Skip to main content
SearchLoginLogin or Signup

በአፍሪካ ውስጥ የሄፐታይተስ ቢ ቫይረስ (HBV) መድሃኒት እና የክትባት ማምለጥ ቅይርታዎች ስልታዊ ግምገማ

This is Amharic translation DOI: https:10.1371/journal.pntd.0006629

Published onJun 20, 2023
በአፍሪካ ውስጥ የሄፐታይተስ ቢ ቫይረስ (HBV) መድሃኒት እና የክትባት ማምለጥ ቅይርታዎች ስልታዊ ግምገማ
·

በአፍሪካ ውስጥ የሄፐታይተስ ቢ ቫይረስ (HBV) መድሃኒት እና የክትባት ማምለጥ ቅይርታዎች ስልታዊ ግምገማ:

አስቸኳይ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ

Abstract

እ.ኤ.አ. በ2030 የቫይረስ ሄፐታይተስን ከህዝብ ጤና ችግርነት ለማስወገድ ዓለም አቀፍ የዘላቂ ልማት ግቦች፣ የመከላከል፣ የምርመራ እና የህክምና ስልቶችን የማመቻቸት ጽኑ አስፈላጊነትን ያሳያሉ።

የሄፐታይተስ ቢ ቫይረስ (HBV) የተመረጡ ወይም የተላለፉ ከመቋቋም ጋር የተያያዙ ቅይርታዎች (RAMs) እና ከክትባት ማምለጥ ቅይርታዎች (VEMs) አሁን ያለውን የህክምና እና የመከላከያ ስልቶች ስኬትን ሊቀንሱ ይችላሉ።

እነዚህ ጉዳዮች በአፍሪካ ውስጥ ከፍተኛ የHBV ስርጭት እና አበር አካበሽታ ኤችአይቪ ኢንፌክሽን ላለባቸው ነገር ግን በተለይ ጠንካራ የኤፒዲሚዮሎጂካያዊ መረጃ እጥረት እና ውስን የትምህርት፣ የምርመራ እና የክሊኒካዊ እንክብካቤዎች ላለባቸው ብዙ አካባቢዎች ጠቃሚ ናቸው።

በእነዚህ ህዝቦች ውስጥ ያለው የRAM እና VEM ስርጭት፣ መስፋፋት እና ተፅዕኖ አሁን ባለው ስነ-ጽሁፍ ችላ ተብሏል።

ስለዚህ ከሰሃራ በታች ላለው የአፍሪካ ክፍል ስልታዊ በሆነ የስነ-ጽሁፍ ግምገማ እና ትንታኔ የታተሙ ተከታታይ መረጃዎችን ለማዋሃድ እንዲሁም እነዚህን መረጃዎች በመስመር ላይ(ኦንላይን) የመረጃ ቋት ውስጥ ለማቅረብ ተነሳስተናል (https://livedataoxford.shinyapps.io/1510659619-3Xkoe2NKkKJ7Drg/).

አብዛኛው መረጃ ከHIV/HBV የጋራ ኢንፌክሽን ተጠኚ ቡድን የተሰበሰበ ነው።

በጣም የተለመደው RAM rtM204I/V ብቻውን ወይም ከተዛማች ቅይርታዎች ጋር ተጣምሮ እና በሁለቱም ህክምና ልምድ በሌላቸውም ባላቸውም አዋቂዎች ተለየቶ ይታወቅ ነበር።

እንዲሁም ከክትባት ማምለጥ ጋር የተያያዙትን የrtM204V/I + rtL180M + rtV173L ቅይርታዎች ስብስብ ከ1/3ኛ በላይ የተጠኝ ቡድን ውስጥ ለይተናል።

ምንም እንኳን ቴኖፎቪር ለመቋቋም ከፍተኛ የጀኔቲክ እንቅፋት ቢኖረውም፣ እየወጡ ያሉ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ምንም እንኳን ትክክለኛው ክሊኒካዊ ተጽዕኖ ባይታወቅም ቅርፀ-ብዙነት ከመቋቋም ጋር ሊዛመድ መቻሉ አሳሳቢ ነው።

