Skip to main content
SearchLoginLogin or Signup

ለካንሰር የመጋለጥ አደጋቸው ከፍተኛ የሆነ አነስተኛ የሲዲ4 ቁጥር እና ኤችአይቪ ያለበቻው የደቡብ አፍሪካ ወጣቶች

Amharic translation of DOI: 10.31730/osf.io/xq6jh

Published onOct 02, 2023
ለካንሰር የመጋለጥ አደጋቸው ከፍተኛ የሆነ አነስተኛ የሲዲ4 ቁጥር እና ኤችአይቪ ያለበቻው የደቡብ አፍሪካ ወጣቶች
·

በደቡብ አፍሪካ ኤችአይቪ ያለባቸው ታዳጊ ጎረምሶች እና ጎልማሶች በካንሰር የመያዝ አደጋ፡ ሃገር አቀፍ የስብስብ ጥናት

የጀርባ ታሪክ፦

ከ2004 እስከ 2014 በደቡብ አፍሪካ ኤችአይቪ ያለባቸው ታዳጊ ጎረምሶች እና ጎልማሶች (ኤ.ያ.ታ.ጎ.ጎ) ላይ የተለያዩ የካንሰር አይነቶች መከሰትን እና የአደጋ መንሰኤዎችን አጥንተናል፡፡

ዘዴዎች፦

በደቡብ አፍሪካ የኤችአይቪ ካንሰር ማች ጥናት ከ15-24 ዓመት ያሉ ሰዎችን አካተናል፤ ከብሄራዊ የጤና ላብራቶሪ ሰርቪስ እና ከብሄራዊ ካንሰር ሬጅስትሪ ከኤችአይቪ ጋር በተያያዙ የላብራቶሪ ልኬቶች ሰፊ ስብስቦች ተገኝተዋል፡፡

በጣም ለተለመዱት የካንሰር አይነቶች የክስተት ምጥነቶችን አስልተናል፡፡

ወሲባዊ ግንኙነት፣ እድሜ፣ የቀን መቁጠሪያ አመትን እና የኮክስ ሞዴሎችን በመጠቀም የተሰላ የሲዲ4 የሴል ቁጥር እና የተስተካከሉ የአደጋ መጠኖች (የ.አ.መ) ከካንሰር ጋር ያላቸውን ግንኙነት ገምግመናል፡፡

ግኝቶች፡

የሚከተሉትን አካተናል 782,454 ኤ.ያ.ታ.ጎ.ጎ (89% ሴቶች)፡፡

ከእነዚህ 867 ያህሉ በካንሰር የተያዙ ሲሆን፣ 429 ያህሉ ካፖሲ ሳርኮማ ፣ 107 ያህሉ ናን ሆድጅኪን ሊምፎማ፣ 48 ያህሉ ሆድጅኪን ሊምፎማ፣ 45 ያህሉ የማህጸን በር ካንሰር እና 32 ያህሉ ደግሞ በሉኪሚያ ተይዘው ነበር፡፡

ከ15-19 እድሜ ክልል ውስጥ ካሉት ቡድኖች ጋር ሲወዳደሩ ከ20-24 አድሜ ክልል ውስጥ ባሉ ሰዎች ላይ ካፖሲ ሳርኮማ በበለጠ ሁኔታ ተከስቶ ነበር፡፡

የወንድ ጾታ ከከፍተኛ የካፓሲ ሳርኮማ ምጥነቶች ጋር የተቆራኘ ሲሆን (የ.አ.መ 2.06, 95% CI 1.61-2.63)፣ ናን ሆድጅኪን ሊምፎማ ደግሞ (የ.አ.መ 3.17, 95% CI 2.06-4.89)፣ ሆድጅኪን ሊምፎማ (የ.አ.መ 4.83, 95% 2.61-8.93)፣ እና ሉኪሚያ

በመነሻ ደረጃ አነስተኛ የሲዲ4 ሴል ቁጥሮች ከከፍተኛ የካፖሲ ሳርኮማ፣ የማህጸን በር ካንሰር፣ ናን ሆድጅኪን እና ሆድጅኪን ሊምፎማ ጋር ተቆራኝተው ነበር፡፡

ትርጓሜ፡

በደቡብ አፍሪካ ኤ.ያ.ታ.ጎ.ጎ ላይ ከኢንፌክሽን ጋር የተያያዙ የካንሰር አይነቶች በጣም የተለመዱ ናቸው፡፡

የእነዚህ ካንሰሮች ሸክም በኤችቢቪ ክትባት፣ በታለመ የኤችአይቪ ምርመራ፣ ጸረ-ኤችአይቪ ህክምና ቀድሞ በመጀመር እና የህክምና ክትትልን በማሻሻል ሊቀንስ ይችላል፡፡


ለካንሰር የመጋለጥ አደጋቸው ከፍተኛ የሆነ አነስተኛ የሲዲ4 ቁጥር እና ኤችአይቪ ያለበቻው የደቡብ አፍሪካ ወጣቶች

ከ15 እስከ 24 እድሜ ክልል ውስጥ ያሉ አነስተኛ የሲዲ4 ቁጥር ያላቸው እና ከኤችአይቪ ጋር የሚኖሩ ሰዎች ለካንሰር የመጋለጥ እድላቸው ከፍተኛ ነው፤ በተለይም የደከሙ ኢሚዩን ሲስተሞችን በሚያጠቁ የቫይረስ ኢንፌክሽኖች ለሚከሰቱ ካንሰሮች ተጋላጭ ናቸው፡፡

