Skip to main content
SearchLoginLogin or Signup

ሳይንቲስቶች የህክምና አማራጮችን ለመሞከር እና ለማስፋፋት ወባ እንዴት ሴሎችን እንደሚጠልፍ ያጠናሉ፡፡

Amharic translations of DOI: 10.1101/2020.08.31.275867

Published onMay 23, 2023
ሳይንቲስቶች የህክምና አማራጮችን ለመሞከር እና ለማስፋፋት ወባ እንዴት ሴሎችን እንደሚጠልፍ ያጠናሉ፡፡
·

የ CRISPR-Cas9 ሰፊ-ጂኖም ስክሪን በፕላስሞዲየም የጉበት ኢንፌክሽን ወቅት የተለወጠ የማይክሮቲዩቢዩል አደረጃጀት CENPJን እንደ ተቀባይ መቆጣጠሪያ ለይቶታል፡

 

የወባ በሽታ ምልክት ከመታየቱ አስቀድሞ አንድ ነጠላ ፕላስሞዲየም ስፕሮዞይት ሄፕቶሳይትን ይበክላል እነዚህም በከፊል የተቀባዩን ግብአት በመለቃቀም በሺዎች ወደሚቆጠሩ ሜሮዞይትስ ያድጋሉ፡፡

የተቀባዩ ማይክሮቲዩቢዩሎች ተለዋዋጭ በሆነ መልኩ እያደገ ባለው የጉበት ገጽ (ጉ.ገ) ጥገኛ ተውሳክ ዙሪያ እንደሚደራጁ እናሳያለን፡፡

የCRISPR-Cas9 ሰፊ-ጂኖም ስክሪንን በመጠቀም የተቀባይ ሳይቶስኬለተን አደራጆችን የቬስል ዝውውሮችን እና የፕላስሞዲየም ጉ.ጸ እድገትን የሚቆጣጠሩ የER/ጎልጂ የጭንቀት እና የሊፒድ ባዮጀኔስስን ለይተናል፡፡

ሴንትሮሜር ፕሮቲን ጄን (ሴ.ፕ.ጄ) ጨምሮ እነዚህ አዳዲስ የኢንፌክሽን መቆጣጠሪያዎች በኢንፌክሽን ወቅት እንዴት የማይክሮቲዩቢዩል መደራጃ ማእከሎችን (ማ.መ.ማ) መቆጣጠር እንደሚቻል ለመሞገት አነሳስተውናል፡፡

የሴ.ፕ.ጄ መሟጠጥ ይህንን ወደ አካባቢ መመለስን እና የኢንፌክሽን መጨመርን እንደገና አባብሶታል፡፡

በተጨማሪም ጎልጂ በጥገኛ ተውሳኩ ዳር ላይ γ-ቲዩቢዩሊንን በማደራጀት እና የማይክሮቲዩቢዩል ኒውክሌሽንን በማነቃቃት ሴንትሮሶማል ማ.መ.ማ ባለመሆን እንደሚሰራ አሳይተናል፡፡

አንድላይ በሞሆን እንዳሳየነው ፕላስሞዲየም ጉ.ገ ተቀባይ ጎልጂውን ከተቀባይ ኦርጋኔሎች ጋር ወደ PVM በመሆን፣ በMT የታረቁ ቱቦዎችን በመመልመል የጉበት ገጽ እድገትን ይደግፋሉ፡፡

ብዙ ተቀባይ ላይ የታለሙ ፋርማኮሎጂካል ከልካዮች የ ጉ.ገ ኢንፌክሽኖችን ሊገቱ እንደሚችሉ ግኝቶቻችን ይጠቁማሉ፡፡


ሳይንቲስቶች የህክምና አማራጮችን ለመሞከር እና ለማስፋፋት ወባ እንዴት ሴሎችን እንደሚጠልፍ ያጠናሉ፡፡

 ብዙ ጥገኛ ተውሳኮች ለመራባት የተቀባይ ሰው ወይም እንስሳት ሴሎችን አልሚ ምግቦች እና ግብአቶች ለራሳቸው ይጠቀማሉ፡፡

በዚህ ጥናት ተመራማሪዎቹ በጉበት ሴሎች ውስጥ ለወባ ኢንፌክሽኖች ሚና የሚጫወቱ ልዩ ጂኖችን ለይተው አውቀዋል፤ይህም ለወደፊቱ አዲስ የጸረ-ወባ መድሃኒት ግቦችን ሊያስገኝ ይችላል፡፡

 የወባ በሽታ በወባ ትንኝ ንክሻ የሚመጣ በፕላስሞዲየም ጥገኛ ተውሳክ የሚተላለፍ በሰፊው የተሰራጨ እና ለህይወት አስጊ ሊሆን የሚችል በሽታ ነው፡፡

ፕላስሞዲየም ወደ ሰውነት ከገባ በኋላ ለመራባት በቀጥታ ወደ ጉበት ያመራል፤ ይህ የመጀመሪያ ደረጃ ለጸረ-ወባ ህክምና ምቹ ነው፤ምክንያቱም ምንም አይነት የበሽታ ስሜት ካለመኖሩ በላይ በሽታው ሊተላለፍ አይችልም፡፡