በአጠቃላይ የተሻሻለ የምርመራ ማጣራት፣ የHBV ከህክምና በፊት እና በህክምና ወቅት የተሻሻለ የላብራቶሪ ግምገማ፣ እና ከላሚቩዲን ብቻ ይልቅ የቴኖፎቪርን ቀጣይነት ያለው አቅራቦት መጀመር በአስቸኳይ ይፈለጋል።

ለሄ.ቢ.ቫ) ምርመራ፣ ክትትል እና ህክምና በእነዚህ በጣም ተጋላጭ አካባቢዎች ውስጥ የህዝብ እና የግለሰብ አቀራረቦችን ለማሳወቅ ተጨማሪ መረጃ ያስፈልጋል።

Summary Title

የHBV መድሃኒት መቋቋም እና የክትባት ማምለጥ ለአፍሪካ አስቸኳይ ጉዳይ ነው

አፍሪካ፣ ክትባት እና መድሃኒት የሚቋቋመው የሄፐታይተስ ቢ ቫይረስ (HBV) ከፍተኛ ስርጭት ያላት ሲሆን፣ ብዙ የኤችአይቪ ኢንፌክሽን ባለባት አህጉር ላይ ትልቅ የጤና ስጋትን ይፈጥራል።

ተመራማሪዎች አፍሪካ በተሻለ የHBV ምርመራ እና ህክምና እርምጃዎች ላይ ኢንቨስት ማድረግ አለባት ይላሉ።

የተባበሩት መንግስታት የዘላቂ ልማት ግቦች (SDG 3) እ.ኤ.አ. በ2030 የቫይረስ ሄፐታይተስ ከህዝብ ጤና ችግርነት እንዲወገድ ጥሪ ያቀርባሉ።

ይህ ማለት የቫይረስ ሄፐታይተስን የመከላከል፣ የመመርመር እና የማከም ሂደቶችን ማሻሻል ማለት ነው።

ነገርግን፣ አንዳንድ የሄፐታይተስ ቢ ቫይረስ (HBV) ቅይርታዎች ለመከላከል እና ለማከም የሚደረጉትን ጥረቶች ያዳክማሉ።

እነዚህ ችግሮች በአፍሪካ ውስጥ ከፍተኛ የHBV እና የኤችአይቪ የጋራ ኢንፌክሽን ባለባቸው ቦታዎች ይገኛሉ

በተጨማሪም፣ HBV አንዳንድ መድሃኒቶችን እንዲቋቋም ወይም በክትባቶች ከሚመነጨው የበሽታ መከላከያ ምላሽ እንዲያመልጥ ስለሚያስችሉት ቅይርታዎች ስርጭት እና ተፅዕኖ ያለው መረጃ ትንሽ ነው።

በዚህ ጥናት ተመራማሪዎች ከሰሃራ በታች ባለው የአፍሪካ ክፍል ያለውን አነስተኛ መረጃ ገምግመው በአንድ ነጠላ የመስመር ላይ (አንላይን) የመረጃ ቋት ውስጥ እንዲገኝ አድርገውታል።

የመረጃ ቋቱ በአፍሪካ ውስጥ የሚገኙ ከመድሃኒት ተቋቋሚ ቅይርታዎች (RAMs) እና ከክትባት ማምለጥ ቅይርታዎች (VEMs) ጋር የተያያዙ ቅይርታዎችን ድግግሞሽ፣ ስርጭት እና አብሮ መከሰት ይገልጻል።

ተመራማሪዎቹ የታተሙትን ጽሑፎች በMEDLINE፣ SCOPUS እና EMBASE የሳይንስ ጆርናል ቤተ-መጻሕፍት ውስጥ በጥቅምት 2017 እና በጥር 2018 መካከል ፈልገዋል።

የሕትመት ዓመቱን፣ የጥናት ንድፍ፣ የናሙና መጠን፣ የጥናት ብዛት፣ የፀረ-ቫይረስ ህክምና እና በእያንዳንዱ እትም ውስጥ የሚገኙ ሌሎች ተዛማች መረጃዎችን መዝግበዋል።

በአፍሪካ ውስጥ በጣም የተለመደው፣ ከመቋቋም ጋር የተያያዘው ቅይርታ rtM204I/V ተብሎ እንደሚጠራ የደረሱበት ሲሆን፣ ይህም ህክምና ባልተደረገላቸው እና ህክምና በተደረገላቸው አዋቂዎች ላይ ተለይቶ ይታወቃል።

