Skip to main content
SearchLoginLogin or Signup

ባዮቻር እና ማዳበሪያን አደባልቆ መጠቀም በከፍተኛ ደረጃ በአየር የተጠበሰውን የባህር ዳርቻ የሳቫና አፈር ጥራት ማሻሻል ይችላል?

Amharic translation of DOI: 10.1016/j.heliyon.2021.e07089

Published onApr 04, 2023
ባዮቻር እና ማዳበሪያን አደባልቆ መጠቀም በከፍተኛ ደረጃ በአየር የተጠበሰውን የባህር ዳርቻ የሳቫና አፈር ጥራት ማሻሻል ይችላል?
·

ባዮቻር እና ማዳበሪያን አደባልቆ መጠቀም በከፍተኛ ደረጃ በአየር የተጠበሰውን የባህር ዳርቻ የሳቫና አፈር ጥራት ማሻሻል ይችላል?

ከሰሃራ በታች አፍሪካ የአፈር ለምነት መቀነስ ለሰብል ምርት ትልቅ ገደብ ነው፡፡

ባዮቻር እና ማዳበሪያን መጨመር በአፈር ለምነት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እንዳለው በብዙ ጸሃፊዎች ተዘግቧል፡፡

በዚህ ጥናት 120ግ ናሙናዎችን በመጠቀም የ30 ቀን በላብራቶሪ የመቀፍቀፍ ሙከራ ተደርጓል፡፡ ለዚህም በበቆሎ እሸት ባዮቻር (በባዮ)፣ በሩዝ ቅርፊት ባዮቻር (ሩባዩ)፣ በኮኮናት ቅርፊት ባዮቻር (ኮኮ300 እና ኮኮ700) ወይም በዶሮ እርባታ ብስባሽ ማዳበሪያ (ማዳበሪያ) እና በህብረት ማዳበሪያ የሩዝ ቅርፊት ባዮቻር (rcocomp) ወይም በህብረት ማዳበሪያ የበቆሎ እሸት ባዮቻር (cococomp) የተሻሻለ ሃፒሊክ አርኪሶል በቅደም ተከተል በ 1% w/w ማሻሻያ፡አፈር

በጥናቱ የዋሉ ሌሎች ህክምናዎች የሚከተሉት ናቸው፡ የዶሮ እርባታ ብስበባሽ ማዳበሪያ እና የበቆሎ እሸት ባዮቻር ወየም የሩዝ ቅርፊት ባዮቻር ( በቅደም ተከተል 1% ማዳበሪያ + 1% ባዮቻር፡ 1% አፈር w/w) ፡፡ ይህም በመሰረታዊ የአፈር ትንፈሳ ላይ ያላቸውን ተጽእኖ ለመመርመር ፣ በአፈር ፒኤች፣ የአፈር ረቂቅ ተህዋሲያን ካርቦን፣ የካታዩን የልውውጥ አቅም፣ ጠቀልላላ ኦርጋኒክ ካርቦን እና ጠቅላላ ናይትሮጅን እና የሚገኘው የናይትሮጅን ውፍረታ፡፡

ካልተሻሻለው የመቆጣጠሪያ ናሙና ጋር ሲነጻጸር ባዮቻር እና ማዳበሪያ በተናጥል ወይም በአንድላይ ሲጨመሩ እና የዳበረ ባዮቻር የአፈርን ፒኤች ከ0.28 ወደ 2.29 የፒኤች ክፍሎች ከፍ አድርገውታል፡፡

ከብቸኛ ማዳበሪያ መሰረታዊ ትንፈሰ ወይም ከዳበረ የሩዝ ቅርፊት ወይም ከበቆሎ እሸት ባዮቻር ወይም ከተቀላቀለ ባዮቻር እና ማዳበሪያ ካልተሻሻለው የመቆጣጠሪያ ናሙና ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ ነበር፡፡ ይህ ደግሞ ባዮቻርን ብቻ ከተጠቀመው ህክምና ጋር ይመሳሰል ነበር፡፡

