Description
Lay summary of the research article published under the DOI: 10.1101/2020.04.14.20064717
This is Amharic translation of DOI: 10.1101/2020.04.14.20064717
ቅድመ ወሊድ 37ቱን የእርግዝና ሳምንታት ሳያጠናቅቁ መውለድ ማለት ነው፡፡
ከእናቶች በተወሰደው እዥ ውስጥ ያለው የሴሊኒየም፤ የመዳብ እና የዚንክ ክምችት ከቅድመ ወሊድ ጋር ያለውን ተዛማጅነት ለመገምገም ጥናት ተደርጓል፡፡
በዚህ ምጡን ጉዳይ አካታች ጥናት ውስጥ 181 ነፍሰጡር ሴቶች የተካፈሉ ሲሆን፤ 90/181 (49.7%) በጊዜያቸው የወለዱ ሲሆን፣ 91/181 (50.3 %) ደግሞ ቅድመ ወሊድ ያጋጠማቸው ናቸው፡፡
በአጠቃላይ ለመናገር፣ ከእነዚህ መነሻ እሴቶች ማለትም፤ ከ 47-142ug/L, 0.76-1.59ሚግ/L እና 0.59-1.11ሚግ/L አንጻር በእዥ ውስጥ ያለው የሴሊኒየም ክምችት 77.0; SD 19.4ug/L, መዳብ ደግሞ፣ 2.50; SD 0.52ሚግ/L፤ እንዲሁም የዚንክ መጠን 0.77;SD 0.20ሚግ/L በቅደም ተከተል ነበር፡፡
ወቅቱን ከጠበቀ ውልደት ጋር ስናነጻጽረው፤ ቅድመ ወሊድ ማለት በእዥ ውስጥ ያለው የሴሊኒየም ክምችት 79.7፤ SD 21.6ug/L ፣ የመዳብ ክምችት 2.61፤ SD 0.57ሚግ/L፣ እንዲሁም የዚንክ ደግሞ 0.81፤ SD 0.20ሚግ/L ነበር ማለት ነው፡፡ ሴሊኒየም (74.2;SD 16.5ug/L፤p=0.058)፣ መዳብ ((2.39፤ SD 0.43 mg/L፤ p = 0.004) እና ዚንክ(0.73;SD 0.19ሚግ/L፤P=0.006) በቅደም ተከተል፡፡
በተስተካከለው ትንተና፤ በእናት ውስጥ የሚከሰተው እያንዳንዱ የሴሊኒየም ክምችት ክፍል መጨመር፤ የቅድመ ወሊድ ተጠቂ የመሆን እድልን ያሰፋዋል፡፡ OR 1.01 (95% CI: 0.99; 1.03)፣ p=0.234, መዳብ OR 1.62 (95% CI: 0.80; 3.32); p = 0.184፣ ዚንክ OR 6.88 (95% CI: 1.25; 43.67)፣ p=0.032 ፡፡
ውጤቶቹ እንደሚያሳዩት ከሆነ፣ በእርግዝና ወቅት የሴሊኒየም እና የዚንክ እጥረት አልነበረም፤ ከፍተኛ የመዳብ ክምችትም በእዡ ውስጥ አልተገኘም፡፡
ቅድመ ወሊድ በወላድ እዥ ውስጥ ከሚከማቹ መዳብ እና ዚንክ ጋር ተዛማጅነት ነበረው፡፡
ተመራማሪዎች የሴሊኒየም፤ መዳብ እና ዚንክ ደቂቅ ንጥረ ምግብ ክፍተኛ ክምችትን ቅድመ ወሊድ ባጋጠማቸው ሴቶች ላይ አግኝተዋል፡፡ ሆኖም ግን እነዚህ ከፍተኛ ክምችቶች የመጡት ከሚመገቧቸው ምግቦች ይሁን አይሁን እስካሁን አላወቁም፡፡
ቅድመ ወሊድ የሚከሰተው አንዲት ሴት 37ቱን የእርግዝና ሳምንታት ሳትጨርስ በምትወልድበት ወቅት ነው፡፡
ቅድመ ወሊድ ህጻኑን ከሚያጋጠሙት ከልደት ጉደለቶች ጀምሮ፤ እስከ ሞት የሚያደርሱ አሉታዊ የጤና እክሎች ጋር ተዛማጅነት አለው፡፡
ለቅድመ ወሊድ መከሰት ብዙ ምክንያቶች ሊኖሩ ቢችሉም፤በምግብ እና በአካባቢው ውስጥ የሚገኘው ከፍተኛ የደቂቅ ንጥረ ምግቦች ክምችት ያለው ሚና በአንጻራዊ መልኩ አይታወቅም፡፡
እነዚህ ደቂቅ ንጥረ ምግቦች ለህጻኑ እድገት አስፈላጊ ቢሆኑም፤በብዛት በሚገኙበት ወቅት ምን ሊያጋጥም እንደሚችል ተመራማሪዎቹ መረዳት ይፈልጋሉ፡፡
