Skip to main content
SearchLoginLogin or Signup

ሳይንቲስቶቹ ጸረ-ተባይ መድሃኒቶችን እንዲቋቋሙ የሚያስችላቸውን የዲኤንኤ ቅይርታዎችን በደቡብ አፍሪካ ትንኞች ላይ አግኝተዋል፡፡

Amharic translation of DOI: 10.1101/2020.05.05.078600

Published onAug 07, 2023
ሳይንቲስቶቹ ጸረ-ተባይ መድሃኒቶችን እንዲቋቋሙ የሚያስችላቸውን የዲኤንኤ ቅይርታዎችን በደቡብ አፍሪካ ትንኞች ላይ አግኝተዋል፡፡
·

የA 6.5kb ብዘሀ-ጂን መዋቅራዊ ልዩነት፣ በP450-የታረቁ የወባ አስተላላፊ ትንኞች ፓይሪትሮይድን የመቋቋም አቅም በመጨመር የአጎበሩን ውጤታማነት ይቀንሳል፡፡

ትንኞች በጸረ- ተባይ መድሃኒቶች ላይ የሚያሰማሩትን ውስብስብ እና እየተቀየረ የሚሄድ እራሳን የመከላከል  ውጥን ግልጽ ማድረግ  በጸረ-ነፍሳት መድሃኒቶች ላይ የተመሰረቱ እርምጃዎችን ውጤታማነት ለማስጠበቅ ወሳኝ ነው፡፡

እዚህ ጋር፣ የ6.5kb መዋቅራዊ ልዩነት (መ.ል) በ450-የታረቁ የወባ አስተላላፊ ትንኞች ፓይሪትሮይድ  አኖፊለስ ፉኒስተስን ተጋትሮ እና ሳይቶክሮምን ለመምራት የሚጫወቱትን ሚና  ተረድተናል፡፡

ስፍራን በማቀያየሩ ክስትት የፓይሪትሮይድ ተጋትሮ ባላቸው ትንኞች ውስጥ ሙሉ ጂኖም ተዋህደው በመፈራረቅ የብዘሃ- ጂን 6.5kb መ.ል በተባዙት CYP6P9a/bP450ዎች መካከል ተገኝቷል፡፡

የአፍጣኝ ትንታኔ በ17.5-እጥፍ ከፍ ያለ  እንቅስቃሴ (P<0.0001) መ.ል -ተሸካሚ ቁራጭ መ.ል-ነጻ ከሆነው ይልቅ እንደሚበልጥ ግልጽ አድርጓል፡፡

የqRT-ፖ.ሰ.ም የምላሽ እንቅስቃሴ ልኬት፣  ለCYP6P9a/b ለእያንዳንዱ መል  ጂኖታይፕ የማሻሻል ሚናውን አግዟል፤ ይህም የሆነው መ.ል+/ መ.ል+ ሆሞዛይጎት ትንኞች ከሁለቱም ጂኖች፣ ሄትሮዛይጎት መ.ል+/  መ.ል- (1.7-2- እጥፍ) እና ሆሞዛይጎት መ.ል-/መ.ል-(4-5 እጥፍ) የበለጠ ጉልህ የምላሽ እንቅስቃሴ ነበራቸው፡፡

የ ፖ.ሰ.ም ምርመራን መንደፍ በዚህ መ.ል እና በፓይሬሪትሮይድ ተጋትሮ  መካከል ያለውን ጠንካራ ግንኙነት አሳይቷል   (SV+/SV+ vs SV-/SV-; OR=2079.4፣ P=<0.001) ፡፡

የ6.5kb መ.ል በደቡባዊው አፍሪካ በከፍተኛ ሞገድ (80-100%) ሲገኝ፣በምስራቅ/ በመካከለኛው/ምእራብ አፍሪካ ግን የለም፡፡

የምርመራ ጎጆ ተሞክሮዎች እንደሚያሳዩት፣ ሆሞዛይጎት መ.ል ትንኞች በፓይሬትሮይድ- ለታከመ አጎበር (OR 27.7; P < 0.0001) እና ደም ለመመገብ ቢጋለጡ የላቀ የመትረፍ እድል እንዳላቸው አሳይቷል፡፡

በተጨማሪም፣ ከሶስትዮሽ ተጋላጭ ትንኞች ይልቅ ሶስትዮሽ ሆሞዛይጎት ተጋትሮ ያለው (መ.ል+/CYP6P9a_R/CYP6P9b_R) ለአጎበሮች ሲጋለጥ ጠንካራ የተጋትሮ ደረጃን በማሳየቱ የላቀ የበላይነት ተጽእኖ እንዳለው አሳውቋል፡፡

ይህ ጥናት፣የወባ ትንኞች በጸረ-ተባይ መድሃኒቶች ላላቸው የተጋትሮ እድገት እና በፓይሬትሮይድ-ላይ በተመሰረቱ ኦጎበሮች ውጤታማነት ላይ ላላቸው ጎጂ ተጽእኖ የመዋቅራዊ ልዩነቶችን ትልቅ ሚና አጉልቶ ያሳያል፡፡


ሳይንቲስቶቹ ጸረ-ተባይ መድሃኒቶችን እንዲቋቋሙ የሚያስችላቸውን የዲኤንኤ ቅይርታዎችን በደቡብ አፍሪካ ትንኞች ላይ አግኝተዋል፡፡

ሳይንቲስቶቹ ትንኞቹን ለመግደል  የተሰራን ኬሚካል (ጸረ-ተባይ መድሃኒቶች) ለመቋቋም የሚረዳቸው የዲኤንኤ ዝርጋታን አግኝተዋል፡፡

