Skip to main content
SearchLoginLogin or Signup

በስኳር በሽተኞች ዘንድ የብልት መቆም ችግር መስፋፋት፣ ከአጠቃላይ የሰውነት ትልቅነት ጠቋሚ እና ከግላይኬትድ ሄሞግሎቢን ጋር ያለው ግንኙነት

This is Amharic translation of DOI:10.1155/2020/5148370

Published onJun 20, 2023
በስኳር በሽተኞች ዘንድ የብልት መቆም ችግር መስፋፋት፣ ከአጠቃላይ የሰውነት ትልቅነት ጠቋሚ እና ከግላይኬትድ ሄሞግሎቢን ጋር ያለው ግንኙነት
·

በስኳር በሽተኞች ዘንድ የብልት መቆም ችግር መስፋፋት፣ ከአጠቃላይ የሰውነት ትልቅነት ጠቋሚ እና ከግላይኬትድ ሄሞግሎቢን ጋር ያለው ግንኙነት:

ስልታዊ ግምገማ እና ሜታ አናሊሲስ በአፍሪካ

Abstract

የጀርባ ታሪክ፡፡

በስኳር በሽተኞች (ስ.በ) ዘንድ ያለው ታማሚነት እና ሟችነት፣ደም ቅዳ፣ ደም መልስ፣ እንዲሁም ካፒላሪስ በሚባሉት እና በሰውነት ውስጥ የተለያየ ስራ በሚያከናውኑት የደምስሮች ውስጥ በሚያጋጥም መወሳሰብ (ማይክሮ ቫስኪዩላር እና ማክሮ ቫስኪዩላር) ላይ ተጥሏል፡፡

ሆኖም ግን፣ በአፍሪካ ውስጥ በስ.በ ዘንድ ያለውን የብልት መቆም ችግር (ብ.መ.ች) መስፋፋትን በተመለከተ፣ በመጀመሪያ ደረጃ ጥናቶች ውስጥ ጉልህ መጠን ያለው ልዩነት ታይቷል፡፡

ስለዚህ፣ ይህ ጥናት ያነጣጠረው በአፍሪካ በስ.በ ውስጥ ያለው አጠቃላይ የብ.መ.ች መስፋፋት ከአጠቃላይ የሰውነት ትልቅነት ጠቋሚ (አ.ሰ.ት.ጠ) እና ከግላኬትድ ሄሞግሎቢን ጋር ያለውን ግንኙነት መገመት ላይ ነበር፡፡

ስልቶች፡፡

በስ.በ ዘንድ ያለውን ብ.መ.ች አስመልክቶ የተሰሩ ጥናቶችን ለማግኘት፣ ፐብሜድ፣ዌብኦፍ ሳይንስ፣ኮክሬን ላይብረሪ፣ ስኮፐስ፣ሳይክኢንፎ ፣ በመስመር ላይ ያሉ አፍሪካዊ መጽሄቶች፣ እና ጉግል ስኮላር ተፈትሸዋል፡፡