በብቸኛ ማዳበሪያ እና በተቀላቀለ የበቆሎ እሸት ባዮቻር እና የማዳበሪያ ህክምና ውስጥ ያለው TOC ከመቆጣጠሪያ ናሙናው ጋር ሲነጻጸር በቅደም ተከተል 37% እና 117% ከፍ ያለ ነበር፡፡

የተቀላቀለ የሩዝ ቅርፊት ባዮቻር እና ማዳበሪያ መጨመር ከመቆጣጠሪያ ናሙናው ጋር ሲነጻጸር MBCን በ132% ከፍ ያደረገው ሲሆን ብቸኛ ማዳበሪያ መጨመር ደግሞ MBCን በ247% በቅደም ተከተል ጨምሮታል፡፡

ባጠቃላይ ጥናቱ በተናጠል ወይም አቀላቅሎ ማዳበሪያ እና ባዮቻርን መጨመር ወይም የዳበረ ባዮቻር የሚከተሉትን የአፈር መለኪያዎች አሻሽሏል፡ የአፈር ፒኤች እና MBC እና የአፈር ርጉነትCን እና TOCን፤ እንዲሁም በመሰረታዊ ትንፈሳ የአፈርC ማጣትን ቀንሷል፡፡


ባዮቻር እና ማዳበሪያ ለሰብሎች የአፈር ጥራትን ያሻሽላሉ፡፡

ይሄ ጥናት ባዮቻር እንዴት ከተጣለ ስብስብ-ህይወት የተሰራ እና በጣም ርጉ እና በካርቦን የበለጸገ ቁስ አካል እንደሆነ የመረመረ ሲሆን የከሰሃራ በታች አፍሪካ የአፈር ጥራትን ለማሻሻል ጥቅም ላይ መዋል ይችላል፡፡

ባዮቻር ከሌሎች በጣም ውድ እና በቀላሉ ከማይገኙ አማራጮች እኩል የአፈርን ጥራት ማሻሻል እንደሚችል ጥናቱ አግኝቷል፡፡

ከሰሃራ በታች ያሉ የአፍሪካ የሰብል ምርቶች ከሚጋፈጧቸው ችግሮች መካከል አንዱ እና ዋንኛው የአፈር ለምነት መቀነስ ነው፡፡

የተሻለ የአፈር ጥራት ወደተሻለ የሰብል ምርት ያመራል፡፡ ይህም የገጠር ድህነትን ይቀንሳል፤ የተፈጥሮ ሃብት መመናመንንም ይቀለብሳል

ምርምሩ እንዳሳየው በጣም ርጉ እና በካርቦን የበለጸገው ቁስ አካል ባዮቻር የአፈር ለምነትን ለማሻሻል ጥቅም ላይ መዋል ይቻላል፡፡

ባዮቻር ዝቅተኛ ወይም ምንም ኦክሲጅን በሌለበት ጊዜ ኦርጋኒክ ቁስ አካልን ወይም ስብስብ-ህይወትን በማሞቅ የሚገኝ ተጓዳኝ ውጤት ነው፡፡

ባዮቻር የአፈር ንጣፍ ስፋትን፣ ውሃን እና የአየር አቅርቦትን እንደሚጨምር እና ረቂቅ ተህዋስያንን እንደሚያነቃቃ ታይቷል፡፡

ይህ ጥናት ባዮቻር እና ማዳበሪያ የአፈር ጥራት ላይ ያላቸውን ተጽእኖ እንደ አፈር ትንፈሳ፣ የአፈር ፒኤች፣ የረቂቅ ተህዋስያን መኖር እና የካርቦን እና የናይትሮጅን መጠን የመሳሰሉ አመላካቾችን በመጠቀም ፈትኗል፡፡

ተመራማሪዎቹ ግይታዊ ፍርሰትን በመጠቀም ኦክሲጅን በሌለበት ጊዜ ኦርጋኒክ ቁስ አካልን በ450 ዲ.ሴ በሃገር ውስጥ በተመረተ ምድጃ በማሞቅ የበቆሎ እሸት፣ የኮኮናት እና የሩዝ ቅርፊት ባዮቻርን አምርተዋል፡፡

