Skip to main content
SearchLoginLogin or Signup

የግብጽ ተመራማሪዎች ኮቪድ-19ን ለመመርመር እና ለማከም የሚረዳ የኮምፒውተር ሞዴልን እንደ ሃሳብ አቅርበዋል፡፡

Amharic translation of DOI: 10.1101/2020.04.16.20063990

Published onAug 14, 2023
የግብጽ ተመራማሪዎች ኮቪድ-19ን ለመመርመር እና ለማከም የሚረዳ የኮምፒውተር ሞዴልን እንደ ሃሳብ አቅርበዋል፡፡
·

የኮቪድ-19 ታማሚዎች ለህክምና የሚሰጡት ምላሽ  የምርመራ እና የትንበያ ሞዴል፣ ውስብስብ ነርቫዊ አውታረ መረቦችን እና የዌል ኦፕቲማይዜሽን አልጎሪዝም ላይ የተመሰረቱ የሲቲ ምስሎችን በመጠቀም

የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሸኝ በመላው አለም በከፍተኛ ሁኔታ ተሰራጭቷል፡፡

የአለም ጤና ድርጅት (አ.ጤ.ድ) የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) አለም አቀፍ ወረርሸኝ መሆኑን አስታውቋል፡፡

የትክክለኛ-ሰአት የቅልበሳ ቅጂ ፖሊመሬዝ ሰንሰለት ምላሽ (ቅ.ቅ-ፖ.ሰ.ም) በኮቪድ-19 የመጀመሪያ ደረጃ ላይ ዝቅተኛ የአዎንታ እና የትብነት ተመን አለው፡፡

ከዚህ የተነሳ በኮምፒውተር የተሰራ ቶሞግራፊ (ሲቲ) ምስል ለምርመራ ጥቅም ላይ ይውላል፡፡

በ ሲቲ ስካን ሲታይ ከሌላ አይነት የቫይረስ ሳምባ ምቾች ይልቅ ኮቪድ-19 የተለያዩ ቁልፍ ምልክቶች አሉት፡፡

እነዚህ ምልክቶች በአሸዋ እንደተገረፈ መስታወት ደብዛዛ እይታን፣ማጠናከሪያዎችን ፣እና የማይጨበጡ አካሄዶችን ያካትታሉ፡፡

በዚህ ጽሁፍ ውስጥ ለኮቪድ-19 ምርመራ እና ትንበያ ታካሚው ለህክምናው ለሚኖረው ምላሽ (AIMDP) በአርተፊሻል ኢንተሊጀንስ ላይ የተመሰረተ ሞዴል እንደ ሃሳብ ቀርቧል፡፡

AIMDP ሞዴል በሁለት የታቀዱ ሞጁሎች ውስጥ የተንጸባረቁ፣ የምርመራ ሞጁል (ም.ሞ) እና የትንበያ ሞጁል (ት.ሞ) የተሰኙ ሁለት ዋና ዋና አገልግሎቶች አሉት፡፡

የምርመራ ሞጁል (ም.ሞ) በኮቪድ-19 የተያዙትን ታማሚዎች ቀደም ብሎ እና በትክክል ለማወቅ እና ከሲቲ ስካኖች የተገኙ የኮቪድ-19 ምልክቶችን በመጠቀም ከሌሎች የሳምባ ምች ቫይረሶች ለመለየት እንደ አማራጭ የቀረበ ነው፡፡

የምርመራ ሞጁል (ም.ሞ)፣ ውስብስብ ነርቫዊ አውታረ መረቦችን ( ው.ነ.አ.መ)  እንደ ጥልቅ የመማሪያ ቴክኒክ፣ ለመከፋፈል እና የኮቪድ-19 ምርመራን ለማፋጠን በመቶዎች የሚቆጠሩ የሲቲ ምስሎችን በሰከንዶች ውሰጥ ለማካሄድ ይጠቀምባቸዋል፤ እንዲሁም በውስጥ አያያዙ የበኩሉን አስተዋጽኦ ያደርጋል፡፡

