Skip to main content
SearchLoginLogin or Signup

የማሽን ትምህርትን ከስነ-ስፔክትሮስኮፕ ጋር በማጣመር ወባን መለየት

Amharic translation of DOI: 10.1186/s12936-019-2982-9

Published onJul 26, 2023
የማሽን ትምህርትን ከስነ-ስፔክትሮስኮፕ ጋር በማጣመር ወባን መለየት
·

መካከለኛ ኢንፍራሬድ ስነ-ስፔክትሮስኮፕን እና የሎጂስቲክስ አማካይ ተዛምዶ ትንተናን በመጠቀም በደረቅ የሰው ደም ጠብታ ውስጥ የወባን ጥገኛ ተህዋስያን መለየት

የጀርባ ታሪክ

 በአሁኑ ግዜ፣ የወባ በሽታ ኢፒዴሞሎጂካል ጥናቶች ለፕላስሞዲየም ፋልሲፓረም ኢንፌክሽኖች፣ በማይክሮስኮፕ፣በፖሊመሬስ ሰንሰለት ምላሽ (ፖ.ሰ.ም) ንጥረ-ጥናት ወይም ፈጣን የምርመራ ሙከራ ሽክፎች(ፈ.ም.ሙ.ሽ) ላይ ይተማመናሉ፡፡

ይህ ጥናት መካከለኛ ኢንፍሬርድ(መ.ኢ) ስነ-ስፔክትሮስኮፕ፣ቁጥጥር ከሚደረግበት የማሽን ትምህርት ጋር በጥምረት፣ በቀጥታ ከሰው ከተወሰዱ ደረቅ የደም ጠብታዎች፣ለፈጣን የወባ ምርመራ አማራጭ ዘዴን ያስገኝ እንደሆነ አጣርተዋል፡፡

ስልቶች

 ከተሻጋሪ የወባ በሽታ ጥናት፣ በታንዛኒያ ደቡብ ምስራቅ ካሉ 12 ወረዳዎች በ2018/19 ደረቅ የደም ጠብታዎችን (ደ.ደ.ጠ) የያዙ የማጣሪያ ወረቀቶች ተገኝተው ነበር፡፡

(ደ.ደ.ጠ)ዎቹ ፣ከፍተኛ ጥራት ለማግኘት፣ መ.ኢ ስፔክትራ በ4000ሴ.ሜ-1 ክልል ውስጥ እስከ 500ሴ.ሜ-1አቱኔትድ ቶታል ሪፍሌክሽን-ፎሪየር ትራንስፎርም ኢንፍሬርድ (ATR-FTIR) ስፔክትሮሜትርን በመጠቀም ተቃኝተዋል፡፡

ስፔክትራዎቹ የከባቢ አየር የውሃ ትነትን እና የካርቦን ዳይ ኦክሳይድን ጣልቃ ገብ ጥብጣቦች ለመተካት ጽዱ ነበሩ፤ እንዲሁም፣ የተለያዩ የምደባን ስልተ ቀመሮች በማሰልጠን ፣በወባ የተለከፈን እና ያልተለከፈን ደ.ደ.ጠ መለየት የሚያስችሉ ወረቀት ላይ የተመሰረቱ የ ፖ.ሰ.ም ሙከራ ውጤቶችን እንደ ማጣቀሻ ተጠቅመዋል፡፡

ትንተናው፣ 123 በፖ.ሰ.ም የተረጋገጡ ወባ የተገኘባቸው እና 173 ያልተገኘባቸውን ጨምሮ 296 ግለሰቦችን ከግምት ውስጥ ያስገባ ነበር፡፡

80% የሚሆነውን የዳታ ስብስብ በመጠቀም የሞዴል ስልጠና ተሰርቷል፡፡ ከዚያም በኋላ በጣም ተስማሚ የሆነው ሞዴል 80/20 ክፍልፋይ/ለሙከራ የተሸነሸኑ ክፍሎችን በማስጀመር አመቻችቷል፡፡