ተመራማሪዎቹ ግይታዊ ፍርሰትን በመጠቀም የኮኮናት ቅርፊት ባዮቻርን በ300 እና በ700 ዲ.ሴ አምርተዋል፡፡

ከዛ ተመራማሪዎቹ ከባዮቻር ጋር የተደባለቁ የአፈር ናሙናዎችን ለ30 ቀናት ቀፍቅፈዋል፡፡

ሁሉም ናሙናዎች በጥንቃቄ የተዘጋጀ እና ሃፕሊክ አክሪሶል የተሰኘ አፈር ይዘው ነበር፡፡ ይህም ከተለያዩ ከበቆሎ እሸት፣ ከሩዝ እና ከኮኮናት ቅርፊት እና ከዶሮ እርባታ ብስባሽ ማዳበሪያ የተሰሩ የባዮቻር ድብልቆች ጋር የተቀላቀለ ነበር፡፡

ሌሎች ናሙናዎች ደግሞ የዶሮ እርባታ ብስባሽ ማዳበሪያ እና የአፈር ድብልቅን ከሩዝ ቅርፊት ባዮቻር እና ከበቆሎ እሸት ባዮቻር ጋር በቅደም ተከተል ይዘው ነበር፡፡

ተመራማሪዎቹ እያንዳንዱ ድብልቅ በአፈር ጥራት ላይ ያለውን ተጽእኖ ማጥናት እንዲችሉ ሁሉም ናሙናዎች 1 % ማዳበሪያ እና 1 % ባዮቻር ይዘው ነበር፡፡

ተመራማሪዎቹ ካልተቀላቀለ አፈር ጋር ሲነጻጸር፣ ባዮቻር እና ማዳበሪያ አፈር ውስጥ በተናጠል ወይም በአንድላይ መጨመር የአፈሩን የፒኤች መጠን ከ0.28 ወደ 2.29 የፒኤች ክፍሎች እንደሚያሳድገው ደርሰውበታል፡፡

ፒኤች ጨመረ ማለት የአፈሩ አሲዳማነት ቀነሰ ማለት ነው፡፡

ጥናቱ መሰረታዊ ትንፈሳ ወይም በአፈር የሚለቀቀው የካርቦን ዳዮክሳይድ መጠን ማዳበሪያ ለብቻው ወይም ማዳበሪያ ከሩዝ ቅርፊት ጋር ተቀላቅሎ ወይም የበቆሎ እሸት ባዮቻር እና ሌሎች ድብልቅ ባዮቻሮች ሲጨመርበት ከፍ እንደሚል አግኝቷል፡፡

የአፈር ናሙናዎቹ ማዳበሪያ ለብቻው ሲጨመርባቸው መላው የኦርጋኒክ ካርቦን ይዘታቸው የ37% እድገት አሳይቷል፤ ከማዳበሪያ ጋር የበቆሎ እሸት ባዮቻር ሲቀላቀል ደግሞ የ117% እድገት አምጥተዋል፡፡

አፈሩ ማዳበሪያ ብቻ ካለው አፈር የ247% እድገት ጋር ሲነጻጸር፣ ማዳበሪያ እና የሩዝ ቅርፊት ባዮቻር ድብልቅ ሲጨመርበት የረቂቅ ተህዋስያን እንቅስቃሴ በ132% ጨምሯል፡፡

የዚህ ምርምር ውጤት የሚያሳየው በርካሽ እና በቀላሉ የሚገኘውን ባዮቻር በመጠቀም የአፈርን አሲዳማነት መቀነስ እንደሚቻል ነው፡፡

ይሄ ከሰሃራ በታች አፍሪካ ላሉ ባለአነስተኛ ይዞታ ገበሬዎች ውድ እና በቀላሉ የማይገኘውን አፈርን የማጋህየት አማራጭ ጋር ይጻረራል፡፡

Connections
1 of 5
Comments
0
comment
No comments here
Why not start the discussion?