Skip to main content
SearchLoginLogin or Signup

በኤችአይቪ ህመምተኞች ላይ ያለው የጉበት ጉዳት መጠን እና ሊያጋጥሙ የሚችሉ የአደጋ ምክንያቶች

Amharic translation of DOI: 10.1101/2020.11.16.384339

Published onAug 07, 2023
በኤችአይቪ ህመምተኞች ላይ ያለው የጉበት ጉዳት መጠን እና ሊያጋጥሙ የሚችሉ የአደጋ ምክንያቶች
·

ውህድ የጸረ-ኤችአይቪ ህክምና ክስተቶች እና የስጋት ምክንያቶች- በካሜሩን ባሊ ወረዳ ሆስፒታል ውስጥ ባሉ የኤችአይቪ ታማሚዎች መካከል የጉበት ዝለት ክስተት

መግቢያ

የጉበት ዝለት ክስተት ለህይወት አስጊ ሲሆን ውህድ የጸረ-ኤችአይቪ ህክምናውን (ው.ጸ.ኤ.ህ) በመውሰድ የቆዩት ታማሚዎች ላይ የመጨረሻ-ደረጃ የጉበት በሽታን ሊያስከትል ይችላል፡፡

ጥናታችን በገጠር ወረዳ ሆስፒታል ውስጥ ባሉ የው.ጸ.ኤ.ህ የረዥም ጊዜ ተጠቃሚዎች መካከል በው.ጸ.ኤ.ህ ምክንያት የሚከሰተውን የጉበት ዝለት (ው.ም.ጉ.ዝ) አጋጣሚ እና ትንበያዎች ለመገምገም ሞክሯል፡፡

ዘዴዎች፦

ይህም በባሊ ወረዳ ሆስፒታል የተደረገ ሆስፒታል-ተኮር ሰፊ የክፍል በክፍል ጥናት ነው፡፡

የስፔክትሮፎቶሜትሪክ ዘዴ ለአላኒን-አሚኖትራንስፈሬዝ (አላ.አ) እና ለአስፓርቴት-አሚኖትራንስፈሬዝ (አስ.አ) ደረጃዎች ቁጥር መለኪያነት ጥቅም ላይ ውሏል፡፡

አላ.አ እና አስ.አ ከፍ ብሎ የሚታይባቸው ታማሚዎች እንደ ው.ም.ጉ.ዝ ተቆጥረዋል፡፡

የቺ (χ2) ካሬ ሙከራ፣ ANOVA እና ካፕላንሜየር የምዝገባ ማስታወሻ ደረጃ/ የትርፈት ትንተና መረጃውን ለመተንተን ጥቅም ላይ ውለዋል፡፡

በዚህ ትንታኔ ከተካተቱት 350 ተሳታፊዎች ውስጥ [156 (44.6%) ወንዶች እና 194 (55.4%) ሴቶች] እድሜያቸው 43.87 ± 0.79 አመታት (በ20 – 84 አመት የእድሜ ክልል) በዚህ ትንታኔ ውስጥ ተጠቃለዋል፤26 (4.4%) ያህሉ መካከለኛ ው.ም.ጉ.ዝ አጋጥሟቸዋል፡፡

57 (16.3%)፣62 (17.7%) እና 238 (68%) የ ALT + AST ፣ ALT እና AST ከፍ ያሉ ደረጃዎችን በቅደም ተከተል ተመልክተናል፡፡

በጥናቱ ወቅት ሁለቱ ገለልተኛ የው.ም.ጉ.ዝ የትንበያ ምክንያቶች ወንድ ጾታ እና የአልኮል ሱሰኛነት ናቸው፡፡

ማጠቃለያ

በባሊ ውስጥ በኤችአይቪ ኢንፌክት የተደረጉ ታማሚዎች ውስጥ ያለው የው.ም.ጉ.ዝ ስርጭት በቀደምት ጥናቶች ከታየው ያነሰ ነው፡፡

የህክምናው የቆይታ ጊዜ በው.ም.ጉ.ዝ ድግግሞሽ ላይ ምንም ተጽእኖ አልነበረውም፡፡

የአልኮል ሱሰኛነት እና አጫሽነት በው.ም.ጉ.ዝ እድገት ላይ ከፍተኛ ልዩነት አሳይቷል፡፡


በኤችአይቪ ህመምተኞች ላይ ያለው የጉበት ጉዳት መጠን እና ሊያጋጥሙ የሚችሉ የአደጋ ምክንያቶች

በካሜሩን በባሊ ሆስፒታል ወረዳ ውስጥ በውህድ ጸ.ኤ.ህ ምክንያት (ጸረ-ኤችአይቪ ህክምናዎች) በኤችአይቪ በሽተኞች ውስጥ ያለው የጉበት ጉዳት ደረጃ ከቀደምት ጥናቶች ጋር ሲነጻጸር አነስተኛ ነው፡፡