በተጨማሪም አንዳንድ ሃገሮች ለሁሉም ታካሚዎች የህክምና እና የጽኑ እንክብካቤ አገልግሎት የመስጠት አቅም ስለሌላቸው ምላሽ ለሚሰጡ ታካሚዎች ብቻ ህክምና መስጠት ግዴታ ይሆናል፡፡

በዚህ አውድ ውስጥ፣ የትንበያ ሞጁል (ት.ሞ) የተለያዩ ምክንያቶችን ፣ለምሳሌ፣ እድሜ፣ የኢንፌክሽን ደረጃ፣ የመተንፈሻ አካላት ውድቀት፣የብዝሃ-አባላካል ውድቀት እና  የህክምናውን ስርአቶች መሰረት በማድረግ ፣ የታካሚውን ለህክምና ምላሽ የመስጠት አቅምን ለመተንበይ እንደ አማራጭ ቀርቧል፡፡

ት.ሞ እጅግ ወሳኝ የሆኑትን የታካሚ ባህሪያትን ለመምረጥ  የዌል ኦፕቲማይዜሽን አልጎሪዝምን ይጠቀማል፡፡

የሙከራ ውጤቶቹ በመቶዎች የሚቆጠሩ ትክክለኛ መረጃዎችን እና የሲቲ ምስሎችን በመጠቀም ለቀረቡት የምርመራ እና የትንበያ ሞጁሎች ተስፋ ሰጪ ክንዋኔን ያሳያሉ፡፡


የግብጽ ተመራማሪዎች ኮቪድ-19ን ለመመርመር እና ለማከም የሚረዳ የኮምፒውተር ሞዴልን እንደ ሃሳብ አቅርበዋል፡፡

ተመራማሪዎች እየጀመረ ያለ- ኮቪድ-19ን በበለጠ ፍጥነት እና በከፍተኛ ትክክለኛነት ለመመርመር የሙከራ የኮምፒውተር ፕሮግራም ፈጠሩ፡፡

እንዲሁም አንድ በሽተኛ በህክምና ምን ያህል ማገገም እንደሚችል ለመተንበይ ሞዴል አዘጋጅተዋል፡፡

ኮቪድ-19ን የሚያስከስተው የመተንፈሻ አካል ቫይረስ፣ሳርስ-ኮቫ-2፣ በ2020 በፍጥነት ተሰራጭቶ አለም አቀፍ  የኮቪድ-19 ወረርሽኝን አስከትሏል፡፡

የቅልበሳ ቅጂ ፖሊመሬዝ ሰንሰለት ምላሽ (ቅ.ቅ-ፖ.ሰ.ም)  ሙከራ ኮቪድ-19ን  ለመመርመር በጣም ትክክለኛ ከሆኑት ሙከራዎች አንዱ ነው፡፡

ነገር ግን በመጀመሪያዎቹ የኢንፌክሽን ደረጃዎች ላይ ትክክል ላይሆን ይችላል፡፡

በኮምፒውተር የተሰራ ቶሞግራፊ (ሲቲ) ስካኖች እየጀመረ ያለ-ኮቪድ-19ን ለመመርመር የበለጠ ትክክለኛ ይመስላሉ፤ነገር ግን ስካኖቹ በሰው ባለሞያዎች መተንተን አለባቸው፡፡

ሆስፒታሎች በብዛት በኮቪድ-19 በሽተኞች ይጨናነቁ ስለነበር የህክምና ባለሞያዎች ሁሉንም ለማከም የሚያስችል ግብአት አልነበራቸውም፡፡

የዚህ ጥናት ጸሃፊዎች “የማሽን ትምህርት” የተሰኘ ቴክኖሎጂን መጠቀም ፈልገው ነበር፡፡ይህም ፊት ለፊት ተጋፋጭ ባለሞያዎች ያሉትን አናሳ ግብአቶች በመጠቀም የኮቪድ-19 ታማሚዎችን ከሲቲ ስካኖች በመለየት በጣም በቀላሉ ሊድኑ የሚችሉትን ታማሚዎች ማከም ያስችላቸዋል፡፡

