Skip to main content
SearchLoginLogin or Signup

ኢትዮጽያውያኖች የእንሰት አይነቶችን በማየት ይለዩዋቸዋል፡፡ ነገር ግን እነዚህ የሙዝ ዝርያዎች በጣም ተመሳሳይ ናቸው

Amharic translation of DOI: 10.1101/2020.08.31.274852

Published onJul 16, 2023
ኢትዮጽያውያኖች የእንሰት አይነቶችን በማየት ይለዩዋቸዋል፡፡ ነገር ግን እነዚህ የሙዝ ዝርያዎች በጣም ተመሳሳይ ናቸው
·

የእንሰት ( እንሰት ቬንትሪኮሰም) የጄኔቲክ አወቃቀር እና የጄኔቲክ ልዩነቶች ለባህላዊ ህክምና የሚውሉት የመሬት ዘሮች፣ ስታርቺ ሆነው ከተገኙት የመሬት ዘሮች ጋር ተመሳሳይ ናቸው

የጀርባ ታሪክ:

 እንሰት (እንሰት ቬንትሪኮሰም) በደቡብ እና በደቡብ ምእራብ ኢትዮጽያ የሚመረት ለሰው ምግብነት እና ለእንስሳት መኖ የሚሆን ሁለገብ ሰብል ነው፡፡

ለ20 ሚሊዮን ህዝብ የምግብ ዋሰትና እና ለገጠር ኑሮ እንደ መተዳደሪያ አስተዋጽኦ ያደርጋል፡፡

በባህላዊ መድሃኒትን ጥቅም ላይ የሚውሉ በርካታ ልዩ የእንሰት የመሬት ዝርያዎች ይመረታሉ፡፡

ማህበረ-ኢኪኖሚያዊ ለውጦች እና የሃገሬው ተወላጅ እውቀት ማጣት ጠቃሚ መድሃኒት የመሬት ዘሮች እና ተያያዥ የጄኔቲክ ልዩነቶቻቸውን ወደ እንዲያሽቆለቁል ሊያደርገው ይችላል፡፡

ሆኖም ግን በአሁኑ ጊዜ መድሃኒት የመሬት ዘሮች ከሌሎች የመሬት ዘሮች በባህሪያቸው ይለዩ እንደሆነ አይታወቅም፡፡

እዚህ ጋር የመድሃኒት እንሰት የመሬት ዝርያዎችን ጄኔቲካዊ ልዩነት እናሳያለን፡፡ ይህም ልዩነቶቻቸውን ለመጠቀም እና ውጤታማ ጥበቃን ለመደገፍ ያግዛል፡፡

ውጤቶች:

 51የእንሰት መሬት ዝርያዎችን ጄኔቲክ ልዩነቶች ገምግመናል፡፡ ከነሱም 38ቱ የመድሃኒትነት ዋጋ እንዳለቸው ተዘግቧል፡፡

ከመላው15 ቀላል የቅደም ተከተል ድግግሞሽ ነጥቦች (SSR loci) 38 የጂን መለዋወጦችን ተገኝተዋል፡፡

የሞሊኪላዊ ልዩነት ትንተና (ሞ.ል.ት ) 97.6% የሚሆነው አጠቃላይ የጄኔቲክ ልዩነት በግል 0.024 FST ካላቸው መድሃኒት በሆኑት እና መድሃኒት ባልሆኑት የመሬት ዝርያዎች መካከል እንደሆነ አሳይቷል፡፡

አንድ ጎረቤት አገናኝ ዛፍ፣ ከመሬት ዝርያዎች የዋጋ ጥቅም ጋር ምንም ዝምድና የሌላቸውን አራት የተለያዩ ዘለላዎችን አሳይቷል፡፡

ዋና የቅንጅት ትንተና በቡድኖቹ መካከል ልዩ የሆኑ ዘለላዎች አለመኖር ለባህላዊ መድሃኒትነት በሚውሉ እና ሌሎች የጥቅም ዋጋ ባላቸው የመሬት ዝርያዎች መካከል አነስተኛ ልዩነቶችን እንደሚያሳይም አረጋግጧል፡፡

