Skip to main content
SearchLoginLogin or Signup

ፓይሮሬትድ ባዮዲዝልን በመጠቀም የሲቴን አሻሻዮች እና የኢታኖል አሰራር እና ልቀቶች ባህሪያት

This is Amharic translation of DOI: 10.20944/preprints201806.0106.v1

Published onJun 20, 2023
ፓይሮሬትድ ባዮዲዝልን በመጠቀም የሲቴን አሻሻዮች እና የኢታኖል አሰራር እና ልቀቶች ባህሪያት
·

ፓይሮሬትድ ባዮዲዝልን በመጠቀም የሲቴን አሻሻዮች እና የኢታኖል አሰራር እና ልቀቶች ባህሪያት

Abstract

በዝቅተኛ ዋጋ የሚገኙ አማራጭ ነዳጆች፣ ለተፈጥሮ አካባቢ ተስማሚ ስለሆኑ እና የሃይል ፍላጎቶችን ስለሚያሟሉ፣ በአሁኑ ጊዜ ለእነሱ ያለው ፍላጎት እና አጠቃቀም እየጨመረ መጥቷል፡፡

ኢታኖል ከፍተኛ የኦክሲጅን ይዘት ያለው ማራኪ የታዳሽ ሃይል ምንጭ ነው፡፡

ኢታኖል በኢታኖሊስስ ሊመሰረት ይችላል፡፡ ነገር ግን ለዚህ ስራ የተለመደውን ዲዝል ዘይት፣ ከውዳቂ ፕላስቲክ ፕሮሊስስ ዘይት (ባዮ ድፍድፍ ዘይት)፣ ከኢታኖል እና ከኢኖስፔክ ኩባንያ ከተገዛ CI-0808 የንግድ ነዳጅ ማሻሻያ ጋር በቀጥታ ለመቀላቀል ሙከራ ተደርጓል፡፡

የሴቴን ማሻሻያ የተጨመረበት ዋና አላማ የድብልቆቹን የቃጠሎ ባህሪያት ቢያንስ በ1-3 የማቃጠል ጥራት ነጥቦች ለማሻሻል ነው፡፡

አምስት የድብልቅ ንጥጥሮች በሚከተለው ቅደም ተከተል ተመርጠው ነበር፡ 50:25:25, 60: 20:20፣ 70: 15:15፣ 80: 10:10 እና 90: 5:5፣ በቅደም ተከተል፣ ለውዳቂ ፕላስቲክ ፕሮሊሲስ ዘይት (WPPO)፣ ለኤታኖል እና ለተለመደው የዲዝል ዘይት (CD)፡፡

ነገር ግን፣ ለተጨማሪ ነዳጅ ማደባለቂያ ንጥጥር፣ የአጠቃላይ መጠኑ መቶኛ/ፐርሰንቴጅ ታሳቢ የተደረገ ሲሆን፣ ንጥጥሩ ከአጠቃላይ የነዳጅ ድብልቁ መጠን 0.01% ሆኖ ተቀምጦ ነበር፡፡

ለዚህ ስራ WPPO፣ የዲዝል ዘይት ድብልቆች እና ተጨማሪ የነዳጅ ማሻሻያዎች እንደ አማራጭ ነዳጅ ጥቅም ላይ ውለው ነበር፡፡

ይህም በቋሚ ነጠላ ሲሊንደር የቀዘቀዘ ውሃ የሙከራ ዲዝል ዘይት ሞተርን የአፈጻጻም እና የፍልቀት ባህሪዎች ለመገምገም ነው፡፡

CI-0808 የተጨመረው የ CO፣ UHC፣ NOX፣ PM ፍልቀትን ለመቀነስ ባለው አቅም ምክንያት ሲሆን፣ የሞተሩን የመስራት አቅም አሻሽሎታል፡፡

የተገኙት ውጤቶች በጥንቃቄ ከASTM ደረጃዎች ጋር የተወዳደሩ ሲሆን፣ የግራፍ ኩርባ አሃዞችን እና በሰንጠረዥ የተቀመጡ ዋጋዎችን በመጠቀም ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

መደምደሚያውም፣ የኢታኖል እና WPPO ድብልቆች በዲዝል ዘይት ሞተሮች ያለምንም ማሻሻያ እንደአማራጭ ጥቅም ላይ መዋል እንደሚችሉ ነው፡፡

ከሴቴን ማሻሻያዎች ጋር በአንድ ላይ ጥቅም ላይ ሲውሉ፣ ፍልቀቶቹ በከፍተኛ ሁኔታ ይቀንሳሉ፡፡ አፈጻጸሙም ከተለመደው የዲዝል ዘይት ጋር እኩል በሆነ መልኩ ተሻሸሏል፡፡

