Skip to main content
SearchLoginLogin or Signup

የስነ ባህሪይ ተመራማሪዎች ብዙም የማይታወቅ የወባ ጥገኛ ተውሳክ እንዴት በአለም ላይ እንደተስፋፋ በዝርዝር ይመዘግባሉ፡፡

Amharic translation of DOI: 10.1101/2020.06.01.127423

Published onAug 14, 2023
የስነ ባህሪይ ተመራማሪዎች ብዙም የማይታወቅ የወባ ጥገኛ ተውሳክ እንዴት በአለም ላይ እንደተስፋፋ በዝርዝር ይመዘግባሉ፡፡
·

በሱዳኑ ፕላዝሞዲየም ቫይቫክስ ውስጥ የሚገኝ ሰፊ ጄኔቲካዊ ልዩነት እና ከሌሎች ጂኦግራፊያዊ ልይቶች ጋር ያለው ጄኔቲካዊ ግንኙነት

ፕላዝሞዲየም ቫይቫክስ ወባ በክስተቱ የማነስ ደረጃ እና በትክክለኛ ምርመራ እጦት የተነሳ በአፍሪካ ችላ የተባለ ትሮፒካል በሽታ ነው፡፡

በቅርብ ጊዜ በምስራቅ አፍሪካ የፕ.ቫይቫክስ አስደናቂ መጨመር እና ወደ ምእራባዊ ሃገሮች መዛመቱም ተዘግቧል፡፡

ይህ ጥናት በሱዳን የሚገኘውን ፕ.ቫይቫክስ ጂኦግራፊያዊ አመጣጥ እና ጄኔቲካዊ ልዩነት በ14 የማይክሮ ሳተላይት ጠቋሚዎች መርምሯል፡፡

በአጠቃላይ 113 ክሊኒካዊ የፕ.ቫይቫክስ ናሙናዎች ከሁለት ወረዳዎች፣ ማለትም ከኒው ሃልፋ እና ከሱዳን ካርቱም ተሰብስበዋል፡፡

በተጨማሪም በፕ.ቫይቫክስ ልይቶች መካከል ያለውን ጄኔቲካዊ ግንኙነት በክልላዊ እና በአለም አቀፋዊ ሚዛን የበለጠ ለማሳደግ ከአለም አቀፍ ጄኔቲካዊ ትንተና መረጃ ቋት የተገኙት 841 ጂኦግራፊያዊ ናሙናዎች በትንተናው ውስጥ ተካተዋል፡፡

ከሱዳን ናሙናዎች መካከል በክልል ሚዛን 91 ልዩ እና 8 የጋራ ተቀራራቢ የቅንጅብራሂ ስብስቦችን ተመልክተናል፡፡

ከሌሎች ጂኦግራፊያዊ ልይቶች ጋር ሲነጻጸር እንዲህ ያለው ከፍተኛ ጄኔቲካዊ ልዩነት ፕ.ቫይቫክስ የመነጨው ከአፍሪካ ነው የሚለውን መላምት ይደግፋል፡፡

በአለም አቀፍ ሚዛን ቀደም ሲል እንደታየው ከአፍሪካ፣ ደቡብ አሜሪካ እና እስያ (ፓፑዋ ኒው ጊኒ እና የሰሎሞን ደሴቶችን ጨምሮ) በሶስቱም ክምችቶች ውስጥ ከተወሰነ ቅልቅል ጋር የተለየ የፕ.ቫይቫክስ ጄኔቲካዊ ስብስብን አስተውለናል፡፡

የዋና አካል ትንተና እና ስርወዘራዊ ዛፍ ተመሳሳይ የክምችት ቅጦችን አሳይተዋል፤ እንዲሁም አፍሪካዊያኑ ልይቶች በአለም ዙሪያ ለታየው ጄኔቲካዊ ልውጠት ያላቸውን ድርሻ አጉልተዋል፡፡

በቅርቡ ሊሆኑ የሚችሉ ትውውቆችን እየጠቆመ የምስራቅ አፍሪካ ፕ.ቫይቫክስ ከጥቂት እስያውያን ልይቶች ጋር ተመሳሳይነትን አሳይቷል፡፡

ውጤቶቻችን ፍሬያማ የቁጥጥር እርምጃዎችን ለመተግበር የማይክሮ ሳተላይት ጠቋሚዎችን ፍቱንነት እየጠቆሙ የሰፊ ጄኔቲካዊ ልዩነቶች ከጉልህ የብዘሃ-ነጥብ ትስስር አለመመጣጠን ጋር ህብረ-ክስተት መኖሩን ያሳያሉ፡፡


የስነ ባህሪይ ተመራማሪዎች ብዙም የማይታወቅ የወባ ጥገኛ ተውሳክ እንዴት በአለም ላይ እንደተስፋፋ በዝርዝር ይመዘግባሉ፡፡

ተመራማሪዎች የተለያዩ ልውጠቶች እንዴት በአለም ላይ ሊሰራጩ እንደቻሉ ለመከታተል የወባ በሽታን ከሚያስከትሉ ጥገኛ ተውሳኮች የአንዱን የስነ ባህሪይ አወቃቀር በዝርዝር አስፍረዋል፡፡

