Description
This is a lay summary of the article published under the DOI: 10.1101/2020.01.10.901470
Amharic translation of DOI: 10.1101/2020.01.10.901470
የስምጥ ሸለቆ ትኩሳት (ስ.ሸ.ት.)በአንዳንድ የዓለም ክልሎች ብቅ ያለ እና እንደገና ብቅ እያለ ያለ የእንስሳት እና ሰዎችን የሚያጠቃ የዙኖቲክ በሽታ ነው።
ባለ አንድ ሻኛ ግመሎች በአፍሪካ ውስጥ ለመጎተት፣ ለማጓጓዣ እና ለምግብነት የሚያገለግሉ ጠቃሚ የኢኮኖሚ የእንስሳት ዝርያዎች ናቸው።
ክልላዊ እና ዓለም አቀፋዊ ንግድ ይህ በሽታ በሰፊው እየተስፋፋ እና አስከፊ ኢኮኖሚያዊ እና የህዝብ ጤና ውድመት በተጠቁ አካባቢዎች ላይ እያስከተለ አደጋው እንዲያድግ ማድረጉን ቀጥሏል።
እነዚህ አደጋዎች ቢኖሩም በናይጄሪያ ውስጥ በግመሎች ውስጥ ስለ ስ.ሸ.ት. ሁኔታ መረጃ እጥረት አለ።
ይህ ጥናት የተካሄደው በናይጄሪያ ውስጥ በባለ አንድ ሻኛ ግመሎች ላይ የስ.ሸ.ት. ቫይረስ ስርጭትን ለመለካት እና ከበሽታው ጋር ተያይዘው የሚመጡትን አደጋዎች ለመለየት ተነስቷል።
በጂጋዋ እና ካትሲና ግዛቶች በሰባት የአካባቢ መስተዳድር አቅራቢያዎች በቀላል የዘፈቀደ ናሙና ክፍል በክፍል ጥናት ተካሂዷል።
ከግመሎች የተገኘው እዥ ለፀረ-ስ.ሸ.ት.ቫ.IgG ተፈትሿል።
የግመል ባለቤቶች እውቀታቸውን፣ አመለካከታቸውን እና ተግባራቸውን ለማረጋገጥ የተዋቀረ መጠይቅ ተሰጥቷቸዋል።
አጠቃላይ ስርጭት 19.9% (95% CI; 17.07-22.90) ተመዝግቧል።
በእድሜ ምድቦች ላይ በመመስረት ከፍተኛው የ20.9% (95% CI; 17.00-25.31) በትላልቅ ግመሎች (6-10 ዓመት እድሜ) መካከል ተገኝቷል፤ በሴት ግመሎች ደግሞ 20.4% ከፍተኛ ስርጭት ተመዝግቧል (95%CI; 15.71-25.80)።
ሱሌ ታንካር-ካር በጂጋዋ ግዛት በ33% (95%CI; 1.31-4.72, p= 0.007) እና OR 2.47 ከፍተኛውን ስርጭት ሲያስመዘግብ ማይአድዋ ደግሞ በካትሲና ግዛት 24.7% (95%CI; 0.97-2.73, p=0.030) በ OR 1.62 አስመዝግቧል።
ከስጋት ካርታው ከኒጀር ሪፐብሊክ ጋር የሚዋሰኑ የአካባቢ መስተዳደር አቅራቢያዎች ለስ.ሸ.ት. ከፍተኛ ስጋት ላይ ነበሩ።
ከፍተኛ የዝናብ መጠን ብቻ ከስ.ሸ.ት. በግመል አርብቶ አደር ዘላኖች መካከል ከተከሰተው ክስተት ጋር በእጅጉ የተገናኘ አልነበረም (95%CI 0.93-5.20; p=0.070)።
የስምጥ ሸለቆ ትኩሳት (ስ.ሸ.ት.)በግመሎች ላይ ጥገኛ የሆኑትን ናይጄሪያዊያንን ጤና እና ኢኮኖሚ ሊያቃውስ ይችላል።
ተመራማሪዎች በክልሉ ውስጥ የዚህን በሽታ ስርጭት ካርታ ወስደዋል እና እንስሳትን ይዞ ድንበር መሻገር ትልቁን የመስፋፋት አደጋ ያመጣል ይላሉ።
ባለ አንድ ሻኛ ግመሎች በአፍሪካ ውስጥ ለመጎተት፣ ለማጓጓዣ እና ለምግብነት የሚያገለግሉ ጠቃሚ የኢኮኖሚ የእንስሳት ዝርያዎች ናቸው፤ ነገር ግን እንደ ሰው ልጅ እና ሌሎች እንስሳት ለገዳዩ የቫይረስ ፍስተደም ትኩሳት ማለትም ለስ.ሸ.ት. ተጋላጭ ናቸው።