ጥናቱ ከክትባት ማምለጥ ጋር የተያያዙትን rtM204V/I፣ rtL180M እና rtV173L ቅይርታዎችን ፈልጎ ያገኘ ሲሆን እነዚህም በብዙ ጥናቶች ከተመረመሩት የተጠኝ ቡድን ሰዎች ውስጥ በአንድ ሶስተኛው ውስጥ እንደተገኙ ተዘግቧል።

ምንም እንኳን እስካሁን ድረስ ለቴኖፎቪር መድሃኒት የማይቻል እንደሆነ ተደርጎ ቢቆጠርም፣ ተመራማሪዎቹ ይህ መድሃኒት የመድሃኒት መቋቋምን እያመጣ ሊሆን እንደሚችል የሚጠቁሙ ቀደምት ምልክቶች እንዳሉት በስጋት ተመልክተዋል።

ግኝቶቹ እነዚህ ቅይርታዎች ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ህዝቦች ላይ ከፍተኛ ስርጭት እንዳላቸው ይጠቁማሉ።

የግብአቶች እጥረት ለHBV ምርመራ ማጣሪያ እጥረት፣ ወጥነት ለጎደለው የመድሃኒት አቅርቦት እና ለክሊኒካዊ ክትትል ዝቅተኛ ተደራሽነት አስተዋጽዖ ያደረገ ሲሆን እነዚህ ሁሉ ደግሞ ለመድሃኒት እና ለክትባት መቋቋም አስተዋጽዖ ያደርጋሉ።

ይህ በአፍሪካ የመጀመሪያው ለHBV ፣ RAMsን እና VEMsን የሚገመግም ስልታዊ ግምገማ ነው።

ካሜሩንን እና ደቡብ አፍሪካን ጨምሮ በአንዳንድ አካባቢዎች በኤችአይቪ የተያዙ ሰዎች ላይ ያለው ከፍተኛ የHBV ኢንፌክሽን ምናልባት በመደበኛ የማጣሪያ እጥረት፣ በግንዛቤ ጉድለት፣ በመገለል፣ በከፍተኛ ወጪ እና በውስን የክሊኒካዊ እና የላብራቶሪ መሠረተ ልማት ምክንያት ቀደም ሲል የHBV ኢንፌክሽን በበቂ ሁኔታ ሪፖርት እንዳልተደረገ አመላካች ሊሆን ይችላል።

የHBV ኢንፌክሽንን የማጣራት ስራ በብዙ የአፍሪካ አካባቢዎች በመደበኛነት የማይከናወን ስለሆነ የHBV ኢንፌክሽን ትክክለኛ ስርጭት እና ባህሪ አይታወቅም።

ተመራማሪዎቹ የHBV የጀኔቲካዊ ቅደም ተከተል ስላላቸው ታካሚዎች በጣም ጥቂት የታተሙ ጥናቶችን ብቻ ለይተው ማወቅ ችለዋል።

ይህ በአፍሪካ ያለውን ከፍተኛ የHBV ቸልተኝነት ችግር እና ከጀኔቲካዊ ቅደም ተከተል መረጃ ጋር የተያያዘ ልዩ ክፍተት እንዳለ ያሳያል።

ዚህ ጥናት ውጤት ተመራማሪዎቹ ተከታታይነት ያለው የመድሃኒት እና የክትባት አቅራቦትን ለማስፋት ፣ ኢንፌክሽኖችን ለመመርመር እና የመድሃኒት መቋቋምን ለመለየት የሚያስችል የማጣሪያ ምርመራ ለማድረግ ዘላቂ የረጅም ጊዜ ኢንቨስትመንትን ይመክራሉ።

ከሰሃራ በታች ላሉ እና በከፍተኛ ደረጃ ተጋላጭ ለሆኑ የአፍሪካ አካባቢዎች ለHBV ምርመራ፣ ክትትል እና ህክምና እና የህዝብ እና የግለሰብ አቀራረቦችን ለማሳወቅ ተጨማሪ መረጃ ያስፈልጋል።

Connections
1 of 5
Comments
0
comment
No comments here
Why not start the discussion?