ይህ የዲኤንኤ ዝርጋታ የደቡብ አፍሪካ ትንኞች ወባን ወደ ሰው እንዳያስተላልፉ ለመከላከል በአጎበሮች ላይ የሚደረገውን የተለመደ የጸረ- ተባይ መድሃኒት ፓይሬትሮይድን በተሻለ ሁኔታ እንዲያብላሉት የሚያስችሏቸውን ጂኖች ከፍ የሚያደርግ ይመስላል፡፡

በጸረ- ተባይ መድሃኒት- የታከመ አጎበር ወባ  ተሸካሚ ትንኞች በሽታውን ወደ ሰው እንዳያስተላልፉ  ለመከላከል  አንዱ እና ዋነኛው መንገድ ነው፡፡

ሆኖም ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ትንኞች ለሞት ለሚዳርጉ የጸረ- ተባይ መድሃኒቶች ተጋልጠውም  እየተረፉ ይገኛሉ፡፡

ሳይንቲስቶቹ የወባ በሽታን ለመቆጣጠር የጸረ- ትንኝ አጎበሮች እንዲሻሻሉ ከዚህ ጸረ-ተባይ መድሃኒት ተጋትሮ ጀርባ ያለውን ባዮሎጂካል ምክንያት ለይተው ማውጣት ይፈልጋሉ፡፡

በዚህ ጥናት ተመራማሪዎቹ  በወባ ተሸካሚ ትንኞች ውስጥያለው እና ቅይር የዲኤንኤ ዝርጋታ ፣ ፓይሬትሮይድ ለተባለው ጸረ- ተባይ መድሃኒት ያላቸውን ተጋትሮ እንዴት እንደሚጨምር ማሳየት ይፈልጋሉ፡፡

በተጨማሪ ይህ የጄኔቲክ መላመድ በተለያዩ የአፍሪካ ክልሎች ባሉ ትንኞች  ይገኝ እንደሆነ ለማየት ፈልገው ነበር፡፡

ተመራማሪዎቹ የተለያዩ የወባ ትንኝ ዝርያዎችን ዲኤንኤ ተንትነዋል፤ እናም ትንኞቹ ፓይሬትሮይድን ምን ያህል እንደሚቋቋሙ አረጋግጠዋል፡፡

መደምደሚያ ላይ ለመድረስ በምርመራ ጎጆዎች ውስጥ በተለቀቁ ትንኞች ላይ የኮምፒውተር ሞዴሊንግ፣ የላብራቶሪ ሙከራዎችን፣ እና ፍተሻዎችን ተጠቅመዋል፡፡

በግኝታቸው መሰረት የዲኤንኤ መገኘት የወባ ተሸካሚ ትንኞች በጸረ-ተባይ ለታከሙ አጎበሮች ተጋትሮ እንዲያዳብሩ ያስችላል፡፡

በዚህ ጥናት ውስጥ ፓይሬትሮይድን የሚቋቋሙ ሁሉም ትንኞች ትልቅ ቅይር የዲኤንኤ ዝርጋታ ነበራቸው፡፡

የሚገርመው ግን እነዚህ ትንኞች የመጡት ከደቡብ አፍሪካ ነበር፤ ቅይርታው በምእራብ ፣ምስራቅ ወይም በመካከለኛው አፍሪካ ባሉ ወባ ተሸካሚ ትንኞች ውስጥ አልተገኘም፡፡

ሳይንቲስቶቹ ምንም እንኳ ወባ ተሸካሚ ትንኞች ቀደም ሲል እነሱን ስንገድልባቸው ለነበሩት ኬሚካሎች ተቋቋሚ እየሆኑ መምጣታቸውን አስቀድመው ቢያውቁም፣ ይህ ጥናት በጄኔቲካዊ ደረጃ  እንዴት ጸረ- ተባይ መድሃኒቶችን ማምለጥ እንደቻሉ ያብራራል፡፡

ወደፊት ይህንን ለሚመለከቱ ሌሎች ሳይንቲስቶች ይጠቅም ዘንድ ተመራማሪዎቹ በተጨማሪ በትንኞቹ ውስጥ ያለውን የዲኤንኤ ቅይርታ ለመቆጣጠር የሚያስችል ዘዴን  አዳብረዋል፡፡

መጪው ስራ  ይበልጡኑ የእነዚህ  አይነቶቹን ቅይር ዲኤንኤ ቅደም ተከተል እና በትክክል  በወባ ትንኞች ውስጥ ባሉት ተቋቋሚ ጂኖች ላይ እንዴት ተጽእኖ እንደሚያደርሱ በጥልቀት መመልከት እንዳለበት ተመራማሪዎቹ ይመክራሉ፡፡

በተለይም  በደቡብአፍሪካትንኞቹበጸረ-ተባይመድሃኒትየታከሙአጎበሮችንለማምለጥለምንእንደቻሉየዲኤንኤማስረጃባገኘንበትበአሁኑጊዜየወባበሽታንመስፋፋትለመቆጣጠርአዳዲስዘዴዎችእንደሚያስፈልጉንይህየካሜሩናውያኑተመራማሪዎችጥናትያመለክታል፡፡

Connections
1 of 5
Comments
0
comment
No comments here
Why not start the discussion?