የኮምፒውተር ፕሮግራሙን ኮቪድ-19ን ከሲቲ ስካኖች እንዴት መመርመር እንደሚችል ለማሰልጠን እና አንድ በሽተኛ ለህክምናው ጥሩ ምላሽ ይሰጥ እንደሆነ ለመተንበይ እውነተኛ የኮቪድ-19 ታካሚ መረጃን መጠቀም ፈልገው ነበር፡፡

እንዲሁም ሲቲ ስካኖችን በመጠቀም የኮቪድ-19 ምርመራዎችን የማድረግ ፍጥነትን እና ትክከለኛነት መጨመር ፈልገው ነበር፡፡

እነዚህ ተመራማሪዎች የኮቪድ-19 በሽታን መመርመር እንዲሰለጥን እና የህክምና አማራጮችን እንዲያቀረብ ለማድረግ የኮምፒውተራቸውን ፕሮግራም ( እንደ ሲቲ ስካኖች፣ የቅ.ቅ-ፖ.ሰ.ም ሙከራ ውጤቶች፣እና ሙሉ የደም ቆጠራ) ያሉትን የታካሚ መረጃዎች ያስገቡበታል፤ ሁሉም ግን የሚመሰረቱት ከዚህ ቀደም በሽተኞችን ለይተው ካወቁ እና ካከሙ የሰው ባለሙያዎች ልምድ በመነሳት ነው፡፡

ተመራማሪዎቹ ፕሮግራማቸው 97% ትክክለኛ እና ከሲቲ ስካን በ20 ሰከንድ ውስጥ ትንበያን መስጠት የሚችል ነው ይላሉ፡፡

ሌሎች ተመራማሪዎች የተለያዩ የመረጃ ስብስቦችን በመጠቀም ማሳካት ከቻሉት በበለጠ ፕሮግራማቸው በአጭር ጊዜ ውስጥ ትክክለኛ ትንበያዎችን እንደሚፈጽምም ተናግረዋል፡፡

ሌሎች የምርመር ቡድኖች ሲቲ ስካኖችን እና የማሽን ትምህርትን በመጠቀም የኮቪድ-19 በሽታን ስለመመርመር ተመልክተዋል፡፡

በሚያሳዝን ሁኔታ በእነዚያ ጥናቶች የማሽኑ ሞዴሎች የሰው ባለሙያዎች በሚያደርጉት መንገድ ምርመራቸውን ማብራራት አልቻሉም፤ አብዛኛውን ጊዜ በቀላሉ የምርመራውን ውጤት ብቻ ይሰጣሉ፡፡

በዚህ ጥናት ተመራማሪዎቹ ኮምፒውተሩ ምርመራውን ለማድረግ ምን አይነት ሲቲ ስካን እንደሚጠቀም በማጉላት ችግሩን ለመፍታት ሞክረዋል፡፡

ተመራማሪዎቹ ውጤታቸውን ለማረጋገጥ ይህንን ሞዴል በተጨማሪ መረጃዎች ላይ ለመሞከር አቅደዋል፡፡

እንዲሁም የኮቪድ-19 በሽታ ያለባቸው ታማሚዎች ምን ያህል እንደታመሙ የሚተነብይ አዲስ ሞዴል ለመስራት አቅደዋል፡፡

ይህም ዶክተሮች በሽተኛን እንዴት በተሻለ ሁኔታ ማከም እንዳለባቸው ለመወሰን እንደሚረዳቸው ተናግረዋል፡፡

ከተጨማሪ ምርምር ጋር አንድ ላይ በመሆን ይህ የግብጻውያኑ የምርምር ቡድን ሀሳብ፣ ብዙ ዶክተሮች የኮቪድ-19 በሽተኞችን በሚያክሙበት ጊዜ አነስተኛ ግብአቶችን በሚገባ እንዲያስተዳድሩ ሊረዳቸው ይችላል ፡፡

ነገርግንየእነሱቴክኒኮችበአንጻራዊደረጃእንደሲቲማሽኖችእናየላቁኮምፒውተሮችያሉከፍተኛደረጃያላቸውመሰረተልማቶችንይጠይቃሉ፤ይህምበብዙየአፍሪካቦታዎችላይገኝይችላል፡፡

Connections
1 of 5
Comments
0
comment
No comments here
Why not start the discussion?