Skip to main content
SearchLoginLogin or Signup

ለምስራቅ አፍሪካ የተመቻቹ የአየር ንብረት ሞዴሎች እ.ኢ.አ 2100 ዓ.ም በጣም ሞቃት ይሆናል ይላሉ፡፡

Amharic translation of DOI: 10.20944/preprints202101.0611.v1

Published onAug 14, 2023
ለምስራቅ አፍሪካ የተመቻቹ የአየር ንብረት ሞዴሎች እ.ኢ.አ 2100 ዓ.ም በጣም ሞቃት ይሆናል ይላሉ፡፡
·

በምስራቅ አፍሪካ CMIP6 ሞዴሎችን በመጠቀም አማካይ የገጽታ ሙቀት መጠን ትንበያ እና ግምገማ

ይህ ጥናት CMIP6 ሞዴሎችን በመጠቀም አማካይ ታሪካዊ የገጽታ ሙቀትን (ከዚህ በኋላ T2m የምንለውን) ይገመግማል፤ እናም T2m በምስራቅ አፍሪካ (ም.አ) በ21ኛው ክፍለ ዘመን እንዴት  እንደሚለወጥ ይመረምራል፡፡

በአማካይ ሁኔታ፣አዝማሚያዎች፣ እና ስታትስቲካዊ መለኪያዎች፣(አድልኦ፣ የተዛምዶ መለኪያ፣የስር አማካይ የካሬ ልዩነት፣ እና የታይለር ክህሎት ውጤት) ላይ የተመሰረቱ ግምገማዎች ተካሂደዋል፡፡

ለ ም.አ የወደፊት ትንበያዎች፣(በታሪካዊ አማካይ የምስለ-ሙቀት  የክንውን ደረጃቸው ላይ በመመስረት)ምርጥ ከዋኝ CMIP6 ሞዴሎች፣ በጋራ ማህበረ -ኢኮኖሚያዊ ጎዳናዎች SSP2-4.5 እና SSP5-8.5 ሁኔታዎች ተተግብረው ነበር፡፡

ታሪካዊ ተመስሎዎቹ ዝቅተኛ ግምትን የሚያሳዩ ጥቂት ሞዴሎች ካሉት የጥናት ክልል ይልቅ፣ በአማካይ አመታዊ T2m ኡደት ላይ ከመጠን ያለፈ ግምትን ያሳያሉ፡፡

በተጨማሪም የ CMIP6 ሞዴሎች በተገመገመው ክልል ቅርበት ውስጥ የሚታዩትን የቦታ እና የጊዜ አዝማሚያዎች አስመስለው በድጋሚ ያቀርባሉ፡፡

በአጠቃላይ በጣም ጥሩ ክንዋኔ ያላቸው ሞዴሎች የሚከተሉት ናቸው፡

FGOALS-g3፣ HadGEM-GC31-LL፣ MPI-ESM2-LR፣ CNRM-CM6-1 እና IPSL-CM6A-LR ::

በሚከተሉት በሶስቱ ከግምት ውስጥ በገቡ የጊዜ ክፋዮች፣ የብዙ ሞዴሎች ስብስብ (ብ.ሞ.ስ) በመጨረሻዎቹ (2080 – 2100) ወቅት፣ የሚጠበቁ በ2.4 °ሴ ለ SSP2-4.5 እና 4.4 °ሴ ለ SSP5-8.5 ሁኔታ ብዙ አማካይ ለውጦችን አሳይቷል፡፡

በሴን ስሎፕ ገማች እና በማን-ኬንዳል ሙከራ የተመሰረተው የለውጥ መጠን በSSP2-4.5 (SSP5-8.5) ሁኔታዎች ስር የ 0.24°ሴ አስርት-1 (0.65°ሴ አስርት-1) ትንበያ ከፍተኛ የመጨመር አዝማሚያዎችን ያሳያል፡፡

ምንም እንኳ ተመሳሳይ ፈጣን የጨረር ሃይል ቢኖራቸውም፣ቀድሞ ከነበሩት አንጻር የቅርብ ጊዜዎቹ የ CMIP6 ሞዴል ውጤቶች ከፍ ያለ ሙቀት እንዳላቸው የዚህ ጥናት ግኝቶች  ያሳያሉ፡፡


ለምስራቅ አፍሪካ የተመቻቹ የአየር ንብረት ሞዴሎች እ.ኢ.አ 2100 ዓ.ም በጣም ሞቃት ይሆናል ይላሉ፡፡

ተመራማሪዎቹ እ.ኢ.አ በ2100 ዓ.ም የሙቀት መጠን እንዴት እንደሚጨምር በተሻለ ሁኔታ ለመተንበይ፣ አሁን ያሉትን በኮምፒዩተር ላይ የተመሰረቱ የአየር ንብረት ሞዴሎችን አመቻችተዋል፡፡

ይህ መረጃ የክልል ባለስልጣናት እንደ የምግብ እጥረት ወይም የተፈጥሮ አደጋዎች ላሉ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽእኖዎች እንዲያቅዱ እና እንዲላመዱ ይረዳቸዋል፡፡

