ የምስራቅ አፍሪካ ሃገር ዩጋንዳ፣ በቫይረሱ ዝግመተ ለውጥ ላይ የሚያተኩር መግለጫ ለማቅረብ እድል ይሰጣል፡፡
እዚህ ጋር፣ አዲስ ብቅ ባለው እና ከA.23 ወደ A.23.1 በተለወጠው የትውልድ ሃረግ፣ አሁን ላይ የዩጋንዳን ሁነቶች በመቆጣጠር ላይ ያለውን እና ወደ 26 ሌሎች ሃገሮች የተሰራጨውን የኣካባቢ ወረርሽኝ የቅርብ ጊዜ ፈቀቅታ እናሳያለን፡፡
ምንም እንኳ በ A.23.1 ውስጥ ያሉት ትክክለኛ ለውጦች፣ ከአስጊ-ልውጠቶች (አ.ል) ከወሰዳቸው ለውጦች የተለዩ ቢሆኑም ዝግመተ ለውጡ የተመሳሳይ ፕሮቲኖች ስብስብ መገጣጠምን ያሳያል፡፡
የ A.23.1 ስፓይክ ፕሮቲን ኮድ የማድረጊያ ክልል አ.ል ውስጥ ከታዩት ብዙ ለውጦች ጋር የሚመሳሰሉ ብዝሃ ለውጦችን አከማችቷል፡፡ ይህም በቦታ 613 ላይ የተደረገ ለውጥን ጨምሮ መሰረታዊ የአሚኖ አሲድ ሞቲፍን የሚያራዝመው የፉሪን ስንጥቅ ቦታ ለውጥን እና በ ኤን-ተርሚናል ግዛት ላይ በርካታ ለውጦችን አምጥቷል፡፡
በተጨማሪም የA.23.1 የትውልድ ሃረግ በስፓይክ-ቢስ ፕሮቲኖች ውስጥ ሌሎች አ.ል የሚያሳዩትን ለውጦች (nsp6፣ ORF8 እና ORF9) ኮድ ያደርጋል፡፡
የA.23.1 ልውጠት ክሊኒካዊ ተጽእኖ ገና ግልጽ አይደለም፤ ነገር ግን ይህንን ልውጠት በጥንቃቄ መከታተል እና የስፓይክ-ፕሮቲን ለውጦች በክትባት ውጤታማነት ላይ የሚያስከትሉትን ተጽእኖ በፍጥነት መገምገም አስፈላጊ ነው፡፡
በ2021 ተመራማሪዎች እንደዘገቡት ኮቪድ-19ን የሚያመጣው አዲሱ ልውጠት ሳርስ-ኮቫ-2፣ ከዩጋንዳ ወጥቶ ወደ 26 ሌሎች ሃገሮች ተሰራጭቷል፡፡
ይህንን ልውጠት “A.23.1” ብለው ሰይመውታል፤ እንዲሁም ተመራማሪዎቹ በዚህ ወቅት በአለም ዙሪያ በሌሎች አስጊ-ልውጠቶች ውስጥ በሚገኙ ፕሮቲኖች ላይ ያስተዋሏቸው ተመሳሳይ ለውጦች አሉት ብለዋል፡፡
ሳይንቲስቶቹ ክትባቶች በአዲሶቹ ልውጠቶች ላይ ምን ያህል እንደሚሰሩ በተሻለ ሁኔታ ለመረዳት የኮሮና ቫይረስ ልውጠቶች እንዴት እንደሚቀያየሩ ይከታተላሉ፡፡
ኮቪድ-19 በአለም ዙሪያ ብዙ ሰዎችን ገድሏል፡፡
የጂኖሚያዊ ክትትል ተብሎ በሚታወቀው ሂደት ውስጥ ሳይንቲስቶቹ የቫይረሱ ስነ ባህሪይ እና ፕሮቲኖች በስርጭቱ ወቅት እንዴት እንደሚለወጡ ይቆጣጠራሉ፡፡
ይህን መረጃ በሽታውን ለመቆጣጠር እና የክትባት እድገትን ለመምራት ይጠቀሙበታል፡፡
ለምሳሌ የቫይረሱን ስፓይክ-ፕሮቲኖች አወቃቀር በመረዳት ተመራማሪዎቹ ቫይረሱ ወደ ሰው ሴሎች እንዳይገባ ለመከላከል እነዚያ ፕሮቲኖች ላይ የሚያነጣጥሩ ክትባቶችን መንደፍ ይችላሉ፡፡