መደምደሚያ:

 የእንሰት መሬት ዝርያዎቹ የጥቅማቸው ዋጋ ምንም ይሁን ምን ለመድሃኒትነት የሚበቅሉት እና መድሃኒትነት የሌላቸው የመሬት ዝርያዎች፣ ምንም አይነት የጄኔቲክ ልዩነት ማስረጃ ሳያሳዩ ችምችም እንደሚሉ ደርሰንበታል፡፡

ይህ እንደሚጠቁመው የእንሰትን የመድሃኒትነት ባህሪያት ይበልጡን ወደ ውሱን የጄኖቲፒክ ቁጥር ሊገድባቸው ይችላል፡፡ ይህም የአካባቢ እና የአስተዳደራዊ ልምምድ መስተጋብር፣ወይም በከፊል የተሳሳተ ዘገባ ውጤት ነው፡፡

ጥናቱ የእነዚህን የተወሰኑ የመሬት ዝርያዎች የመድሃኒትነት ዋጋ በእጅጉ ለመጠቀም ተጨማሪ ምርመራዎችን የሚያበረታታ የመነሻ መረጃ ይሰጣል፡፡


ኢትዮጽያውያኖች የእንሰት አይነቶችን በማየት ይለዩዋቸዋል፡፡ ነገር ግን እነዚህ የሙዝ ዝርያዎች በጣም ተመሳሳይ ናቸው

ኢትዮጽያውያን እንደሚሉት፣ እንሰት ጥበቃ ሊደረግለት የሚገባ ብዙ አይነት ዝርያዎች ያሉት በጣም አስፈላጊ የሆነ ምግብ እና ባህላዊ የመድሃኒት ሰብል ነው፡፡ ነገር ግን ተመራማሪዎቹ በእነዚህ የመሬት ዘሮች መካከል ጥቂት የጄኔቲክ ልዩነቶችን አግኝተዋል፡፡

 “የመሬት ዘሮች” በእይታ የሚለዩ የተለያዩ የእጽዋት እና የእንስሳት አይነቶች ናቸው፡፡

በኢትዮጽያ የተለያዩ የእንሰት የመሬት ዘሮች የተሰበሩ አጥንቶችን ለመጠገን የጉበት በሽታን ወይም ተቅማጥን ለማከም ለባህላዊ መድሃኒትነት ጥቅም ላይ ይውላሉ፡፡

ሌሎቹ ለምግብነት፣ ለእንስሳት መኖ እና ፋይበር ይውላሉ፡፡ የግንዱ ክፍሎች ሊበሉ ቢችሉም ተክሉ ግን የሚተከለው ለፍሬው ሲባል አይደለም፡፡

በሚያሳዝን ሁኔታ በማህበራዊ-አኮኖሚያዊ ለውጦች እና በሃገር-በቀል እውቀት ማጣት የተነሳ ለመድሃኒትነት የሚውለው የእንሰት አይነት በሰብል ደረጃ ከሌሎቹ ለምግብነት በስፋት ከሚመረቱት የሰብል አይነቶች ይልቅ የበለጠ የመጥፋት አደጋ ላይ ነው፡፡

 በእንሰት ላይ የተሰሩት ቀደምት ጥናቶች ተክሎችን ከተወሰኑ ቦታዎች አንጻር አይተዋል፡፡ ግን በዚህ ጥናት ተመራማሪዎቹ በተለይ ለመድሃኒትነት የሚውለውን እንሰት የጄኔቲክ ልዩነቶች እንዲሁም በመሬት ዘሮች መካከል ያለውን የጄኔቲክ ግንኙነቶች መርምረዋል፡፡

የእንሰት ጄኔቲካዊ አወቃቀር በተሻለ መልኩ በመረዳት ሳይንቲስቶች እነዚህን በባህላዊ እና በቁሳዊ ደረጃ ጠቃሚ የሆኑ ተክሎችን ለመጠበቅ በመረጃ የተደገፉ የጥበቃ ውሳኔዎችን ማድረግ ይችላሉ፡፡