በሽታውን የሚያስፋፋው ክልላዊ እና ዓለም አቀፋዊ ንግድ በናይጄሪያ በግመሎች ላይ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ እና የህዝብ ጤና ውድመት አስከትሏል።
እንደ አለመታደል ሆኖ፣ በአብዛኛዎቹ የአፍሪካ ሀገሮች ለስ.ሸ.ት. የሚደረገው ክትትል ውስን ሲሆን ወረርሽኙ ሳይስተዋል እና በተሳሳተ ምርመራ እንዲሁም በቂ ሪፖርት ሳይደረግ ሊቀር ይችላል።
እንዲያውም፣ ምንም እንኳን ቫይረሱ በተለያዩ የእንስሳት ዝርያዎች ውስጥ በእዥ ናሙናዎች ውስጥ ቢገኝም ፣ ናይጄሪያ በአጠቃላይ የስምጥ ሸለቆ ትኩሳት ወረርሽኝ መከሰቱን ሪፖርት አላደረገችም፡፡ነገር ግን ቫይረሱ በግመሎች ውስጥ እስካሁን አልተገኘም፤ ይህ ጥናት በናይጄሪያ ውስጥ በባለ አንድ ሻኛ ግመሎች ላይ የስ.ሸ.ት. ቫይረስ ስርጭትን ለመለካት እና ከበሽታው ጋር ተያይዘው የሚመጡትን አደጋዎች ለመለየት ተነስቷል።
ተመራማሪዎች በጂጋዋ እና ካትሲና ግዛቶች በሰባት የአካባቢ መስተዳድር አቅራቢያዎች ክፍል በክፍል ጥናት አካሂደዋል።
ከግመሎች የእዥ ናሙናዎች ሰብስበው ስ.ሸ.ት. መኖሩን የሚጠቁሙ ፀረ እንግዳ አካላት ፈትሸዋል።
ፀረ-ስ.ሸ.ት. ፀረ እንግዳ አካላት በ19.9% ግመሎች ውስጥ በሁለት ሰሜናዊ የናይጄሪያ ግዛቶች ውስጥ እንደሚገኙ ደርሰውበታል።
እነዚህ ግዛቶች በቅርቡ ወረርሽኝ መከሰቱን ከዘገበው የኒጀር ሪፐብሊክ ጋር ድንበር ይጋራሉ።
ጥናቱ እንዳመለከተው እድሜያቸው ከ6 እስከ 10 ዓመት የሆናቸው ግመሎች ከፍተኛ ስርጭት ሲኖራቸው 20.9% የሚሆኑት ፀረ-ስ.ሸ.ት. ፀረ እንግዳ አካላት በእዥ ናሙናቸው ይገኛሉ።
ተመራማሪዎቹ በሱሌ ታንካር-ካር ውስጥ ያሉ ግመሎች በ33% ስርጭት በስ.ሸ.ት. የመያዝ እድላቸው ካለመያዝ በ2.47 ይበልጣል።
ጥናቱ እንደሚያመለክተው፣ ከፍተኛ ተጋላጭነት ያለው የግመሎች ከናይጄሪያ ወደ ጎረቤት ሀገራት እንዲሁም ተመልሰው ወደ ናይጄሪያ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ መጨመር ነው።
እነዚህ ቁጥሮች እንደ ኒጀር ሪፐብሊክ (47.5%)፣ ሞሪታኒያ (45%) እና ታንዛኒያ (38.5%) ባሉ በሌሎች ሀገሮች ቀድሞ ከተደረጉ ጥናቶች ያነሱ ናቸው።
ቢሆንም ተመራማሪዎቹ ከጎረቤት ሀገራት የሚመጡ እንስሳት እንደ ስ.ሸ.ት. ላሉ ድንበር ተሻጋሪ ተላላፊ በሽታዎች እንዲመረመሩ ናይጄሪያ የኳረንታይን ክፍሎች በድንበሮቿ ላይ ማቋቋም እንዳለበት ተናግረዋል።
Northern Sotho(Sepedi) translation of DOI: 10.1101/2020.01.10.901470
Luganda translation of DOI: 10.1101/2020.01.10.901470
Yoruba translation of DOI: 10.1101/2020.01.10.901470
Hausa translation of DOI: 10.1101/2020.01.10.901470
Zulu translations of DOI: 10.1101/2020.01.10.901470