በዚህ ጥናት ውስጥ ተመራማሪዎች ሳርስ-ኮቫ-2 በተለይ በዩጋንዳ ውስጥ እንዴት እየተለወጠ እንደመጣ አስተውለዋል፡፡
ተመራማሪዎቹ ከመላው ዩጋንዳ ከተሰበሰቡ የኮቪድ-19 ፖዘቲቭ ናሙናዎች የጄኔቲክ ዋነኛ አወቃቀሮችን ወስነዋል፡፡
በዚህ መንገድ የለዩትን (A.23.1 ተብሎ የሚጠራውን) አዲሱን ልውጠት የትውልድ ሃረግ ( ወይም የቤተሰብ ታሪክ) ለመከታተል የኮምፒውተር ሶፍትዌር ተጠቅመዋል፤ እና ልውጠቱ በሳርስ-ኮቫ-2 የዘር ሃረግ ውስጥ የቱ ጋር እንደሚገባ ለማየት ችለዋል፡፡
ውጤታቸው A.23.1 ልውጠት በቅርብ ጊዜ A.23 ከተባለ ከሌላ ልውጠት የመጣ እና 90% በሚሆኑት በሁሉም ፖዘቲቭ ናሙናዎች ውስጥ የተገኘ መሆኑን ያሳያል፡፡
በሌላ አነጋገር ከኦክቶበር 2020 ጀምሮ የኡጋንዳን ናሙናዎች ተቆጣጥሮ ነበር፡፡
በተጨማሪም የA.23.1 ልውጠት በሌሎች አስጊ-ልውጠቶች ላይ እንደታየው አይነት ለውጦች በስፓይክ-ፕሮቲኖች ውስጥ ብዙ ለውጦች እንደነበረው ደርሰውበታል፡፡
ለውጦቹ ልውጠቱን የበለጠ ተላላፊ (በፍጥነት የሚሰራጭ) እና ለክትባቶች እና ለህክምናዎች የበለጠ ተቋቋሚ ሊያደርጉት ይችላሉ፡፡
ይህ ጥናት የሳርስ-ኮቫ-2 ልውጠቶችን ዋነኛ አወቃቀር ለመለየት በሚደረገው አለም-አቀፋዊ ጥረት ላይ ግብአት ይጨምራል፡፡
ውጤቶቹ ሳርስ-ኮቫ-2 ብዙ ሰዎችን እየበከለ እና ክትባቶችን እያመለጠ በሚሰራጭበት ጊዜ በፍጥነት ስለመቀያየሩ እያደጉ በመጡት ማስረጃዎች ላይ ግብአቶችን ይጨምራሉ፡፡
ነገር ግን በA.23.1 ልውጠት ውስጥ የስፓይክ-ፕሮቲኖች ተጽእኖ እና አገልግሎት በትክክል ምን እንደሆነ ለመረዳት ተጨማሪ ምርምር ያስፈልጋል፡፡
ተመራማሪዎቹ የቫይረሱ ልውጠቶች በኡጋንዳ እና በሌሎች ሃገሮች ላሉት ክትባቶች እንዴት ምላሽ እንደሚሰጡ ለመረዳት ተጨማሪ የጂኖሚያዊ ክትትል ማድረግን ይመክራሉ፡፡
በተጨማሪምተመራማሪዎቹቫይረሱበሃገርውስጥእንዴትእንደሚዘዋወርበበለጠመረዳትይችሉዘንድአለምአቀፍጉዞዎችንበቅርበትመከታተልአስፈላጊነውይላሉ፡፡
Zulu translation of DOI: 10.1101/2021.02.08.21251393
Northern Sotho (Sepedi) translation of DOI: 10.1101/2021.02.08.21251393
Yoruba translations of DOI: 10.1101/2021.02.08.21251393
Luganda translation of DOI: 10.1101/2021.02.08.21251393
Hausa translation of DOI: 10.1101/2021.02.08.21251393