የፕላዝሞዲየም ቫይቫክስ ጥገኛ ተውሳክ ከአፍሪካ የመጣ ሳይሆን አይቀርም ይላሉ፡፡

ተመራማሪዎች ቀደም ሲል በዚህ ጥገኛ ተውሳክ ምክንያት የሚከሰተው የወባ በሽታ መጠን አነስተኛ ነው ብለው ያስቡ ነበር፡፡

ነገር ግን በምስራቅ አፍሪካ እና በሌሎቹም የአለም ክፍሎች በሽታዎቹ በአስደናቂ ሁኔታ እየጨመሩ የመጡ ይመስላል፡፡

የፕላዝሞዲየም ቫይቫክስ (ፕ.ቫ) ወባ ህመሞች አብዛኛውን ጊዜ ከባድ አይደሉም፣ ነገር ግን በቅርብ ጊዜ የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ፕ.ቫ በሰዎች ላይ አድብቶ በመደበቅ በተደጋጋሚ እየበከለ ከስራቸው ሊያስቀራቸው ይችላል፡፡

ይህ ከተደጋጋሚ ህክምና አስፈላጊነት ጋር ኢኮኖሚን ሊጎትት ይችላል፡፡

 በዚህ ጥናት ተመራማሪዎች በአለም አቀፍ ደረጃ በተለያዩ ቦታዎች የተገኙትን የፕ.ቫ  ጥገኛ ተውሳኮች ስነ ባህሪይ ለመተንተን ፈልገዋል፡፡

ይህ ጄኔቲካዊ እና ጂኦግራፊያዊ መረጃ የፕ.ቫ ስርጭትን ለመገደብ እና ወባን በተሻለ ሁኔታ ለማከም የጤና ባለስልጣናትን ሊረዳቸው ይችላል፡፡

ተመራማሪዎቹ በኒው ሃልፋ እና በሱዳን ካርቱም ከሚገኙት የፕ.ቫ ወባ በሽተኞች ጣት ላይ ከተወሰዱ የደም ናሙናዎች ዲኤንኤ አውጥተዋል፡፡

በሌሎች የአፍሪካ፣ ደቡብ አሜሪካ እና እስያ ክፍሎች ከተሰበሰቡ ናሙናዎች የተገኙ መረጃዎችንም ተጠቅመዋል፡፡

በቦታዎች ላይ ተመሳሳይነቶችን እና ልዩነቶችን ለማግኘት ናሙናዎቹን አነጻጽረዋል፡፡

 ተመራማሪዎቹ የፕ.ቫ  ናሙናዎች ስነ ባህሪይ በጥቅሉ ከአንድ አህጉር ከሚገኙ ሌሎች ናሙናዎች ጋር የበለጠ ተመሳሳይ መሆናቸውን ደርሰውበታል፡፡

ይህ ማለት በስነ-ባህሪይው ላይ በመመስረት ናሙናው ከየት እንደመጣ ሊያውቁ ይችላሉ፡፡

በሚገርም ሁኔታ በአፍሪካ ውስጥ የሚሰበሰቡ ናሙናዎች ከሌሎች አህጉራት ከሚመጡ ናሙናዎች ይልቅ ጄኔቲካዊ ልዩነት እንዳላቸው አስተውለዋል፡፡

በሌላ አነጋገር፤ ለምሳሌ የአፍሪካ ናሙናዎች ከሌሎች የአፍሪካ ናሙናዎች ጋር ከሚመሳሰሉት በላይ በእስያ ውስጥ የተሰበሰቡ ናሙናዎች ከሌሎች የእስያ ናሙናዎች ጋር በይበልጥ ይመሳሰላሉ፡፡

በአፍሪካ ያለው የጄኔቲካዊ ልዩነት ፕ.ቫ ከአፍሪካ እንደመጣ ይጠቁማል፡፡

ከደቡብ አሜሪካ ናሙናዎች ይልቅ የአፍሪካ ናሙናዎች ከእስያ ናሙናዎች ጋር ተመሳሳይ መሆናቸውንም ተመልክተዋል፡፡

ይህ ማለት በፕ.ቫ የተያዙ ሰዎች ወይም እንስሳት ምናልባትም በቅርቡ በአፍሪካ እና በኤስያ መካከል ተንቀሳቅሰዋል።

የጥገኛ ተውሳኮችን ስነ ባህሪይ በዚህ መልኩ በዝርዝር ማዘጋጀት ለሳይንቲስቶቹ በሽታ አምጪ ተህዋስያን ወደ ተለያዩ ቦታዎች እንዴት እንደሚዛመቱ ግንዛቤ ይሰጣችዋል፡፡

ተመራማሪዎቹ እንደሚሉት ወደፊት የሚደረጉ ጥናቶች ይህን መረጃ እንደ ተራሮች ያሉ የፕ.ቫን ልውጠቶች የሚወስኑ ጂኦግራፊያዊ ባህሪያትን ለመለየት ሊጠቀሙ ይችላሉ፡፡

ይህንጥናትያካሄዱትተመራማሪዎችመቀመጫቸውበሱዳን፣በኤርትራ፣በፈረንሳይእናበአሜሪካነበር፡፡

Connections
1 of 5
Comments
0
comment
No comments here
Why not start the discussion?