የሰለጠኑት ሞዴሎች፣ በ20% የማረጋገጫ ደ.ደ.ጠ ስብስቦች ውስጥ የፕላስሞዲየም ፋልሲፓረምን መገኘት በመተንበይ ተገምግመዋል፡፡

ውጤቶች

 ውጤቶች የሎጂስቲክ መመለሻ፣ምርጡ የአፈጻጸም ሞዴል ነበር፡፡

ፖ.ሰ.ምን እንደ ማጣቀሻ ብንወስድ፣ሞዴሎቹ የፕላስሞዲየም ፋልሲፓረምን ኢንፌክሽኖች በመተንበይ በጠቅላላው 92% በመስክ ከተሰበሰበ ናሙና፣ (በጠቃሽነት = 91.7% ፣ በጥልቅነት ደረጃ = 92.8% ) እና የተቀላቀሉ 85% የፕላስሞዲየም ፋልሲፓረምን ኢንፌክሽኖችን እና ፕላስሞዲየም ኦቫልን በመተንበይ፣ (በጠቃሽነት = 85% ፣ በጥልቅነት ደረጃ = 85% ) ትክክለኛነትን ተቀዳጅተዋል፡፡  

መደምደሚያ

 እነዚህ ውጤቶች፣ መካከለኛ ኢንፍሬርድ ስነ-ስፔክትሮስኮፕ ቁጥጥር ከሚደረግበት የማሽን ትምህርት (መ.ኢ-ማ.ት) ጋር በመጣመር በሰው ውስጥ ካሉ ደ.ደ.ጠ ውስጥ የወባ ጥገኛ ተህዋስያንን ለመመርመር ሊጠቅሙ እንደሚችሉ ያሳያሉ፡፡

አቀራረቡ፣ ፕላስሞዲየምን ክሊኒካል ባልሆኑ መቼቶች (ምሳሌ፤ የመስክ ዳሰሳዎች) እና በክሊኒካል መቼቶች ሁኔታዎችን ለማስተዳደር በሚረዱ ምርመራዎች) ፈጣን እና ከፍተኛ-የማስተላለፍ መመርመሪያ ችሎታ ሊኖረው ይችላል፡፡

ሆኖም ግን፣ አቀራረቡን በስራ ላይ ከማዋላችን በፊት፣ከሌሎች የጥናት ጣቢያዎች ፣የተለዩ ጥገኛ ተህዋስያን ካሉባቸው ህዝቦች እና የባዮሎጂ መሰረት ካላቸው የ መ.ኢ ምልክቶች ጥልቅ ግምገማዎች፣ ተጨማሪ የመስክ ማረጋገጫ ያስፈልገናል፤

የስልተ ቀመሩን ምደባ ማሻሻል እና በትላልቅ የዳታ ስብስቦች ሞዴሎችን ማሰልጠን ፣ የጠቃሽነትን እና የሚስጠርነትንም ደረጃ ሊያሻሽለው ይችላል፡፡

የመ.ኢ-ማ.ት ስነ-ስፔክትሮስኮፕ ስርአት በአካል ጠንካራ፣ዝቅተኛ ዋጋ ያለው እና አነስተኛ ጥገናን የሚጠይቅ ነው፡፡


የማሽን ትምህርትን ከስነ-ስፔክትሮስኮፕ ጋር በማጣመር ወባን መለየት

 ተመራማሪዎች የወባ ኢንፌክሽኖችን ለመመርመር በወቅቱ ካሉት ቴክኒኮች እና የምርመራ ሙከራዎች ይልቅ በቀላሉ የሚገኝ እና የበለጠ አስተማማኝ የሆነ አዲስ ዘዴ ነድፈዋል፡፡

የእነሱ ዘዴ የተመሰረተው መካከለኛ ኢንፍራሬድ ስነ-ስፔክትሮስኮፕ የተባለ ቴክኖሎጂን (መ.ኢ) ከማሽን ትምህርት ጋር በማዋሃድ ነው፡፡

ባለስልጣናት የጤና እንክብካቤ ሃብቶችን ማዘጋጀት እና ጉዳዮችን ማስተዳደር እንዲችሉ፣የወባ ኢንፌክሽኖችን በሁለቱም በሰዎች እና በቢምቢዎች ውስጥ መከታተል ያስፈልጋል፡፡

የአይ ተመራማሪዎች በአሁኑ ጊዜ የወባ በሽታን ለመመርመር በማይክሮስኮፖች፣በ ፖ.ሰ.ም (በፖሊሜራስ ሰንሰለት ምላሽ) ሙከራዎች፣ ወይም በፈጣን የመመርመሪያ ሙከራዎች ይተማመናሉ፡፡ ነገር ግን እነዚህ ዘዴዎች ላያስተማምኑ፣ የብዙ ሰዎችን ጉልበት ሊጠይቁ ወይም በሩቅ እና በገጠራማ አካባቢዎች ላይ ለመተግበር እጅግ ሊወደዱ ይችላሉ፡፡