Summary Title

የዲዘል ዘይት ፍልቀትን ለመቀነስ የውዳቂ ፕላስቲክ ዘይት እና የባዮ ነዳጅ ድብልቅ፡፡

ተመራማሪዎች ነዳጁን ዘላቂነት ካላቸው ተደማሪዎች ጋር በማቀላቀል የዲዝል ዘይት ፍልቀትን ለመቀነስ ችለዋል፡፡

ቅይጡም የኢታኖል ባዮ ነዳጅ እና ከውዳቂ ፕላሰቲክ የተሰራ ዘይት ሲሆን ካንሰርን የሚየስከትሉ ጎጂ ጋዞችን በአነስተኛ ሁኔታ ቢያፈልቅም እንደተለመደው ዲዝል ዘይት ስራውን በሚገባ ያከናውናል፡፡ የተለመደው ዲዝል ዘይት ከማይታደስ ድፍድፍ ዘይት የተሰራ የቅሬተ አካል ነዳጅ በመሆኑ ለቤተ እጽ ጋዞች ፍልቀት ዋነኛ ምክንያት ነው፡፡

የዲዝል ዘይት ሞተሮች ከቤንዚን ሞተሮች ይልቅ ውጤታማ ናቸው ፡፡ሆኖም ግን የሰውን ልጅ በሽታ ላይ የሚጥሉ እና ከባቢውን አየር የሚጎዱ ናይትረስ ኦክሳይድ እና ሌሎችንም አደገኛ ኬሚካሎች በከፍተኛ ሁኔታ ያፈልቃሉ፡፡

ይህ ጥናት መሰረት ያደረገው እንዴት ዘላቂ የነዳጅ ምትኮች እና ተደማሪዎች የዲዝል ዘይት ፍልቀትን ለመቀነስ ሊጠቅሙ እንደሚችሉ መመርመር ላይ ነው፡፡

ጥናቱ፣ እንደገና ጥቅም ላይ ከዋለ ፕላስቲክ ከተሰራ ዘይት በተጨማሪ እንደ እንጨት፤ ጥቅም ላይ ከዋለ (የበሰለ ዘይት) እና ከተጣሉ ባዮማሶች፤ የተሰራ ኢታኖል ባዮ ነዳጅን ለመጠቀም ሃሳብ አቅርቧል፡፡

እነዚህ የነዳጅ አማራጮች በራሳቸው እንደ ዲዝል ዘይት ጥሩ አይደሉም፤ እነሱን ለመጠቀምም ልዩ ሞተሮች መሰራት ይኖርበታል፡፡ነገር ግን ይህ ጥናት የተለመደውን የዲዝል ዘይት ፍልቀት ለመቀነስ እና ይህንን የነዳጅ ቅይጥ በመደበኞቹ የዲዝል ሞተሮች ላይ ለመጠቀም ያለመ ነው፡፡

ተመራማሪዎቹ የተለመደውን ዲዝል ዘይት(CD)፤ ከኢታኖል ነዳጅ (E)፤ እንዲሁም ከውዳቂ ፕላስቲክ ከተሰራ ዘይት ጋር አቀላቅለዋል፡፡

ሞተሩ ብዙ እያቃጠለ አነስተኛ ፍልቀት እንዲኖረው የሚያግዘውን የዲዝል ዘይት ጥራት ለማሻሻል “ሴቴን አሻሻይ” የተባለ ገበያ ላይ የሚገኝ ኬሚካል ጨምረውበታል፡፡

ተመራማሪዎቹ ነጠላ ሲሊንደር ዲዝል ሞተርን በመጠቀም በላብራቶሪ እያንዳንዱን ሞተር በየአንዳንዱ የነዳጅ ቅይጥ ላይ ያለውን አፈጻጸም ፈትነዋል፡፡

በተለመደው ዲዝል ዘይት ብቻም ያለውን ያአሰራር ጥራት አነጻጽረዋል፡፡

ተመራማሪዎቹ ኢታኖልን እና ከውዳቂ ፕላስቲክ የተገኘ ዘይትን፤ ከተለመደው ዲዝል ዘይት ጋር በመቀላቀል ፍልቀትን መቀነስ ብቻ ሳይሆን ደረጃውንም በጠበቀ መልኩ ስራውን ማስቀጠል ችለዋል፡፡

90% የዲዝል ዘይት ቅይጥ፡፡ 5% የውዳቂ ፕላስቲክ ዘይት፡፡ 5% ኢታኖል እንደተለመደው ዲዝል ዘይት በቅልጥፍና ያገለግላል፣ የሚያመነጨው ፍልቀት ግን እጅግ አነስተኛ ነው፡፡

በተጨማሪ፣ እነዚህን አማራጭ የነዳጅ ድብልቆች ከተለመደው የዲዝል ዘይት ጋር መጠቀም የጭስ ማውጫ ሙቀትን እንደማይጨምር አግኝተዋል፡፡ ማለትም፣ የሞተሩ ጤና ላይ አሉታዊ ተጽእኖ አይፈጥርም፡፡

Connections
1 of 5
Comments
0
comment
No comments here
Why not start the discussion?