በአለም ሙቀት መጨመር ምክንያት አማካይ የሙቀት መጠኖች ከፍ እያሉ ነው፤ ይህም እንደ ድርቅ እና ጎርፍ ያሉ የከፉ የአየር ሁኔታ ክስተቶችን በማስከተል የበሽታ መሰራጨትን እና የእርሻ ስራ መስተጓጎልን አስከስቷል፡፡

እንደዚህ ያሉ ያልተጠበቁ ክስተቶች ለአየር ንብረት ለውጥ መዘጋጀትን እና መላመድን ፈታኝ ያደርጉታል፤ ስለዚህ ተመራማሪዎች  የአየር ንብረት ለውጥን በተሻለ ሁኔታ ለመተንበይ ሞዴሎችን እየሰሩ ነው፡፡

በዚህ ጥናት ተመራማሪዎች በምስራቅ አፍሪካ ያሉትን ለውጦች በተሻለ መልኩ የሚተነብዩ በተለይም እ.ኢ.አ ከ2021 እስከ 2100 ዓ.ም ባሉት አመታት ውስጥ የነበሩ የአየር ንብረት ሞዴሎችን ለይተው ማወቅ ይፈልጋሉ፡፡

ተመራማሪዎቹ ከኬንያ ፣ኡጋንዳ፣ታንዛኒያ፣ብሩንዲ እና ሩዋንዳ የተመዘገቡትን የሙቀት ቅጂዎች ባሉት 13 ኮምፒውተር-ተኮር የአየር ንብረት ሞዴሎች ውስጥ አስገብተዋል፡፡

የሙቀት ቅጂዎቹ የሚካተቱት እ.ኢ.አ ከ1970 እስከ 2014 ዓ.ም ባሉት አመታት ውስጥ ነው፡፡

ከሌሎች የምስራቅ አፍሪካ መረጃዎች ጋር በጣም ትክክለኛ የሆኑትን 5 ሞዴሎች አጣምረዋል፡፡

ይህን ጥምር ሞዴል የምስራቅ አፍሪካ አየር ንብረት በጊዜ ብዛት እ.ኢ.አ እስከ 2100 ዓ.ም እንዴት እንደሚቀየር ለመተንበይ ተጠቅመውበታል፡፡

ለሁለት የተለያዩ  ሁኔታዎች ትንበያዎችን አካሂደዋል፡፡

አንደኛው የአየር ንብረት ለውጥን ለመቀነስ አዲስ መመሪያዎች የማይተገበሩበት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ መመሪያዎቹ በመጠኑ እንዲዘገይ የሚደረጉበት ነው፡፡

ተመራማሪዎቹ በምስራቅ አፍሪካ ያለው አማካይ የሙቀት መጠን ከ2021 እስከ 2049 በ1 ዲግሪ ሴልሲየስ ቀስ በቀስ እንደሚጨምር ተንብየዋል፡፡

ነገር ግን እ.ኢ.አ ከ2080 እስከ 2100 ዓ.ም የሙቀት መጠኑ ከ2.4 ወደ 4.4 ዲግሪ ሴልሲየስ በፍጥነት እንደሚጨምር ይገምታሉ፡፡

የአየር ንብረት ለውጥን በመጠኑ ሊያዘገዩ ከሚችሉ መመሪያዎች ጋር ሲነጻጸር ፣የአየር ንብረት ለውጥን ሊያዘገዩ የሚችሉ መመሪያዎች ካልቀረቡ፣ አማካይ የሙቀት መጠኑ በ3 እጥፍ ያህል ፍጥነት እንደሚጨምር ተንብየዋል፡፡

እነዚህ ግኝቶች ለምስራቅ አፍሪካ ምርጥ ነባር የአየር ንብረት ሞዴሎችን እና ከ2021 ጀምሮ ለክልሉ በጣም ትክክለኛ አማካይ የሙቀት ትንበያዎችን ለይተው አውጥተዋል፡፡

ይህ መረጃ ወደፊት የሚመጡ ተመራማሪዎች የአየር ንብረት ሞዴሎችን እና ከዚህ አካባቢ ጋር የተያያዙ ትንበያዎችን እንዲያሻሽሉ ይረዳል፡፡

ተመራማሪዎቹ እንደ ድርቅ እና ጎርፍ የመሰሉ አስከፊ የአየር ሁኔታ ክስተቶችን በሚገባ የመተንበይ ስራ የሞዴሎቹን አቅም በማሻሻል መጀመር እንዳለበት ይጠቁማሉ፡፡

ውስብስብ በሆኑ እንደ ተራራ ወይም ሃይቅ ባሉ ቦታዎች ላይ የሞዴሎቹ ትክክለኛነት መሻሻል አለበት ይላሉ፡፡

ይህጥናትየተካሄደውበኡጋንዳ፣ሩዋንዳ፣ሞሮኮእናቻይናተመራማሪዎችነው፡፡

Connections
1 of 5
Comments
0
comment
No comments here
Why not start the discussion?