ተመራማሪዎቹ ኤችአይቪ ፖዘቲዝ የሆኑ ወጣቶችን ለማህጸን በር ካንሰር መመርመር እና የማህጸን በር ካንሰር ለሚያስከስተው ለኤችቢቪ ወይም ለሂዩማን ፓፒሎማ ቫይረስ መከተብ እንደሚያስፈልግ ይመክራሉ፡፡

በተጨማሪም የበለጠ የኤችአይቪ ምርመራዎችን ማድረግ፣ በተዳከመ የኢሚዩን ሲስተም ምክንያት በቫይረስ ኢንፌክሽኖች የሚፈጠሩ ካንሰሮችን ለመከላከል እና በተቻለ ፍጥነት መደበኛ የጸረ- ኤችአይቪ ህክምና ማድረግን ያበረታታሉ፡፡

በደቡብ አፍሪካ ወጣቶች የኤችአይቪ ኢንፌክሽን ትልቅ የጤና አደጋ ነው፡፡

ሳይንቲስቶች ከኤችአይቪ ጋር የሚኖሩ ሰዎች በካንሰር የመያዝ እድላቸው ከፍተኛ እንደሆነ ያውቃሉ፤ ነገር ግን በተለየ መልኩ በወጣቱ መሃል ያሉ የካንሰር ክስተቶችን አልዳሰሱም፡፡

በዚህ ጥናት ተመራማሪዎቹ ኤችአይቪ ፖዘቲቭ የሆኑ ምን ያህል ወጣቶች ካንሰር እንዳለባቸው እና በተለያዩ የካንሰር አይነቶች የመያዝ አደጋ መንስኤዎች ምን እንደሆኑ ማየት ፈልገው ነበር፡፡

ከ2004 እስከ 2014 ከ15 እስከ 24 ዓመት የእድሜ ክልል ውስጥ ያሉ የተወሰኑ የደቡብ አፍሪካ ታማሚ ሰዎችን ሪኮርድ ዳሰዋል፡፡

ለምሳሌ የታማሚዎቹ ጾታ፣ እድሜ እና የሲዲ4 ቁጥር ከካንሰሮች ጋር ያላቸውን ግንኙነት ዳሰዋል፡፡

ከናን ሆድጅኪንስ ሊምፎማ፣ ሆድጅኪንስ ሊምፎማ ፣ ከማህጸን በር ካንሰር እና ሉኪሚያ  ቀጥሎ ተመራማሪዎቹ እንደዘገቡት ካፖሲ ሳርኮማ በጣም የተለመደው የካንሰር አይነት ነበር፡፡

የኤችአይቪ ህክምና የሚያገኙት አነስተኛ ቁጥር ያላቸው ወጣቶች ስለሆኑ በቫይረስ ኢንፌክሽን ምክንያት የሚከሰተው ካፖሲ ሳርኮማ በጣም የተለመደ ነው ብለው ያስባሉ፡፡

ኤችአይቪ ያለባቸው እና ህክምና የማያገኙ ሰዎች የተዳከ ኢሚዩን ሲስተም ሊኖራቸው ይችላል በዚህም ምክንያት የቫይረስ ኢንፌክሽንን መቋቋም አይችሉም፡፡

ተመራማሪዎቹ በተጨማሪ ከ 20 እስከ 24 እድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ሰዎች ከ15 እስከ 19 ዓመት እድሜ ክልል ውስጥ ካሉት ጋር ሲነጻጻሩ በካንሰር የመያዝ እድላቸው ከፍተኛ ነው፡፡

ለምሳሌ፣ ከ20 እስከ 24 እድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ብዙ ሰዎች በናን ሰርቪካል ካርሲኖማ፣ በማህጸን በር ካንሰር እና በካፖሲ ሳርኮማ እንደተያዙ ደርሰውበታል፡፡

በተጨማሪ ውጤቶቻቸው ወንዶች ከፍተኛ የካንሰር መከሰት ምጥነትን እንዳሳዩ ይጠቁማል ምክንያቱም 11% ወንዶች ብቻ ካንሰር ስለሌላቸው።

ተመራማሪዎቹ ሪፖርት እንዳደረጉት ከሉኪሚያ በስተቀር  አነስተኛ የሲዲ4 ሴል ቁጥር በተለይም ከካፖሲ ሳርኮማ እና ከሁሉም ሌሎች የካንስር አይነቶች ከፍተኛ ምጥነት ጋር ይቆራኛል፡፡

ከ20 እስከ 24 ዓመት ካሉት ሰዎች ጋር ሲነጻጸሩ  ከ15 እስከ 19 ዓመት ያሉት ሰዎች የሲደ4 ሴል ቁጥራቸው  በትንሹ  ከፍ እንደሚል አስተውለዋል፡፡

ይሄ ኤችአይቪ ፖዘቲቭ የሆኑ ወጣቶች በካንሰር የመያዝ አደጋ መጠንን በደቡብ አፍሪካ ዙሪያ በሰፊው ያጠና የመጀመሪያው ጥናት ነው

800 000 ገደማ የሚደርሱ የታማሚ ሪኮርዶችን ቢዳስሱም እንኳ ተመራማሪዎቹ የተወሰኑ የካንሰር አይነቶች ቁጥር አነስተኛ ነበር ብለዋል፡፡

በተጨማሪም የፈለጉትን የአንዳንድ ታማሚዎች መረጃ ማግኘት እንዳልቻሉ ገልጸዋል፡፡

ሌሎችተመራማሪዎችየካንሰርክስተቶችንለመለየትየተለዩዘዴዎችንሊጠቀሙእንደሚችሉአሳስበዋል፤በዚህምምክንያትእነዚህውጤቶችከሌሎችውጤቶችጋርበቀላሉመወዳደርአይችሉይሆናል፡፡

Connections
1 of 5
Comments
0
comment
No comments here
Why not start the discussion?