ይሁን እንጂ ጾታ ፣አልኮል መጠጣት፣እና ማጨስ  በኤችአይቪ በሽተኞች ላይ የጉበት ጉዳት የማድረስ ተጽእኖ አላቸው፡፡

በአለም ዙሪያ ከግማሽ በላይ የሚሆኑትን የኤችአይቪ ጥቃቶች ከሳሃራ በታች ያሉትን የአፍሪካ ሃገራት ይወክላሉ፡፡

ወሁድ የኤችአይቪ መድሃኒቶች የሚመከሩ ህክምናዎች ቢሆኑም ውጤታቸው ግን ለታማሚዎች የጉበት መጎዳት ምክንያት ነው፡፡

በጸ.ኤ.ህ የሚደርስ የጉበት ጉዳት ላይ የሚያተኩሩ ብዙ ጥናቶች  የሉም ስለዚህ በዚህ ላይ ተጨማሪ መረጃ ያስፈልጋል፡፡

ሳይንቲስቶቹ በአካባቢው የጉበት ጉዳት ያለባቸው የኤችአይቪ ተጠቂ ሰዎች ምን ያህል እንደሆኑ ማወቅ ፈልገው ነበር፡፡

በተጨማሪም የትኞቹ የአኗኗር ዘይቤዎች በእነዚህ ታማሚዎች ላይ የጉበት ጉዳትን ስጋት እንደሚጨምሩ ማወቅ ፈልገው ነበር፡፡

ተመራማሪዎቹ በባሊ ወረዳ ሆስፒታል ያሉትን እና ከ18 አመት በላይ የሆናቸውን የኤችአይቪ ተጠቂ ታካሚዎች አጥንተዋል፡፡

የደም ናሙናዎች ከሁሉም ታካሚዎች ተወስደው ነበር፤ እናም ከጉበት ጉዳት ጋር የተያያዙ አንዳንድ ፕሮቲኖች መሮር አለመኖራቸውን አጣርተዋል፡፡

ከዚያም የትኞቹ የአኗኗር ዘይቤ ምክንያቶች ከጉበት ጉዳት ጋር ተያያዥነት እንዳላቸው ለመተንበይ የኮምፒዩተር ሞዴሊንግ ተጠቅመዋል፡፡

ተመራማሪዎቹ በኤችአይቪ ተጠቂ ታካሚዎች ውስጥ የጉበት ጉዳትን የሚያመላክቱ ፕሮቲኖች መጠን ከፍተኛ እንደሆነ አረጋግጠዋል፡፡

አንዳንድ የኤችአይቪ ህክምናዎች ከእነዚህ ፕሮቲኖች በከፍተኛ ደረጃ መገኘት ጋር እንዴት እንደተያያዙም  ስራቸው አሳይቷል፡፡

የኮምፒዩተር ሞዴሊንጋቸውም ጸ.ኤ.ህ የሚወስዱ፣ አልኮል የሚጠጡ፣እንዲሁም  ያሚያጨሱ ሰዎች ለጉበት ጉዳት በከፍተኛ ደረጃ ተጋላጭ እንደሆኑ  አሳይቷል፡፡

የኤችአይቪ ተጠቂ ታማሚዎች በሚወስዷቸው ህክምናዎች ምክንያት ለጉበት ጉዳት ሊጋለጡ እንደሚችሉ አስቀድሞ ይታወቅ ነበር፡፡

ይሁን እንጂ ይህ ጥናት በባሊ ወረዳ ሆስፒታል ያሉ የኤችአይቪ ታማሚዎች በየትኛው ደረጃ የጉበት ጉዳት እንደሚያጋጥማቸው ተመልክቷል፡፡

ተመራማሪዎቹ አልኮል መጠጣት እና ማጨስ የኤችአይቪ ታማሚዎችን ለከፍተኛ የጉበት ጉዳት እንደሚያጋልጣቸው ደርሰውበታል፡፡

ተመራማሪዎቹ በዚህ ጥናት ውስጥ የታካሚ መረጃ ገደብ ሳይኖር እንዳልቀረ ያስጠነቅቃሉ፡፡

ከኤችአይቪ ህክምናዎች በተጨማሪ ሌሎች መድሃኒቶችን እንደመጠቀም ያሉትን ሁሉንም ሁኔታዎች ከግምት ውስጥ አላስገቡም፡፡

እንዲሁም ለዚህ ጥናት ጥቅም ላይ የዋለው የህዝብ አይነት ከሌሎች ጥናቶች ጋር ሲነጻጸር እድሜን እና ጾታን አስመልክቶ የተለየ በመሆኑ፣ ድምዳሜው ሌሎች በአፍሪካ ከተደረጉ ጥናቶች ጋር ላይስማማ  ይችላል፡፡

ይህ ጥናት በካሜሩን በአንድ ሆስፒታል ላይ ያተኮረ ሲሆን ግኝቶቹ በሌሎች ክልሎች ወደፊት በሚደረጉ ጥናቶች መረጋገጥ አለባቸው፡፡

አፍሪካ ከፍተኛ የኤችአይቪ ጫና አለባት፡፡

ይህ የካሜሩናውያን ተመራማሪዎች ጥናት በኤችአይቪ ታማሚዎች ጉበት ላይ የሚያጋጥመውን ጉዳት እና  ጉበታቸው የሚጎዳበትን እድል የሚጨምሩ የተለያዩ ምክንያቶችን የሚያሳዩ ጠቃሚ መረጃዎች ላይ ብርሃን ፈንጥቋል፡፡

ይህንንመረጃማግኘቱበኤችአይቪበሽተኞችላይየጉበትጉዳትንለመቆጣጠርሊያግዝይችላል፡፡

Connections
1 of 5
Comments
0
comment
No comments here
Why not start the discussion?