ይህ ጥናት የመካከለኛ-ኢንፍራፌድ (መ.ኢ.)ስነ-ስፔክትሮስኮፕ ቴክኖሎጂን ከማሽን ትምህርት ጋር ማዋሃድ፣ የወባ በሽታን ከደረቅ የሰው ደም ጠብታዎች ውስጥ ለማጣራት ፈጣን እና ተስማሚ አማራጭ ዘዴ መሆን አለመሆኑን መርምሯል፡

 ተመራማሪዎቹ የወባ በሽታ በሚያጠቃው የታንዛኒያ ማህበረሰብ በተፈጥሮ ከተበከሉ ግለሰቦች ደረቅ የደም ጠብታዎችን ከመስክ ዳሰሳዎች አግኝተዋል፡፡

የደረቁትን የደም ጠብታዎች የመ.ኢ. ስነ-ስፔክትሮሜትር በመጠቀም ቃኝተዋቸዋል፡፡

 በፖ.ሰ.ም ሙከራዎች የተረጋገጡ ከ123 ወባ ከተገኘባቸው እና 173 ካልተገኘባቸው የተሰሩ የ296 ግለሰቦች ደረቅ የደም ጠብታዎችን ተንትነዋል፡፡

ተመራማሪዎቹ ፣80% የወባ በሽታን የሙከራ ዳታ በመጠቀም የማሽን ትምህርት ስልተ ቀመርን አሰልጥነዋል፤ እንዲሁም በናሙናው ውስጥ ፕላስሞዲየም ፋልሲፓረም ይገኝ እንደሆነ ለመተንበይ የተመቹ ምርጥ ሞዴሎችን ገምግመዋል፡፡

ተመራማሪዎቹ ፕላስሞዲየም ፋልሲፓረም ኢንፌክሽኖችን በመተንበይ 92% ትክክል የሆነ ፣እና የተቀላቀሉ የ ፕላስሞዲየም ፋልሲፓረም ኢንፌክሽኖችን እና ሌላኛው የወባ በሽታ ምክኒያት የሆነውን ጥገኛ ተህዋስ ፕላስሞዲየም ኦቫልን በመተንበይ 85% ትክክል የሆነ የሂሳብ ሞዴል አግኝተዋል፡፡

 የወባ በሽታን ጥገኛ ተህዋስያን ለማግኘት መካከለኛ ኢንፍሬርድ (መ.ኢ.)ስነ-ስፔክትሮስኮፕ ጥቅም ላይ ሊውል እንደሚችል የበፊቱ ምርምር አሳይቷል፡፡

ቴክኒኩ በወባ የተበከሉ እና ያልተበከሉ ከሰው የደም ጠብታ የተገኙ ደረቅ ናሙናዎችን ለመለየት አስተማማኝ ዘዴ መሆኑን ይህ ጥናት አረጋግጧል፡፡

ይህ ነገር አስፈላጊ የሆነበት ምክንያት፣ ለናሙናዎቹ ተጨማሪ አዋሃጅም ሆነ ቅድመ-ማቀነባበርን አላስፈላጊ ስለሚያደርግ ነው፡፡

እንዲሁም፣ኢንፍሬርድ ስነ-ስፔክትሮስኮፕ እና ኬሞሜትሪክስ በመባል የሚታወቁት በመረጃ ላይ የተመሰረቱ የኬሚስትሪ ቴክኒኮች፣በወባ ትንኝ የሚተላለፉ በሽታዎችን በመከታተል ያላቸውን እምቅ ሚና ተጨማሪ ማስረጃን ያቀርባል፡፡

 የዚህ ምርምር አንዱ ገደብ፣ ጥቅም ላይ የዋሉት የናሙናዎች ቁጥር 296 ብቻ እና አነስተኛ መሆናቸው ነው፡፡

ሌላው ፣ተመራማሪዎቹ እንደ ደም ማነስ፣ጾታ፣እድሜ፣እና የማከማቻ ግዜ የመሰሉት ተለዋዋጮች በደም ናሙናዎቹ መበከል እና አለመበከል ላይ ያላቸው ተጽእኖ እንዴት እንደሆነ አለመለየታቸው ነው፡፡


Connections
1 of 5
Comments
0
comment
No comments here
Why not start the discussion?