Skip to main content
SearchLoginLogin or Signup

ለሲሞንኮንግ ሌሴቶ ታዳሽ ድብልቅ የሃይል ስርአትን ማስመሰል እና ማሻሻል

This is Amharic translation of DOI: https://doi.org/10.1007/978-3-319-93438-9_9

Published onJun 20, 2023
ለሲሞንኮንግ ሌሴቶ ታዳሽ ድብልቅ የሃይል ስርአትን ማስመሰል እና ማሻሻል
·

ለሲሞንኮንግ ሌሴቶ ታዳሽ ድብልቅ የሃይል ስርአትን ማስመሰል እና ማሻሻል

Abstract

ወጣ ገባ ኮረብታ እና የተራራ ሰንሰለቶች እንዲሁም ብዙም ሰው የማይኖርባቸው የገጠር መንደሮች አብዛኛውን የሌሶቶ መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ የሚወክሉ ሲሆን፣ እነዚህን ርቀው የሚገኙ መንደሮችን ከሃገር አቀፍ የኤሌክትሪክ ፍርግርግ ጋር ማገናኘት በሚገድብ ሁኔታ ውድ እና በገንዘብ ረገድ የማያዋጣ ያደርገዋል።

ይህ የመብራት አቅራቦት እጦት ለቤቶች፣ ለትምህርት ቤቶች፣ ለፖሊስ ጣቢያዎች፣ ለክሊኒኮች እና ለአካባቢው የንግድ ተቋማት በቂ የኤሌክትሪክ ሃይል እንዳይቀርብ ስለሚያደርግ ለብዙ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እድገቶች እንቅፋት ሆኗል።

ይህ የምርምር ወረቀት በሌሶቶ ማሴሩ አውራጃ ለምትገኝ ሴሞንኮንግ ከተማ ታዳሽ ሃይል ድብልቅ የሃይል ማመንጫ ዘዴን እንደአማራጭ ያቀርባል።

ጥናቱ የሴሞንኮንግ ከተማን የጭነት ፕሮፋይል እና የሚገኙትን የፀሀይ ጨረር፣ የንፋስ ፍጥነት እና በአቅራቢያው ካለው የማሌፁኒያኔ ወንዝ የውሃ ፍሰት መጠን የታዳሽ ሀብቶች መረጃን በመጠቀም የድብልቅ ሃይል ስርዓቱን ሞዴል ያደርጋል፤ ያስመስላል እንዲሁም ያሻሽላል።

የHOMER ሶፍትዌር ደረጃውን ከጠበቀ የኤሌክትሪክ ሃይል ዋጋ (LCOE) አንፃር እና የተለያዩ የፀሀይ ብርሃን ጉልበት፣ የንፋስ ተርባይን፣ ሚኒ-ሃይድሮ ተርባይን፣ የዲዝል ዘይት ማመንጫ እና የባትሪ ማከማቻ የመሳሰሉ ታዳሽ እና አማራጭ የሃይል ምንጮች ላይ መሠረት ካደረገው ከፍተኛ የታዳሽ ሃይል ክፍልፋይ አኳያ ተመጣጣኝ የስርዓት ውቅር ለማቅረብ ይጠቅማል።

ለዚህ ርቆ የሚገኝ አካባቢ ላይ ለመተግበር ተስማሚ የሆነውን ሙሉ በሙሉ የሚታደስ የሃይል ስርዓት አዋጭነትን ለመገምገም፣ በፀሀይ ጨረር፣ በንፋስ ፍጥነት፣ በጅረት ፍሰት፣ በዲዝል ዘይት ዋጋ እና በሃይል ጥያቄ ላይ የሴንሲቲቪቲ ትንተና ተከናውኗል።

የማስመሰል ውጤቶች ለገለልተኛ የተመቻቸ የሃይድሮ/ንፋስ/PV/የዲዝል ዘይት/ባትሪ ድቅል ስርዓት ውቅረት LCOE 0.289 ዶላር/kW በታዳሽ የሃይል ክፍልፋይ 0.98 አግኝቷል።

ስለዚህ የዲዝል ዘይት ማመንጫ ለሴሞንኮንግ ሃይል ለማመንጨት ሁሌም አስፈላጊ ይሆናል፡፡ በተለይም በደረቃማ እና ቀዝቃዛው የክረምት ወራት ከግንቦት እስከ መስከረም ባለው ጊዜ፣ የፀሀይ ጨረር እና የጅረት ፍሰት ዝቅተኛ ሲሆኑ እና የሃይል አስፈላጊነቱ ከፍተኛ ደረጃ ላይ በሚሆንበት ወቅት።

Summary Title

ሌሶቶ ውስጥ ያለው ሴሞንኮንግ አቅምን ያገናዘበ ታዳሽ ሃይልን ማመንጨት ይችላል።

ተመራማሪዎች እንደሚሉት፣ ሌሶቶ ውስጥ ራቅ ብሎ በሚገኘው ሴሞንኮንግ አካባቢ፣ በንፋስ፣ በሃይድሮ ኤሌክትሪክ፣ በባትሪ እና በብርሃን ጉልበት በመጠቀም የአካባቢውን የታዳሽ ሃይል ድብልቅ ከ66% ወደ 98% በማሳደግ የኤሌክትሪክ አቅራቦት ወጪን በ40% መቀነስ ይቻላል።