ለዚህም ጥናት ተመራማሪዎቹ ቅድመ ወሊድ ባጋጠማቸው ሴቶች ውስጥ ያሉትን የሴሊኒየም፤ መዳብ እና ዚንክ መጠኖችን በመለካት ፤ በእነዚህ ጥናት ሲደረገባቸው በነበሩት ደቂቅ ንጥረ ምግቦች ምክንያት ቅድመ ወሊድ የመከሰት እድሉ ምን ያህል እንደሆነ ለመለካት አቅደዋል፡፡
ተመራማሪዎቹ እ.ኢ.አ በሰኔ 2016 ዓ.ም. እና የካቲት 2017 ዓ.ም. መካከል የማላዊ ዋና ከተማ በሆነችው በሊሎንጉዌ ከሚገኙ ሁለት ሆስፒታሎች 181 ሴቶች ወዲያውኑ እንደወለዱ የደም ናሙናቸውን ወስደው ነበር፡፡
የደም ናሙናዎቹንም ኖርዌይ ወደሚገኝ ላብራቶሪ ልከዋቸው ነበር፡፡ እዚያም በውስጣቸው ያለው እዥ (ወይም ምንም ያልተቀላቀለበት ንጹሁ ደም) ተለይቶ ከወጣ በኋላ፣ በውስጡ ያሉትን የሴሊኒየም፤ የመዳብ እና የዚንክ መጠን ለክተዋል፡፡
በጥናቱ ውስጥ ከተካተቱት 181 ሴቶች፣ ግማሽ የሚሆኑት ቅድመ ወሊድ ያጋጠማቸው ሲሆን፤ በእነዚህም ውስጥ ተመራማሪዎቹ ከፍተኛ መጠን ያላቸው የሴሊኒየም፤ የመዳብ እና የዚንክ መጠኖችን አግኝተዋል፡፡
በመቀጠልም ከደቂቅ ንጥረ ምግቦች በተጨማሪ ለቅድመ ወሊድ መከሰት በምክንያትነት የተጠረጠሩትን እንደ እድሜ፤ ጠቅላላ የጤንነት ሁኔታ፤እና የእርግዝና ታሪክ የመሳሰሉትን ሌሎች ምክንያቶች ከግምት ውስጥ ለማስገባት ስሌቶቻቸውን አስተካክለዋል፡፡
የሴሊኒየም እና የመዳብ በከፍተኛ መጠን መገኘት ቅድመ ወሊድን በማስከሰት ረገድ ጉልህ ሚና እንደማይጫወት ነገር ግን የዚንክ በከፍተኛ መጠን መገኘት ቅድመ ወሊድ የመከሰቱን አደጋ በ6 እጥፍ እንደሚጨምረው ደምድመዋል፡፡
ይሁን እንጂ በመርዛማ ተጽእኖዎቹ የሚታወቀው መዳብ በከፍተኛ መጠን መገኘቱ ለተመራማሪዎቹ ስጋት ነበር፡፡
600 ሴቶችን ማሳተፍ የነበረበት ይህ ጥናት በ181 ሴቶች ላይ ብቻ መሰራቱ ፤ ተመራማሪዎቹን ከሴሊኒየም ከፍተኛ ክምችት ጋር የተያያዙትን ችግሮች በአግባቡ ለማግኘት የመቻል አቅማቸውን ገድቦታል፡፡
ለእነዚህ ሶስት ደቂቅ ንጥረ ምግቦች ምንጭ ሊሆኑ የሚችሉትን ምግቦች ለማግኘት፤ የተሳታፊዎቹ የየቀን አመጋገብ ዘይቤ ላይ ምርመራ አልተደረገም፣ የሰውነት ግዝፈት ጠቋሚ መረጃም (BMI) አልተመዘገበም፡፡
ይህ በማላዊ በሚገኙ ነፍሰጡሮች ላይ የሴሌኒየም፤ የመዳብ እና፤የዚንክ ተጽእኖዎችን ለመለካት የተሰራ በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነ ጥናት ነው፡፡
አፍሪካ በጣም ከፍተኛ ቅድመ ወሊድ ከሚከሰትባቸው ቦታዎች አንዷ ናት፡፡ 5% ከሚከሰትባቸው ምእራባዊ ሃገሮች ጋር ስትወዳደር አፍሪካ 18% ላይ ናት፡፡ ስለዚህ ተመራማሪዎች አመጋገብ ለዚህ ሚና ይጫወት እንደሆነ ማወቅ ይፈልጋሉ፡፡
This is Yoruba translation of DOI: 10.1101/2020.04.14.20064717
This is Hausa translation of DOI: 10.1101/2020.04.14.20064717
This is Zulu translation of DOI: 10.1101/2020.04.14.20064717
This is a Luganda translation of DOI: 10.1101/2020.04.14.20064717
This is a Northern Sotho translation of DOI: 10.1101/2020.04.14.20064717