በዚህ ጥናት ተመራማሪዎቹ በተበከሉ የጉበት ሴሎች ውስጥ የኢንፌክሽንን እድገት ሊለውጡ የሚችሉ የጂኖች እና የፕሮቲኖችን ልዩ ለውጥ ማግኘት ይፈልጋሉ፡፡

 ተመራማሪዎቹ ጂኖቹ በማይሰሩበት ጊዜ ምን አይነት ለውጦች እና መቼ እንደሚደረጉ ለማየት CRISPR-Cas9 የጂን-አርትኦት ቴክኖሎጂን በመጠቀም የተወሰኑ ጂኖችን ለማስቆም ወይም ለማፍዘዝ ችለዋል፡፡

ከዚያም ሁለቱንም ደህነኛ እና የተበከሉ የጉበት ሴሎችን በወባ ጥግኛ ተውሳክ በክለዋቸዋል፡፡

በተለይም የማይክሮቲዩቢዩሎች (ማ.ቲ) የአፈጣጠር ለውጦችን የመረዳት ፍላጎት ነበራቸው፡፡

እነዚህ ቱቦ-መሰል ውቅሮች ከሌሎች ነገሮች በተጨማሪ ንጥረ ነገሮች እና ጠቃሚ ነገሮች በሴሎች ውስጥ በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ላይ ይሳተፋሉ፤ እና አብዛኛውን ጊዜ በሴል አስኳል ዙሪያ መረብ ይፈጥራሉ፡፡

 ከቁልፍ ግኝቶች አንዱ ፕላስሞዲየም በጉበት ሴሎች ውስጥ ያሉትን ማይክሮቲዩቢዩሎች መጥለፉ ነው፤ ማይክሮቲዩቢዩሎች ለሴሉ አስፈላጊ በሆነው አስኳል ዙሪያ በመከማቸት ንጥረ ነገሮችን እና ጠቃሚ ነገሮችን ከማድረስ ፋንታ፣ ማይክሮቲዩቢዩሎቹ በጥገኛ ተውሳኩ ዙሪያ ተከማችተው ንጥረ-ነገሮችን እና ጠቃሚ ነገሮችን እያደረሱ ጥገኛ ተውሳኩ እንዲራባ ያግዙታል፡፡

ተመራማሪዎቹ CENPJ የተባለውን ፕሮቲን በሚያፈዙበት ጊዜ ጥገኛ ተውሳኩ በጣም በተሳካ መልኩ በዙሪያው ማይክሮቲዩቢዩሎችን መሰብሰብ እንደቻለ እና ተህዋሳቱ አድገው በመተለቅ የራሳቸውን ተጨማሪ ቅጂ እንደሰሩ አስተውለዋል፡፡

ሳይንቲስቶቹ በፕላስሞዲየም ኢንፌክሽን ክብደት ላይ ተጽእኖ ያላቸውን ሌሎች ብዙ ጂኖች መለየት ችለዋል፡፡

 ተመራማሪዎቹ ቀደም ሲል ሌሎች ጥገኛ ተውሳኮች በሴል ውስጥ ያሉትን ግብአቶች ወደ ራሳቸው ለመመለስ ማይክሮቲዩቢዩሎችን እንደገና እንደ አደራጁ አሳይተዋል፡፡

በዚህ ጥናት ተመራማሪዎቹ የፕላስሞዲየም ጥገኛ ተውሳኮች ለራሳቸው እድገት የአልሚ ምግቦችን እና ሌሎች ግብአቶችን አቅጣጫ የመቀየር ስልትን ሊጠቀሙ እንደሚችሉ አረጋግጠዋል፡፡

ወደፊት ሳይንቲስቶቹ ጂኖች እና ጥግኛ ተውሳኮች በሴሎች ውስጥ እንዴት እንደሚገናኙ ያላቸውን ግንዛቤ በመጠቀም አዳዲስ የወባ ህክምናዎችን መለየት እንደሚችሉ ተስፋ ያደርጋሉ፡፡

ምንም እንኳ ተመራማሪዎቹ በወባ በሽታ የመጀመሪያ ደረጃ ወቅት በጉበት ሴል ፕሮቲኖች ላይ አንዳንድ አስደሳች ለውጦችን ለመለየት ቢችሉም የመድሃኒት ግቦችን ለይቶ ማወቅ ይቻል ዘንድ ፕላስሞዲየም የሴል ኬሚስትሪን እና አገልግሎትን እንዴት እንደሚቀይር በትክክል ለመረዳት ተጨማሪ ብዙ ስራ ያስፈልጋል፡፡

 ከእነዚህ የሚበዛው ቁጥር በአፍሪካ ሆኖ አሁንም ከወባ በሽታ በየአመቱ በመቶ ሺሆች የሚቆጠሩ የሞት አደጋዎች ይከሰታሉ፡፡

እንደ አለም የጤና ድርጅት ዘገባ እ.ኢ.አ በ2019 ዓ.ም 90% የሚሆነው አለም አቀፋዊ የወባ ክስተት በአፍሪካ የታየ ሲሆን ይህ ወሳኝ ጉዳይ ተጨማሪ የቁጥጥር እና የጣልቃገብነት ጥረቶችን ይጠይቃል ፡፡


Connections
1 of 5
Comments
0
comment
No comments here
Why not start the discussion?