ቀሪው 2% በዲዝል ዘይት ማመንጫዎች ይሸፈናል።

ሴሞንኮንግ የምትባለው ትንሽ ከተማ በማሴሩ አውራጃ በሌሶቶ ውስጥ ከሚገኙት በርካታ ወጣ ገባ ኮረብታዎች እና የተራራ ሰንሰለቶች ውስጥ የምትገኝ ሲሆን ይህም የኤሌክትሪክ አቅራቦትን ውድ ያደርገዋል።

በመሆኑም ሴሞንኮንግ በአሁኑ ጊዜ 66% የኤሌክትሪክ ሃይሉን ለማቅረብ በአካባቢው የማሌፁኒያኔ ወንዝ የሚያመነጨውን የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ሃይል ይጠቀማል።

የተቀረው 34% የሚመጣው ከዲዝል ዘይት ማመንጫዎች ነው።

ይህ ጥናት HOMER (ሃይብሪድ ኦፕቲማይዜሽን ሞዴል ፎር ኤሌክትሪክ ሪኒወብል) ሶፍትዌርን ለመጠቀም የሚያቅደው በጣም በዝቅተኛ ወጪ በክልሉ የሚገኙ የታዳሽ ሃይል ምንጮችን በመጠቀም ሊመነጭ የሚችለውን ከፍተኛ ሃይል ለማስላት ነው።

ተመራማሪዎቹ የተለያየ መጠን ያላቸውን ታዳሽ ሃይል ቴክኖሎጂዎችን እንደ የብርሃን ጉልበት (የፀሃይ ፓነሎች ሃይል)፣ ንፋስ፣ ሃይድሮ ኤሌክትሪክ እና የባትሪ ማከማቻ የመሳሰሉትን ማካተት የሚያስከትላቸውን ተጽእኖዎች በመሞከር የሴሞንኮንግ አካባቢን የኤሌክትሪክ አውታር በኮምፒዩተር ላይ አስመስሎ ለመስራት የHOMER ሶፍትዌርን ተጠቅመዋል።

ተመራማሪዎቹ በሕይወት ዘመናቸው የመሠረተ ልማት አውታሮች ምን ያህል ወጪ እንደሚያስወጡ ለማወቅ ለእያንዳንዱ የኤሌክትሪክ ፍርግርግ ድብልቅ በደረጃ የተቀመጠ የሃይል ዋጋውን (LCOE) ያሰላሉ።

ተመራማሪዎቹ ለሴሞንኮንግ በጣም ርካሹ የኤሌክትሪክ ፍርግርግ አማራጭ የንፋስ፣ የሃይድሮ ኤሌክትሪክ እና የባትሪ ታዳሽ ሃይል ድብልቅ መሆኑን ደርሰውበታል።

ይህ የኤሌክትሪክ ፍርግርግ ድብልቅ 94% ታዳሽ ሃይል ሲሆን የመጨረሻው 6% በዲዝል ዘይት ማመንጫዎች የሚሸፈን ይሆናል።

በ98% ታዳሽ ሃይል ከፍተኛ ድርሻ ያለው አማራጭ የብርሃን ጉልበትን ወደ ርካሹ የኤሌክትሪክ ፍርግርግ ድብልቅ ሲጨምር፣ 2% ብቻ በዲዝል ዘይት ማመንጫዎች እንዲሸፈን ይተዋል።

እነዚህ የHOMER ሶፍትዌር ኮምፒዩተር ማስመሰያዎች ቢተገበሩ በአሁኑ ሰአት ከማሌፁኑያኔ ወንዝ የሚገኘውን እና 66% የሚሸፍነውን ታዳሽ የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ሃይል የኤሌክትሪክ ፍርግርግ ድብልቅን ያሻሽለዋል፡፡ 34% ደግሞ በዲዝል ዘይት ማመንጫዎች ይሸፈናል።

ጥናቱ እንደሚያሳየው 98% ታዳሽ ሃይል ያለው ፍርግርግ ወጪውን በ40% ይቀንሳል።

ጥናቱ ለሴሞንኮንግ ብቻ የሚሰራ መረጃን ተጠቅሟል፣ ይህም ውጤቱ በሴሞንኮንግ ላይ ብቻ ተግባራዊ እንዲሆን ያደርጋል።

ነገር ግን ይህ ጥናት እንደሚያሳየው እንደ ንፋስ፣ ወንዞች እና የፀሀይ ብርሃን የበዛባቸው አካባቢዎች ላይ ያሉ የተፈጥሮ ሃብቶችን መጠቀም፣ በአነስተኛ ወጪ የአካባቢውን እና የሀገር አቀፍ የኤሌክትሪክ ፍርግርጎችን ለማሟላት ያስችላል።

Connections
1 of 5
Comments
0
comment
No comments here
Why not start the discussion?