ፈነል ፕሎት እና ኤገር ሪግሬሽን የተባሉት ፈተናዎች የህትመት አድሏዊነትን ለመገመት ጥቅም ላይ ውለዋል፡፡

በጥናቶቹ መካከል ልዩነት እንዳለ ለማጣራት I2 ስታትስቲኮች በስራ ላይ ውለዋል፡፡

አጠቃላይ የውጤቱን መጠን ለመገመት፣ ዴርሲሞንያን እና ሌርድ ራንደም-ኢፌክት ሞዴሎች ተግባር ላይ ውለዋል፡፡

የንዑስ ቡድን እና ሜታ-ሪግሬሽን ትንተናዎች፣ በሃገር ደረጃ ፣ በናሙና መጠን፤ እና በህትመት አመት ላይ ተካሂደዋል፡፡

አንድ ነጠላ ጥናት በጠቅላላው ግምት ላይ ያለውን ተጽእኖ ለማየት፣ የሴንሲቲቪቲ ትንተና ስምሪት ላይ ውሎ ነበር፡፡

ለሜታ ትንተና፣ ስታታ ስሪት 14 ሶፍትዌር ስራ ላይ ውሏል፡፡

ውጤት፡፡

በዚህ ጥናት በጥቅሉ 13 ጥናቶች እና 3501 ተሳታፊዎች ተካትተዋል፡፡

በአፍሪካ ውስጥ፣ በስ.በ ዘንድ ያለው የብ.መ.ች ስርጭት 71.45% እንደሆነ ገምተናል (95% CI: 60.22–82.69)፡፡

ምንም እንኳ ከብልት መቆም ችግር ጋር ጉልህ ዝምድና ባይኖራቸውም ፣የስኳር በሽተኞች ጠቅላላ የሰውነት ትልቅነት (BMI) ≥30 kg/m2 የነበሩ፤1.26 ጊዜ የብልት መቆም ችግር ሊያጋጥማቸው ይችላል፤ እንዲሁም (AOR = 1.26; 95% CI: 0.73–2.16) እና ግላይኬትድ ሄሞግሎቢናቸው <7% የሆኑ ደግሞ የብልት መቆም ችግር የማጋጠሙ እድል በ7% ያነሰ ነው ፤ (AOR = 0.93; 95% CI: 0.5–5.9)፡፡

መደምደሚያዎች፡፡

በአፍሪካ በስ.በ ዘንድ ያለው የብ.መ.ች መስፋፋት ከፍ እንዳለ ቀጥሏል፡፡

ስለዚህ፣ በስ.በ ዘንድ ያለውን የብ.መ.ች መስፋፋት ለመቀነስ፣ ለየእያንዳንዱ ሃገር ልዩ የሆኑ ፣እና ሁኔታን መሰረት ያደረጉ ጣልቃገብ ስራዎች እንዲሁም ሃገር ተኮር ውስን አውድ ያላቸው የመከላከል ዘዴዎች ሊዳብሩ ይገባል፡፡

Summary Title

በአፍሪካ 70% የሚሆኑ የስኳር በሽተኛ ወንዶች የብልት መቆም ችግር እንደሚያጋጥማቸው ዘግበዋል፡፡

በሚሊዮን የሚቆጠሩ በአለም ዙሪያ ያሉ የስኳር በሽተኞች፣በብልት መቆም ችግር ይሰቃያሉ፤ ሆኖም ግን በአፍሪካ ውስጥ ያሉት ቁጥራቸው እስካሁን ድረስ አልታወቀም ነበር፡፡

በአለም አቀፍ ደረጃ በ2017 እ.ኢ.አ፣ በግምት 425 ሚሊዮን የሚሆን ህዝብ በስኳር በሽታ (ስ.በ) ተጠቅቷል፤ እና ይህም በ2045 እ.ኢ.አ ወደ 629 ሚሊዮን ከፍ ይላል ተብሎ ይገመታል፡፡

አንድ የተለመደ ግን ዝቅተኛ ግምት የሚሰጠው የስኳር በሽታ ውስብስብ ችግር የብልት መቆም ችግር (ብ.መ.ች) ነው፡፡ ይህም አርኪ የሆነን ወሲባዊ ግንኙነት ለመፈጸም በሚያስችል መልኩ ብልትን ማቆም እና እንደቆመም ማቆየት አለመቻል ነው፡፡

49 % በሚሆኑ የለንደን ነዋሪ የስኳር በሽተኛ ወንዶች 35.8 % በጣሊያን፣77.1 % በደቡብ አፍሪካ፣እና 67.9 % በጋና፤የብልት መቆም ችግር ተዘግቧል፡፡