 አስፈላጊ የሆኑትን የመሬት ዘሮች ለመለየት ተመራማሪዎቹ በኢትዮጽያ በአራት የተለያዩ ቦታዎች የመንደሩን ሽማግሌዎች አማክረዋል፡፡

የእነዚህን መድሃኒት የመሬት ዘሮች ጄኔቲካዊ አወቃቀር እርስ በእርሳቸው እና መድሃኒትነት ከሌላቸው እና ለምግብነት ከሚውሉ የመሬት ዘሮች ናሙና ጋር አነጻጽረዋል፡፡

 በሚገርም ሁኔታ ተመራማሪዎቹ በተናጠል በተክሎቹ መካከል ልዩነቶች ቢኖሩም የምግብ እና የመድሃኒት የእንሰት ተክሎች በባህሪያቸው አንዳቸው ካንዳቸው በጣም እንደማይለያዩ አግኝተዋል፡፡

የተለየ የአካባቢ ስም ያሏቸው የመሬት ዘሮች ለመኖራቸው ምንም ማስረጃ አልነበረም፤ ግን ተመሳሳይ በሽታን ለማከም የሚጠቅሙት የመሬት ዘሮች ልዩ የጄኔቲክ ቡድን ይፈጥራሉ፡

እንዲህ ሲባል፣ ተመራማሪዎቹ በልዩ የአካባቢዉ ቋንቋ በሚታወቁት ተክሎች መካከል የቀረበ የጄኔቲክ ዝምድናን አስተውለዋል፡፡ ይህ ማለት የአካባቢው ሰዎች በተወሰኑ የመሬት ዘሮች መካከል ያለውን ልዩነት በእይታ ብቻ የመለየት ምርጥ ችሎታ ኣላቸው፡፡

 እነዚህ ግኝቶች በእንሰት ጄኔቲካዊ አወቃቀር ላይ እያደገ የመጣውን እውቀት ይጨምራሉ፡፡ ይህም ለመድሃኒትነት የሚያስፈልጉትን የመሬት ዘሮች ለመለየት የጥበቃ ጥረቶችን ያግዛሉ፡፡

ይህ የጄኔቲክ መረጃ ለወደፊት ሌሎች ተመራማሪዎች የእንሰትን የመድሃኒትነት ባህሪያት መመርመር እንዲችሉ ሳያግዛቸው አይቀርም፡፡

 ተመራማሪዎቹ ስላገኟቸው የጄኔቲክ መመሳሰሎች ምክንያት ሊሆኑ የሚችሉ በርካታ ነገሮችን ጠቁመዋል፡፡

ለምሳሌ ሁሉም የእንሰት ተክሎች በተወሰነ ደረጃ የመድሃኒትነት ዋጋ ሊኖራቸው ይችላል፡፡ ነገር ግን አንዳንድ የመሬት ዘሮች ከባህላዊ ምክንያቶች የተነሳ ተመራጭነት አላቸው፡፡

ልዩ የሆኑ የመድሃኒትነት ባህሪዎችን በተወሰኑ የእድገት ሁኔታዎች ውስጥ ለሚያዳብሩ አንዳንድ ተክሎች የመድሃኒትነት ዋጋ ከአካባቢያቸው ጋር የተያያዘ ሊሆንም ይችላል፡፡

ለወደፊቱ የተለያዩ የመሬት ዘሮች የሕይወ-ኬሚካል ባህሪያትን ማነጻጸር ስለ ምጡቅ የመድሃኒትነት ዋጋቸው ጥልቅ ግንዛቤዎችን ሊያስጨብጥ ይችላል፡፡

ይህ ጥናት የምግብ ዋስትናን በማሻሻል እና የእንሰት ተክልን የመድሃኒትነት አቅም በመረዳትላይ ያነጣጠረ፣ በዩ.ኬ እና አፍሪካ ላይ ተመስርተው በሚሰሩ ተመራማሪዎች መካከል የተመሰረተ የአንድ ትልቅ ትብብር አካል ነው፡፡

Connections
1 of 5
Comments
0
comment
No comments here
Why not start the discussion?