Skip to main content
SearchLoginLogin or Signup

ሁለቱም ኤችአይቪ እና ከፍተኛ የደም ግፊት ያለባቸው ኡጋንዳዊያን የሚገባውን እንክብካቤ እያገኙ አይደለም፡፡

Amharic translation of DOI: 10.1186/s43058-020-00033-5

Published onOct 02, 2023
ሁለቱም ኤችአይቪ እና ከፍተኛ የደም ግፊት ያለባቸው ኡጋንዳዊያን የሚገባውን እንክብካቤ እያገኙ አይደለም፡፡
·

በኡጋንዳ የኤችአይቪ ክሊኒኮች የተቀናጀ ከፍተኛ የደም ግፊትን እና-ኤችአይቪን ለማስተዳደር ያሉ እንቅፋቶች እና ደጋፊ ምክንያቶችን የተጠናከረ የትግበራ ምርመራ  ማእቀፍን (ተ.ት.ም.ማ) በመጠቀም መዳሰስ

የጀርባ ታሪክ፦

ጸረ-ኤችአይቪ ህክምና እያገኙ ያሉ እና ከኤችአይቪ ጋር የሚኖሩ ሰዎች (ኤ.ጋ.የ.ሰ)  ስርአተ ልብ ወቧንቧ በሽታን (ስ.ል.ወ.በ) የማዳበር ከፍተኛ እድል አላቸው፡፡

በኡጋንዳ ለ ስ.ል.ወ.በ አደጋ ዋነኛ ምክንያት ለሆነው ለከፍተኛ የደም ግፊት (ከ.ደ.ግ) የሚሰጡ አገልግሎቶችን ከኤችአይቪ ክሊኒኮች ጋር ማቀናጀት ይመከራል፡፡

ከዚህ በፊት የሰራናቸው ስራዎች ከኤችአይቪ ህክምና ስኬቶች ጋር የ ከ.ደ.ግ እንክብካቤን የማቀናጀት ተግባር ላይ ብዙ ክፍተቶች እንዳሉ ያሳያሉ፡፡

በዚህ ጥናት በምስራቅ ኡጋንዳ የከ.ደ.ግ ማጣራት እና ህክምናን ከኤችአይቪ ክሊኒኮች ጋር ለማቀናጀት ያሉትን እንቅፋቶች እና ደጋፊ ምክንያቶችን ለመዳሰስ ፈልገን ነበር፡፡

ዘዴዎች፦

በፊት በሰራናቸው ስራዎች ላይ ተመስርተው በተመደቡ በሶስት ዝቅተኛ፣ መካከለኛ እና ከፍተኛ የ ከ.ደ.ግ እንክብካቤ ስኬት ክንዋኔ ባለባቸው የኤችአይቪ ክሊኒኮች፣ ኳሊቴቲቭ ጥናቶችን አካሂዴናል፡፡

በተጠናከረ የትግበራ ምርመራ ማእቀፍ (ተ.ት.ም.ማ) በመመራት፣ በከፊል-የተዋቀሩ ቃለመጠይቆችን እና የትኩረት ቡድን ውይይቶችን ከጤና አገልግሎት አስተዳዳሪዎች ፣ ከጤና አገልግሎት አቅራቢዎች እና ከፍተኛ የደም ግፊት ካላቸው ከኤ.ጋ.የ.ሰ ጋር አድርገናል፡፡

ቃለመጠይቆቹ ቃል በቃል ተገልብጠዋል፡፡

ሶስት ኳሊቴቲቭ ተመራማሪዎች ጠቃሚ ኮዶችን እና ጭብጦችን ለማመንጨት መንእሳዊ (ተ.ት.ም.ማ-መር) ዘዴን ተጠቅመዋል፡፡

እያንዳንዱ የ ተ.ት.ም.ማ ውቅር በ  ከ.ደ.ግ/ኤችአይቪ ቅንጅት ላይ ያለውን ተጽእኖ ለይቶ ለማወቅ የቫለንስ እና የጥንካሬ ደረጃዎች ተከናውነው ነበር፡፡

ውጤቶች፡-

ከ ስድስት የ ተ.ት.ም.ማ ውቅሮች ለ ከ.ደ.ግ/ኤችአይቪ ቅንጅት እንቅፋት የሆኑ ነገሮች ተነስተው ነበር፡

ድርጅታዊ ማበረታቻዎች እና ሽልማቶች፣ ያሉ ግብአቶች፣ የመረጃ እና የእውቀት ተደራሽነት፣ ጣልቃ ገብነቱን አስመልክቶ ያለው ግንዛቤ እና አስተሳሰብ፣ ራስን የመቻል ብቃት እና እቅዶችን ማውጣት፡፡