ነገር ግን ሌሎቹ ከአፍሪካ የመጡት ዘገባዎች እጅግ በጣም ይለያያሉ ፤ስለዚህ ተመራማሪዎቹ በስኳር በሽታ ታማሚዎች ዘንድ እንዴት የብልት መቆም ችግር እንደተስፋፋ፣ ከመጠን ካለፈ የሰውነት ክብደት እና ከከፍተኛ የስኳር መጠን ጋር ዝምድና መኖር አለመኖሩን ለመወሰን ዘገባዎቹን ያነጻጽራሉ፡፡

ተመራማሪዎቹ በስኳር በሽተኞች ላይ ያለውን የብልት መቆም ችግር በተመለከተ፣ የተሰሩ ጥናቶችን እንደ ፐብሜድ፣ዌብኦፍ ሳንይንስ፣ኮክሬን ላይብረሪ፣ ስኮፐስ፣ሳይክኢንፎ፣ በመስመር ላይ ያሉ አፍሪካዊ መጽሄቶች፣ እና ጉግል ስኮላር ላይ በስፋት ዳሰሳ አድርገዋል፡፡

በጠቅላላው 3501 ተሳታፊዎች የተሳተፉባቸውን 13 የጥናት ግኝቶችን ለመተንተን የተለያዩ ስታትስቲካዊ ዘዴዎችን ተጠቅመዋል፡፡

ተስፋፍቶ ያለው የብልት መቆም ችግር አጠቃላይ ግምት አለማዛባቱን ለማረጋገጥ እና አንድም ጥናት በሌሎቹ ላይ ተጽእኖ እንዳያመጣ፣ የሴንሲቲቪቲ ትንተና አካሂደዋል፡፡

ጥናቱ በአፍሪካ በ71.45 % የስኳር በሽተኛ ወንዶች ላይ የብልት መቆም ችግር እንደተስፋፋ ደርሶበታል፡፡

አጠቃላይ የሰውነት ትልቅነታቸው ወደ ግዙፍነት የሚያዘነብል የስኳር በሽተኞች1.26 ግዜ የበለጠ የብልት መቆም ችግር ሊያዳብሩ እንደሚችሉ ደርሰውበታል፡፡

በተጨማሪም በ7% ግላይኬትድ ሄሞግሎቢን ጥቆማ መሰረት፣ የደማቸው የስኳር ቁጥጥር ጥሩ የሆነ እና የረዥም ጊዜ የደም ስኳር ቁጥጥር ያላቸው የስኳር በሽተኞች፣ የብልት መቆም ችግር የማዳበራቸው እድል 7% ያህል ሊቀንስ እንደሚችል ደርሰውበታል፡፡

ጥናቱ ፣በመጪዎቹ ምርምሮች ከግምት ውስጥ ሊገቡ የሚገባቸው አያሌ ገደቦች አሉበት፡፡

በመጀመሪያ፣በአፍሪካ ምንም ውሂብ/ዳታ ባለመገኘቱ ከተለያዩ ሃገራት የተገኙት ውጤቶች መላውን አህጉር ይወክላሉ ብሎ ለመወሰን አስቸጋሪ ነው፡፡

ሁለተኛ፣ ጥናቱ ከግምት ውስጥ ያስገባው የእንጊሊዘኛ ጽሁፎችን ብቻ ነው፤ ይህ ማለት ደግሞ ጥናቱ በሌሎች ቋንቋዎች የታተሙ ጠቃሚ ዳታዎች/ውሂቦች ሊያመልጡት ይችላሉ፡፡

እነዚህ ውጤቶች በአፍሪካ ባሉ የስኳር በሽተኞች ላይ የሚከሰተው የብልት መቆም ችግር እንደተስፋፋ እንደሚቀጥል ያሳያሉ፡፡

ተመራማሪዎቹ ለየእያንዳንዱ ሃገር ልዩ የሆኑ እና ሁኔታ-ተኮር የሆኑ ጣልቃገብ ስራዎችን እንዲያዳብሩ ይመክራሉ፡፡

Connections
1 of 5
Comments
0
comment
No comments here
Why not start the discussion?