እንቅፋቶቹ ደግሞ የሚከተሉትን ያካትታሉ፤ የሚሰሩ የደም ግፊት መለኪያ ማሽኖች አለመኖር፣ በቂ ያልሆነ የጸረ-ከፍተኛ የደም ብዛት መድሃኒቶች አቅርቦት፣ ኤ.ጋ.የ.ሰ ስለ ከ.ደ.ግ እንክብካቤ ያላቸው አነስተኛ ግንዛቤ፣ የጤና አገልግሎት አቅራቢዎች ከ.ደ.ግን አጣርቶ ለማወቅ እና ለመመርመር ያላቸው አነስተኛ ግንዛቤ፣ ክህሎት እና በእራስ የመስራት ችሎታ ማነስ እና የተቀናጁ የ ከ.ደ.ግ/ኤችአይቪ አገልግሎቶችን ለመስጠት ያለው አመርቂ ያልሆነ የእቅድ አወጣጥ ናቸው፡፡

የ ከ.ደ.ግ እና የኤችአይቪ አገልግሎቶችን በአንድ ቦታ በሚገኝ ማእከል ላይ የመስጠት አንጻራዊ ጥቅም ፣ የተቀናጀ የ ከ.ደ.ግ/ኤችአይቪ እንክብካቤ ቀላልነት (ያልተወሳሰበ አሰራር) ፣ መላመድ እና አሁን ላይ እየተሰጡ ካሉ የኤችአይቪ አገልግሎቶች ጋር የከ.ደ.ግ እንክብካቤ ተኳሃኝነት ለ ከ.ደ.ግ/ኤችአይቪ ቅንጅት ደጋፊ ምክንያቶች ናቸው፡፡

የቀሩት የ ተ.ት.ም.ማ ውቅሮች የ ከ.ደ.ግ/ኤችአይቪ ቅንጅት ላይ ተጽእኖ ከማሳደር ረገድ ምንም አይነት አስተዋጽኦ አልነበራቸውም፡፡

ማጠቃለያ

ተ.ት.ም.ማን በመጠቀም ከ.ደ.ግ/ኤችአይቪ ቅንጅት ላይ ያሉ እንቅፋቶች ሊቃኑ የሚችሉ መሆናቸውን ያሳየን ሲሆን፣ የ ከ.ደ.ግ/ኤችአይቪ ቅንጅት ለህምመተኞች፣ ለጤና አገልግሎት አቅራቢዎች እና ለአስተዳዳሪዎች ጠቃሚ ነው፡፡

ከ ኤ.ጋ.የ.ሰን የ ከ.ደ.ግ እንክብካቤ አገልግሎቶች የማግኘት እድልን ለማሻሻል፣ የጤና ሲስተም ማጠናከሪያ ዘዴን በመጠቀም እንቅፋቶችን መወጣት እና ደጋፊ ምክንያቶች ላይ ደግሞ ጠንክሮ መስራትን ያስፈልጋል፡፡

እነዚህ ግኝቶች አነስተኛ እና መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሃገራት አውዶች ጋር ተስማሚ የሆኑ የከ.ደ.ግ/ኤችአይቪ ቅንጅት ጣልቃ ገብነቶችን ለመቅረጽ ጥሩ መረማመጃ ድልድዮች ናቸው፡፡


ሁለቱም ኤችአይቪ እና ከፍተኛ የደም ግፊት ያለባቸው ኡጋንዳዊያን የሚገባውን እንክብካቤ እያገኙ አይደለም፡፡

ምርምሮች እንደሚያሳዩት፣ የኤችአይቪ ክሊኒኮች በከፍተኛ የደም ግፊት የሚሰቃዩ ታማሚዎችን ለመንከባከብ በቂ ግብአቶች እና ባለሞያዎች የሏቸውም፡፡

በኡጋንዳ ከኤችአይቪ ጋር የሚኖሩ ሰዎችን፣ ከፍተኛ የደም ግፊት ወይም ደም ብዛት ከ3 አዋቂዎች 1ሰውን ያጠቃል፡፡

በእነዚህ ሁለት የጤና ሁኔታዎች በአንድላይ የሚሰቃዩ ሰዎች ወደ ሆስፒታል መደበኛ ጉብኝት ማድረግ ስላለባቸው፣ ተመራማሪዎች አሁን ላይ ያሉ የኤችአይቪ ክሊኒኮች ከፍተኛ የደም ግፊት ያለባቸውን ታማሚዎች ወደሌላ ቦታ ከሚልኩ ይልቅ ከፍተኛ የደም ግፊትንም ቢመረምሩ እና ቢያክሙ ትርጉም ይሰጣል ይላሉ፡፡

በሚያሳዝን ሁኔታ፣ ብዙ የኤችአይቪ ክሊኒኮች አሁንም ከፍተኛ የደም ግፊት እንክብካቤን እየሰጡ ካሉት የኤችአይቪ አገልግሎቶች ጋር አልተቀናጁም፡፡

ተመራማሪዎች በምስራቅ ኡጋንዳ የተቀናጀ እንክብካቤ ለምን እንደሚሰራ ወይም እንደማይሰራ መርምረዋል፡፡

ተግዳሮቶቹን በሚገባ መረዳት ከፍተኛ የደም ግፊት እና የኤችአይቪ እንክብካቤን በተሻለ መልኩ ለማቀናጀት የሚረዱ መንገዶችን ለመቅረጽ ያግዛል፡፡

በኤችአይቪ ክልኒኮች ለጤና አገልግሎት ባለሞያዎች እና ከሁለቱም ከኤችአይቪ እና ከከፍተኛ የደም ግፊት ጋር ለሚኖሩ ታማሚዎች ቃለመጠይቅ አድርገዋል፡፡

የጤና አገልግሎት ጣልቃ ገብነቶችን ለማሻሻል ምላሾቻቸውን የተለመዱ ሳይንሳዊ ዘዴዎችን በመጠቀም ገምግመዋል፡፡

የኤችአይቪ ክሊኒኮች የተካነ የሰው ሃይል እና እንደ የደም ግፊት መለኪያ ማሽኖች እና መድሃኒቶች ያሉ ግብአቶች እንደሌሏቸው አግኝተዋል፡፡

ታማሚዎች ደግሞ በኤችአይቪ ክሊኒኮች ውስጥ ለሁለቱም በሽታዎች የጤና አገልግሎት ማግኘት እንደሚቻል አያውቁም ነበር፡፡

ሌሎች ተመራማሪዎች አፍሪካ እንዴት ከፍተኛ የደም ግፊትን እና የኤችአይቪ እንክብካቤን ማቀናጀት እንደምትችል አጥንተዋል፡፡

ነገር ግን ከላይ የተጠቀሰው የተጠናከረ የትግበራ ምርመራ ማእቀፍ (ተ.ት.ም.ማ) የተባለው መደበኛ ሳይንሳዊ ዘዴ በተለይ ችግሩ ላይ ያተኮሩ መፍትሄዎችን ለማምጣት ጥቀም ላይ ሲውል የመጀመሪያው ነው፡፡

ነገር ግን ተመራማሪዎቹ በጥናታቸው፣ ብዙ ታማሚዎች ከዛሬ በፊት ማንም ስላላስተዋወቃቸው ስለ ኤችአይቪ-ከፍተኛ የደም ግፊት የተቀናጀ እንክብካቤ ምንም ግንዛቤ እንዳልነበራቸው አሳስበዋል፡፡

ይህ ማለት ደግሞ አብዛኛዎቸ ሰዎች ላቃለመጠይቅ ጥያቄዎች ተገቢ መልስ መስጠት አልቻሉም ነበር ማለት ነው፡፡

ስለዚህ ወደፊት የሚደረጉ ምርምሮች የታማሚዎች አመለካከቶች ላይ ማተኮር እንዳለባቸው ይመክራሉ፡፡

በተጨማሪም የተቀናጀ የከፍተኛ ደም ግፊት እና የኤችአይቪ እንክብካቤን ጥቅሞች እና ገዳቶች ለማነጻጸር ተጨማሪ ጥናቶች ያስፈልጋሉ ብለዋል፡፡

የኡጋንዳ እና ሌሎች የአፍሪካ የጤና ባለስልጣናት ከዚህ ምርምር የተገኙትን ግንዛቤዎች የተቀናጀ የከፍተኛ የደም ግፊት እና የኤችአይቪ አንክብካቤን ለመቅረጽ ሊጠቀሙባቸው ይችላሉ፡፡

በእንዲህመሰልጣልቃገብነቶችበከፍተኛየደምግፊትምክንያትየሚከሰቱእናልናስቀራቸውየምንችላቸውንሞቶችማጥፋትይችላል፤ይህምየሚሆነውታማሚዎችለኤችአይቪአገልግሎትለማግኘትበሚሄዱበትጊዜበቶሎበሽታውመኖሩስለሚታወቅእናመታከምስለሚችልነው፡፡

Connections
1 of 5
Comments
0
comment
No comments here
Why not start the discussion?